www.maledatimes.com ቤተ-ክርስቲያን የማን ቤት ናት ? - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ቤተ-ክርስቲያን የማን ቤት ናት ?

By   /   March 5, 2015  /   Comments Off on ቤተ-ክርስቲያን የማን ቤት ናት ?

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 40 Second

 

በላስ ቬጋስ ከተማ የምንኖር ህዝበ-ክርስቲያን ፤ በቅርቡ በቤተ-ክርስቲያናችን በደ
ብረ ምህረት
ቅዱስ ሚካኤል ካህናትና በሰበካ ጉባኤው ላይ በተደረገ ምርጫ ምክንያት ችግር ተፈ
ጥሮ ነበር ።
ችግሩን በመመካከር ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ ለአመታት ካገለገሉበት ቤተ-ክርስቲያን
የአሪዞና
የዩህታና የኔቫዳ ሊቀ-ጳጳስን አቡነ ዮሴፍንና ካህናቱን ከስራ የሚያሰናብት ደብዳቤ
ተልኮላቸው
በቅርቡ ወደተገዛው ቤተ-ክርስቲያን ድርሽ እንዳይሉ ይነገራቸዋል ። ጉዳዩ እስከ ፖ
ሊስ ድርሶ
እስካሁን መፍትሄ ያላገኘ ጉዳይ ሆኗል ።
እኔ ዛሬ ይህን መልእክት እንድፅፍ ያነሳሳኝ ማን በደለ ማን ተበደለ ለማለ
ት አይደለም ።
ምንንም ለመወንጀልም ሆነ ለመኮነን ፍላጎትም የለኝም ። ጳጳሱን አቡነ ዮሴፍን ጨም
ሮ ካህናቱ
ወደቤተ ክርስቲያኒቱ እንዳይደርሱ ህጋዊ ደብዳቤ ከደረሳቸው በኋላ ፤ ለጊዜውም ቢሆ
ምእመናኑን ለመሰብሰቢያ ተከራይተውት ከነበረው ቤተ- ክርስቲያን ድረስ ተሂዶ በ
ሲኖዶስ
የተወገዙ ናቸው አታከራዩአቸው በሚል ካህናቱ ቦታ አጥተው ምእመናኑን ባለፈው ሳምን
ት እሁድ
በፓርክ ሰብስበውት ፀሎት ተደርጎ ተበትኖ ነበር ። በዚሁ እለት በፓርኩ የተገኘው
ህዝበ-
ክርስቲያን በሰርቢያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን የመምለኪያ ቦታ የሚያገኝበትን መን
ገድ ለመሻት
ረቡዕ ፊብሩዋሪ 25 ቀን ቀጠሮ ይዞ ተለያዬ ።
በቀጠሮው ቀን የተገናኙት ካህናትና ህዝቡ በዬራሳቸው ዝግጅት አድርገው ነበር የመጡ
ት ።
በእለቱ በብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ግብዣ የዲሲና ሜሪላንድና ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ
አባል ብፁዕ
አቡነ ሳሙኤል ሳይታሰብ በቦታው መገኘት በህዝበ ክርስቲያኑ ላይ ተጨማሪ የደስታ ድ
ባብ
ዘረጋበት ። በመምህር ውብ አምላክ አስተናጋጅነት የተከፈተው የቀጠሮ ጉባኤ በብፁ
ዕ አባታችን
በአቡነ ሳሙኤል ፀሎት ከተከፈተ በኋላ የደብረ- ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ታቦት
በሚቀጥለው
ቀን እንደሚገባ ሲበሰር ወይዛዝርቱ በእልልታ ወንዱ በጭብጨባ መዘምራን በምስጋና
መዝሙር
አዳራሹን ሞሉት ።
ይህን ብስራት የናኙልን ደግሞ የእለቱን ትምህርት “ቤተ-ክርስቲያን የማን ናት ?”
†በሚል ርእስ
የጀመሩት ድምፀ- ነጎድጓዱ ሊቀ-ህሩያን ቀሲስ መላኩ ባወቅ ነበሩ ። በትምህርታ
ቸው ላይ
የዚህች ቤተክርስቲያን አባልነታችሁ በአባልነት ፎርም ሳይሆን በጥምቀታችሁ ነው ሲ
ሉ ህዝቡ
በእኩልነትና በአንድነት መንፈስ የኢትዮጵያ ድርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን አባልነቱን
አረጋገጡለት ።
ክርስቲያኖች በተሰበሰቡበት ሁሉ የእግዚአብሂር መንፈስ ይኖራልና ፤ እዚህ ቤተ-ክ
ርስቲያን
እንዳትደርሱ የተባሉት ካህናት ህዝቡ በሰጣቸው ፍቅርና ሙቀት ፤ ባሳየቸው አንድነት
ፊታቸው
በደስታ ጸዳል ሲሞላና ስብራታቸው ሲጠገን እዚያው የነበርን ሁሉ ምስክሮች ሆንን ።
ንብ ያለአውራው ባዶ እንደሆነ ሁሉ ፤ ህዝበ-ክርስቲያንም ያለ ካህናት ባዶ ነው ።
ንብ በአውራው
አማካይነት የመንጋውን ዘር ቋሚ የህይወት ቀጣይነት እንደሚያረጋግጥ ሁሉ ካህናትም
የምእመናኑን መንፈሳዊ ህይወት ጠባቂዎች ናቸው ። በዚህ ወከባና ጩሀቱ በበዛበት
አለም
ካህናት የእግዚአብሄር እንደራሴዎች ናቸው ። እነዚህን የመንፈስ አባቶች ነው በሥጋ
ዊው ህግ
በብጥሽ ወረቀት ወደቤተ-ክርስቲያኒቱ እንዳይደርሱ የተወሰነባቸው ።
የአምልኮት ተግባራችንን መፈፀም የሚያስችለን ካህናቱ ስርዓተ-ቅዳሴውን ሲመሩት ብቻ
ነው
ያለው ህዝበ-ክርስቲያን አውራዎቹን ይዞ በማምለኪያ ቦታ እጦት ለሳምንታት ተንከራተ
ተ ።

ብርድና ነፋሱ ሳያግዱት ምእመኑ ህጻናት ልጆቹን ይዞ በህዝባዊ ፓርክ ውስጥ የአን
ድ ሰንበት
አምልኮ አደረገ ።
ከላይ የጠቀስኳት የቀጠሮዋ ቀን ፌብሯሪ 25 በላስ ቬጋስ ኔቫዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ
ሳዊ ተዋህዶ
ክርስትያናዊ ታሪክ ታላቅ ቀን ሆና የምትታሰብ ናት ። ምሽት ላይ በሰርቢያ ኦርቶዶ
ክስ ቤተ-
ክርስቲያን አዳራሽ የተሰበሰበው ህዝብ ለላስ ቬጋስ አዲስ የሆነውን የደብረ-ብስራት
ቅዱስ
ገብርኤል ታቦት በማግስቱ እንደሚገባ ብስራቱን ሲሰማ ፤ ታቦታችንማ በድህነት አይገ
ባም ሲል
ሁለት ሰአት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ $104 ሽህ 845 የአሜሪካን ዶላር በማዋጣት አከ
በረው ። ወንዱ
የጣቱን የወርቅ ቀለበት ሴቷ የአንገቷን ሃብል እያወለቀች የታቦቱን ግባት ቀን በደ
ስታ አከበርነው ።
በማግስቱም ታቦቱ ሲገባ የዋዜማው በረከት ያልደረሳቸው ወንድሞችና እህቶች እኛስ ለ
ምን
ይቀርብናል በረከቱ ለኛም ለቤታችንም ይትረፍ በማለት ተጨማሪ $23 ሺህ በማዋጣት
አዲሱን
ታቦት ተቀበሉት ።
ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ዮሴፍ ካደረጓቸው ንግግሮች ውስጥ አንድ የሩሲያ ሰው የትናገረ
ው ነው
በማለት እንዲህ ያሉት ይጠቀሳል ። “ሰው ገፍቶ ገፍቶ ከክርስቶስ እግር ስር ጣለኝ
”†አዎ ይህን
የተናገረው የሩሲያ ታዋቂ ደራሲ ደስተዮቭስኪ ነበር ። ደስቶዮቭስኪ በድርሰት ስራዎ
ቹ ምክንያት
ብዙ መከራ ደርሶበታል ። ከዚያም ፍርድ ቤት ቀርቦ የሞት ፍርድ ተፈርዶበታል ። የ
ፍርድ ቀኑ
ደረሰችና የሞት ቅጣቱን ፈፃሚዎቹ የመስቀያውን ገመድ አንገቱ ውስጥ አስገቧት ። ሸ
ምቀቆው
እየጠበቀ እየጠበቀ ትንፋሹ እያጠረች ስትሄድ ለመጀመሪያ ጊዜ የክርስቶስን ስም ጠር
እንዲያድነው ተማፀነ ። ወዲያው የመሰቀያው ክፍል በር ተከፈተና የሩሲያው ንጉስ መ
ልክተኛ
ፈጥኖ ገባ ። ከንጉሱ የተጻፈውንም መልእክት ከፍ አድርጎ አነበበው ። የሞት ቅጣቱ
ተሽሮ
በሩሲያው ንጉስ ምህረት ተደርጎልሃል የሚል ነበር ። ምሳሌው ለሁላችንም ግልፅ ነው
ብዬ
እገምታለሁ ።
ህዝብ ያቀፈው ህዝብ የወደደው ዘለአለማዊ ነው ። በላስ ቬጋስ ላለፉት አስራ አራት
አመታት
የክህነት ተግባራቸውን ሲያከናውኑ የነበሩት መልአከ-ብስራት ቆሞስ አባ ወልደየሱስም
በተፈጠረው ሁኔታ ምክንያት ጨልሞ የነበረው ፈገግታቸው በምእመናኑ ፍቅርና ሙቀት
እንደተመለሰላቸው ሊቀ-ሕሩያን ቀሲስ መላኩ ባወቅ ሲናገሩ ህዝቡ በእልልታ አዳራሹ
ን ሞላው
በመጨረሻም የብፁዕ ውቅዱስ አቡነ ዮሴፍን መልእክት እንዲህ ይላል ። የአገረ-ስብ
ከቴ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቤተሰቦች ፤ ይህ ያከበራችሁት የደብረ
ብስራት
ቅዱስ ገብረኤል ታቦት የገባባት ቤተ-ክርስቲያን አባልነት በጥምቀታችሁ ብቻ ነው ።
በተለያዩ
ምክያቶች የአባልነት ክፍያ መክፈል ቢያቅታችሁ እንኳ በጥምቀት የክርስቶስ ልጆች ና
ችሁና
አባልነት የሚከለክላችሁ የለም ። የአባልነት መታወቂያ ይኖራችኋል ። ዋናው በሃይማ
ኖታችሁ
መፅናት ነው ። ክርስቲያናዊ ፍቅራችሁና አንድነታችሁን እንዲሁም ፅናታችሁን ይህ ክ
ፉ ቀን
አሳይቶናልና አሁን እንዳላችሁት ሁሉ ሳትለያዩ ተፋቅራችሁ ተከባብራችሁ ኑሩ ። እ
ለሚበድሉን ሁሉ እንፀልያለን ። ይህ ክርስትያናዊ የተሰጠን ግዴታችን ነው ። ከተለ
ዩን ጋርም
በአምላካችን ፈቃድ አንድ እንደምንሆን ተስፋየ ነው ብለዋል ።
ከዚያም ይህች ቤተ-ክርስቲያን የምትተዳደረውም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ
ርዕሳነ ሊቃነ
ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ስር ባለው ሲኖዶስ መሆኑንም ገለፀዋል ።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on March 5, 2015
  • By:
  • Last Modified: March 5, 2015 @ 8:31 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar