www.maledatimes.com አቶ በረከት ስምኦን በፕረዚዳንት ኦባማ ጉብኝት ሰአት የት ገቡ? - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አቶ በረከት ስምኦን በፕረዚዳንት ኦባማ ጉብኝት ሰአት የት ገቡ?

By   /   July 29, 2015  /   Comments Off on አቶ በረከት ስምኦን በፕረዚዳንት ኦባማ ጉብኝት ሰአት የት ገቡ?

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 41 Second

አቶ በረከት ስምኦን

የወያኔው አንጋፋ ኤርትራዊው (የውሸቱ አምሃራ ነኝ)ባዩ እና የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ በረከት ስምኦን በፕረዚዳንት ኦባማ ጉብኝት ወቅት በየትኛውም ቦታ ያልታዩት እና የህብረተሰብን ቀልብ የገዙት እኝሁ ባለስልጣን የገቡበት አለመታወቁ አሳሳቢ ሆኖአል ፣ታዲያም እንዲህ አይነቱ ሁኔታ ወደ አልተፈለገ መንገድ እንዲታሰብ ያደረገ ሲሆን አንዳንድ የመረጃ ማእከሎች የራሳቸውን ትንታኔ እና የምንጮቻቸውን ዘገባ ይዘው ብቅ ብለዋል እንደ አብነት ያህልም ጎልጉል ማህበራዊ ድህረገጽ አቶ በረከት በህይወት ላይኖሩም ይችላሉ ሲሉ አትተዋል ሆኖም ግን ይህንን ድምዳሜ ላይ ለመድረስ የወያኔ ሚስጥራዊ የደህንነት መረጃ ጠቋሚ አካላትን ለማነጋገር ጥረት ለማድረግ እንሞክራለን ተብሎ ይታሰባል ። ልክ እንደዚህ ቀደሙ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ጉዳይ አሳሳቢነት የእርሳቸውም ጉዳይ ትኩረት መሳቡ አይቀሬ ነው ። ከዚህ በታች ጎልጉል ድህረገጽ ያተመውን ሙሉ ጽሁፍ እንዲህ እናስነብባችኋለን ። ማለዳ ታይምስ

“በረከት በህይወት የሉም!” – ጅዳ የሚገኘው “ብግሻን” ሆስፒታል

ጅዳ ሳውዲ አረቢያ ለህክምና በድብቅ ገብተው የልብ በሽታ ህክምና የተደረገላቸው የህወሃት/ኢህአዴግ ከፍተኛ ሹም በህይወት መኖራቸውን እንደሚጠራጠሩ ከሆስፒታሉ የሚወጡ ምስጢራዊ ምንጮች አረጋገጡ፡፡
በልብ በሽታ የሚሰቃዩት አቶ በረከት ለህክምና ጅዳ ሳውዲ አረቢያ የሚገኝ አንድ ሆስፒታል ህክምናቸውን ተከታትለው ወደ ሃገር ከተመለሱ ወዲህ የጤንነታቸው ሁኔታ እምብዛም ባለመስተካከሉ አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ዙር ወደ ሳውዲ አረቢያ “ብግሻን” ሪፈራል ሆስፒታል ማቅናታቸው ይታወሳል፡፡

አቶ በረከት ስሞኦን ከብስጭት፣ ከተለያዩ የአልኮል መጠጦችና ከአእምሮ አደንዛዥ እጽ እንዲርቁ ተመክረው ጤንነታቸው አስተማማኝ ደረጃ እስኪደርስ የሐኪሞች ቅርብ ክትትል እንደሚያሻቸው ተነግሯቸው በቀጠሮ ቢሸኙም የቀጠሮ ግዜያቸውን አክብረው ዶክተሮቻቸው ጋር መቀረብ አለመቻላቸውን የሚገልጹ የሆስፒታሉ ምንጮች በረከት በህይወት መኖራቸውን ይጠራጠራሉ።

ጅዳ “ብግሻን” ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ የልብ ቧንቧ ማስፋት ህክምና የተደረገላቸው የኢህአዴጉ ሹም ጤንነት ሁኔታ የሚጠበቀውን ያህል ለውጥ አሳይቶ እንዳልነበር ሙያዊ ትንታኔ የሚሰጡ ምስጢራዊ የሆስፒታሉ ምንጮች በሽታው የልብ እንደ መሆኑ መጠን ባልታሰበ ግዜ ባለስልጣኑን ለሞት ሊዳርጋቸው እንደሚችል ከአቶ በረከት ጋር ለመጣ አስታማሚ ገልጸው እንደ ነበር ያስታውሳሉ።

በዚህም መስረት አቶ በረከት ስሞዖን ለሶስተኛ ግዜ ልባቸውን መታየት እንዳለባቸው ተነግሯቸው ቢሰናበቱም በቀጠሮ ቀን ተገኝተው ህክምናቸውን መከታተል ባለመቻላቸው በጤናቸው ላይ ሊያደርስ የሚችለው ተጽዕኖ ከፍተኛ መሆኑን የሚያሳየው የምርመራ ውጤት በረከት ሌላ ሃገር ለህክምና ሄደው ካልሆነ በቀር አሁን ባሉበት ሁኔታ የልብ በሽታው አደጋ ላይ ሊጥላቸው እንደሚችል በመጥቀስ ባለስልጣኑ በህይወት የሉም የሚለውን ጥርጣሬ ያጠናክራሉ።

በአቶ በረከት ስምዖን ጤንነት ዙሪያ ከጅዳ “ብግሻን” ሆስፒታል ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ጥረት እናደርጋለን። (Ethiopian Hagere Jed Bewadi ለጎልጉል የላኩት)

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on July 29, 2015
  • By:
  • Last Modified: July 29, 2015 @ 10:31 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar