www.maledatimes.com አባ ሕዝቅኤል ለምን ስብሰባ ረግጠው ወጡ ? - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አባ ሕዝቅኤል ለምን ስብሰባ ረግጠው ወጡ ?

By   /   January 22, 2013  /   Comments Off on አባ ሕዝቅኤል ለምን ስብሰባ ረግጠው ወጡ ?

    Print       Email
0 0
Read Time:7 Minute, 34 Second

“የማንም አሿሿሚ አልሆንም የሥልጣን ጥመኞችን አላገለግልም”በማለት አራት ወራት የቀረውን የሲኖዶስ ዋና ጸሐፊነታቸውን የሚለቁ መሆናቸውን በደብዳቤ ገለጡ እየተባለ ሰሞኑን የሚወራላቸው አባ ሕዝቅኤል  ቀደም ሲልም ስብሰባ ረግጠው ቢወጡ የፈረሰው ቀኖና ይመለስ ብለው እንዳልሆነ መታወቅ አለበት

አባ ሕዝቅኤልና በአዲስ አበባ የሚገኙት የሲኖዶስ አባለት ለእርቅና ለሰላም እንዲሁም ለሀያ ዓመታት የዘለቀውን የቤተ ክርስቲያን መለያየት ወደ አንድነት ለማምጣት በቅንነት እና ግልጽ በሆነ መንገድ ቢጓዙ ኖሮ ለዚህ ለከፋ መከፋፈል እንዲሁም ለመንግሥት ጣልቃ ገብነት ባልተዳረጉ ነበር ይልቁንም አባ ሕዝቅኤል  የመንግሥት ጣልቃ ገብነት አለ መባሉ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው እንደሆነና ቅዱስ ሲኖዶስ ለምርጫ የሚያስፈልጉ ደንቦችን ከማውጣት በቀር መንግሥት ጣልቃ አልገባም በማለት በአደባባይ ተናግረው ጸሐይ የሞቀውን እውነት የካዱ አባት ናቸው አቡነ ገብርኤልም ይሕንኑ ሀቅ ክደው በአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ በሰጡት ቃል የአባ ሕዝቅኤልን ውሸት ደግመውታል

ይልቁንም አባሕዝቅኤል በአፋቸው ስለ እርቅና ሰላም እያወሩ እሳቸውና መሰሎቻቸው  ከእኛም ወገን ይድረሰን ከሚሉት ግብረ አበሮቻቸው የሚፈልጉትን ፓትርያርክ ለማስመረጥ የሚሄዱበት መስመር እየተዘጋ በመንግሥት የሚደገፉት የነ አባ ሣሙኤል ክንድ እየበረታ ሲሄድ  ማንንም አሿሿሚ አይደለሁም፤ የሥልጣን ጥመኞችን አላገለግልም ማለቱ እና  አራት ወር የቀረውን የጸሀፊነት ሥልጣን እለቃለሁ ማለቱ ምክንያታዊነቱ  ፈጽሞ አይታይም

ከወያኔ ጋር አብረው አ/አበባ የገቡት አባ ተከስተ የአሁኑአባ ሳሙኤል

በሐቅና በእውነት የአባ ሕዝቅኤል አቋም ሲታይ ፣

1ኛ/የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ከሁለትና ከዚያም በላይ ተከፋፍላ የምትገኘው ፓትርያርክ መርቆሬዎስ ያለ አግባብ በፖለቲካ ውሣኔ መንበራቸውን እንዲለቁ መደረጉን አምነው አይቀበሉም፣

2ኛ/ሕገ ቤተ ክርስቲያን ተጥሶ ፓትርያርክ በሕይወት እያለ አባ ጳውሎስ መሾማቸው ቀኖና መሻሩን አምነው ለመናገር አይደፍሩም ታዲያ የአባ ሕዝቅኤል አቋም እና እውነት የት ላይ ነው ?

ሁሉም ማወቅ ካለበት እርቅ እንዲመጣ የቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት እንዲመለስ ከተፈለገ ከእርቁ በፊት የምርጫ ሕግ ማውጣት ለምን አስፈለገ ? እርቁ መቅደም አልነበረበትም ? አውነት እንነጋገር ከተባለ የሰላሙን በር አስቀድመው የዘጉት አባ ሕዝቅኤል  አይደሉምን ?ከመንፈስ ቅዱስ ሀሳብ ይልቅ የቁጥር ስሌት ገብተው አምስት ስንል ኖረን አራት አንልም ብለው መግለጫ ከመስጠት አልፈው ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን በፓትርያርክነት ለመቀበል አንችልም ይልቁንም  ታሪክ ይፋለሳል አምስተኛ ፓትርያርክ እያልን ኖረን ከ20 ዓመት በኋላ ወደ ኋላ መመለስ አይቻልም፡፡ ይህ አስቸጋሪ ስለሆነ ቀኖናውንም ታሪኩንም የሚጥስ ስለሆነ ነው እንጂ አቡነ መርቆርዮስ ወደ ቦታቸው እንዳይመጡ የጠላ ማንም የለም፡፡ ሁሉም ሰላሙን ፈልጓል፡፡ አቡነ መርቆርዮስ ወደ ሃገር መጥተው በፈለጉበት ቦታ መቀመጥ ይችላሉ፡፡ ሰላሙ ተመስርቶ በውጭ የሚገኙ አባቶቻችን አዚህ መጥተው የመምረጥም የመመረጥም ዕድል ይኖራቸዋል፡፡በፈለጉበት ቦታ እንደማንኛውም ሰው ገብተው መቀመጥ ይችላሉ በማለት በአንድ መጽሔት በሰጡት ቃለ ምልልስ ደግመው አረጋግጠዋል

አባ ሕዝቅኤል እውነት ለመናገር የማይደፍሩ በተለያዩ ሚዲያዎች እንኳን ለሚቀርብላቸው ጥያቄ አስተያየታቸውን  ለመናገር ቀጠሮ የሚያበዙ ነገሮችን በማድበስበስ ግልጽ አማርኛ ለመናገር ቋንቋ የሚያጥራቸው ግለሰብ ናቸው ታዲያ በምን መመዘኛ ነው አባ ሕዝቅኤልን ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ቆሙ የምንለው

ዘመነ ካሣ

ከጀርመን

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on January 22, 2013
  • By:
  • Last Modified: January 22, 2013 @ 2:32 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar