www.maledatimes.com በችካጎ የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ ያዘጋጀው የሻማ ማብራት ስነ ስርአት በደማቅ ሁኔታ ተከናወነ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በችካጎ የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ ያዘጋጀው የሻማ ማብራት ስነ ስርአት በደማቅ ሁኔታ ተከናወነ

By   /   April 23, 2015  /   Comments Off on በችካጎ የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ ያዘጋጀው የሻማ ማብራት ስነ ስርአት በደማቅ ሁኔታ ተከናወነ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 51 Second

በቺካጎ የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ አዘጋጅነት የተከናወነው ለወገን ጸሎት መታሰቢያ እና የሻማ ማብራት ስነስርአት በደማቅ ሁኔታ ከፍተኛ ህዝብ በተገኘበት ተከናውⶈል ። በእንደዚህ ያለ ጊዜ ብቻም ሳይሆን ቀዳሚ ለሚሆኑ ነገሮች እና ለመልካም ጉዳዮችም ልንገናኝ ይገባናል የዛሬው መምጣታችሁ ሁላችንንም አስደስቶናል ሲሉ ፕረዚዳንቱ ተናግረዋል ።በመቀጠልም የኮሙኒቲው ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር እርቁ ይመር የስደትን አስከፊነት እና ከዛሬ ፵ አመታት በፊት የነበሩ ኢትዮጵያኖች ከሃገራቸው ወጥተው ትምህርታቸውን ተከታትለው መመለስ እንጂ መቅረትን እንደማይፈልጉ ገልጸው ዛሬ ግን ከፍተኛው ቁጥር ያለው ከሰሃራ በታች ካሉት አገሮች መፈናቀሉ እና ወደ ሰው አገር በመጓዝ ህይወቱን ማጣቱ አላስፈላጊ ነው ለዚህም ደግሞ አስፈላጊውን ነገር በማድረግ መፍትሄ መፍጠር ይገባናል ሲሉ ጠቁመዋል ።
በምሽቱ ፕሮግራም ቁጥራቸው በዛ ያለ የተለያየ እምነት ተከታዮች እና በዜግነታቸው ኢትዮጵያዊነት ይሰማናል የኢትዮጵያ ህዝብ ሃዘን ሃዘናችን ነው ብለው ስሜታቸውን በጋራ ለመግለጽ የመጡት ህብረተሰብ በሲቃ እና በለቅሶ ሲራጩ ቆይተዋል ። የዛሬው የምሽት ፕሮግራም በሁለቱም ታላላቅ ሃይማኖት ተቋማቶች ያሉ ወይንም በአስተዳደር ቦታም የተቀመጡ ሰዎች የጋራ ሃሳቦቻቸውን የገለጹ ሲሆን በእስልምና ጉዳይ ላይ ያለውን ወንድማማችነት እና በጋራ ለዘመናት አብሮ የተጓዘ ወዳጅነታችንን በነዚህ አወሬዎች የሆኑ ምንም የእስልምና መንፈስ በሌላቸው ዜጎች ልንቃረን አይገባም ሲሉ ገልጸዋል ።
በተለይም ጆን የተባለው ወጣት ከተሰማው ስሜት እና በደሴ ወሎ አካባቢ በመወለዱ የሁለቱንም እምነት የሚጋራ ከመሆኑም በላይ ወንድሞቼንም ሆነ ዘመድ ወዳጆቼን እንዲሁም ሃገሬን ሲደፈር ዝም ብሎ ማየቱ ይከብደኛል እኛ እንደ እስልምና ተከታይነታችን እኛ፡የምኛመልኸው፡አምላክ፡እንዺሕ፡አያዸርግም፡ሲል እያለቀሰ ገልጾአል ።
በሌላም በኩል ከየመን የመጣች አንዲት ወጣት በየመንም ሆነ በሌሎች አረብ አገራት የኢቶጵያዊ መሞት ዛሬ የጀመረ አይደለም እንዲያውም ዛሬ በጅምላ መገደላችን እና ይፋ በአደባባይ ማውጣታቸው ሊሆን ይችላል እኛን ያሰባሰበን ሆኖም ግን በየመን የሚሞተው ህዝብ ቁጥር የትየለሌ ነው ፤ በጋለ ብረት ተወግቶ የሚሞተው ይበዛል፣ ወይንም ከፎቅ ይወረወራል አልያም ኩላሊቱን አውጥተው ይገሉታል፤ ታዲያ የእኛ ኢትዮጵያዊነት የት ይሆን የተከበረው ስትል የተሰበሰበውን ህዝብ በለቅሶ እንዲታደም አድርጋዋለች። ይህ በእንዲህ እንዳለ በምሽቱ የተለያየ የስነ ግጥም ምሽት ፕሮግራሞች ቀርበዋል IMG_2089የተለያዩ ሰዎች በመድረክ ላይ በመውጣት ሃዘናቸውን ለህዝቡ አካፍለዋል ። በዛሬው ምሽት የተደረገውንም ፕሮግራም እያመሰገንንም ሆነ ሌሎች ህዝቦቻችንን የምንረዳበት መድረክ ቢዘጋጅ የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ በማንኛውም ነገሮች ላይ ሊተባበር እና ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ነጻ ሆኖ ህዝብን ሊያገለግል የተከፈተ ተቋም ስልሆነ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ መጥቶ አስፈላጊውን አገልግሎት ማግኘት ይችላል ሲል ጥሪውንም አስተልፎአል። ማንኛውም ሰው ኮሙኒቲውን በቅርበት ሳያውቅ እና የሚሰራውን ስራ ሳይረዳ ከሚሰጠው አላስፈላጊ የፖለቲካዊ አጀንዳ ይልቅ ኮሙኒቲውን መጥቶ በማየት እና በቅርበት በጋራ በመስራት መለየት የሚቻል ሲሆን ማንኛውም ኢትዮጶያዊ በኢትዮጵያዊነቱ አገልግሎቱ ተካፋይ በመሆን ማግኘት የሚገባውን አግልግሎት ለመስጠትም ዝግጁዎች ከመሆናችንም በላይ የምንቀበለው በደስታ ነው በጋራም መስራት የሚገባንን ነገሮች አብረን ለመስራት ዝግጁ ነን ሲሉ ዶክተር እርቁ ይመር በንግግራቸው አክለው ገልጸዋል ። ማለዳ ታይምስ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on April 23, 2015
  • By:
  • Last Modified: April 24, 2015 @ 5:40 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar