www.maledatimes.com “ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በተወረወረ ጫማ ተመቱ!” - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

“ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በተወረወረ ጫማ ተመቱ!”

By   /   February 26, 2015  /   Comments Off on “ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በተወረወረ ጫማ ተመቱ!”

    Print       Email
0 0
Read Time:52 Second

ሰበር ዜና !!

ድርጊቱን ባልደግፈዉም ትኩስ ገራሚ መረጃ እነሆ:-

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ትላንት ፣ የካቲት 18 ቀን 2007 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ላይ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ቤተ መቅደስ ከምእመናን አቅጣጫ በተወረወረ ቀይ ሸራ ጫማ መመታታቸው ታወቀ ፡፡

ቅዱስ ፓትርያርኩን ጫማ በመወርወር የመታው ግለሰብ አስቻለው ግቢ አናጋው ሲባል ፤ የወረወራቸው የኹለት እግሩ ጫማዎች አንዱ ቅዱስነታቸውን ሲመታ ሌላው የመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም አስተዳዳሪ የኾኑትን ንቡረ እድ አባተ ጠምቀን መምታቱን በሥፍራው የነበረው ምንጫችን መመልከት ችሏል ፡፡
እንደምንጫችን ዘገባ ከኾነ ቅዱስ ፓትርያርኩን ጫማውን በመርወር የመታው አስቻለው ጫማውን እየወረወረ ‹‹ ሌባ ፤ የሌባ ወዳጅ ፤›› ሲል ተደምጧል ፡፡ ቅዱስነታቸውም በድንጋጤ ሲያማትቡ ታይተዋል ፡፡

አስቻለው ድርጊቱን ከፈጸመ በኋላ ለማምለጥ ሲሞክር ፓትርያርኩን በማስመረጥ ዋነኛ ተዋናይ የነበሩት የአሲራ መቲራ ገዳም አስተዳዳሪ የኾኑት አባ ገብረ መድኅን እና መምህር ወንድ ይፍራው ተስፋይ ተረባርበው ይዘው በመደብደብ ለፖሊስ ሲያስረክቡ ማየታቸውን የዐይን እማኞች ገልጠው ፤ የመጡትም ፖሊሶች እየደበደቡት ወደ ኹለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ሲወሰወዱት ማየታቸውን ለምንጫችን አረጋግጠዋል ፡፡ ንቡረ እድ አባ ተጠምቀ የመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም አስተዳዳሪ ፣ መምህር ሙሴ ኀይሉ የፓትርያርኩ ፕሮቶኮል ፣ አባ ኪሮስ የፓትርያርኩ የካሜራ ባለሙያ ለፖሊስ ምስክር ኾነው መቅረባቸውን ለማወቅ ተችሏል ፡፡

@አቤላክ !

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on February 26, 2015
  • By:
  • Last Modified: February 26, 2015 @ 9:28 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar