www.maledatimes.com ከምርጫው በፊት ልናደርገው የሚገባ ሌላ ምርጫ (ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ ሌና) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ከምርጫው በፊት ልናደርገው የሚገባ ሌላ ምርጫ (ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ ሌና)

By   /   March 22, 2015  /   Comments Off on ከምርጫው በፊት ልናደርገው የሚገባ ሌላ ምርጫ (ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ ሌና)

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 38 Second

 ከገዛኸኝ አበበ ኖርዌይ ሌና

Inline image 1በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ስርዓት በማስመልከት በተለያዩ ድረገጽ እና የዜና አውታሮች ላይ የህዝብን ንቃተ ህሊና ሊይጎለብቱ የሚችሉ የተለያዩ ዘገባዎች ይቀርባሉ። በተለይም ደግሞ ፍትህ፣ነጻነት፣እኩልነትን አስመልክቶ እንዲሁም ሊጀመር ጥቂት ጊዜያት የቀረውንና የኢትዮጵያዊያንን አዕምሮ በያዘው የሀገራችን ምርጫ ዙሪያ መነጋገሩ፣ መከራከሩ እና  ከምርጫው በፊት  መስተካከል የሚገባችውን ነገር ማውሳቱ የሰሞኑ ዓቢይ ጉዳይ ሆኗል። በርግጥ የ1997ቱ ምርጫ የህዝብ ቅስም የተሰበረበት እና እስከአሁንም ድረስ የኢትጵያ ህዝብ ስብራት ያላገገመበት ሁኔታ በስፋት ይታያል። በመሆኑም እንደ እኔ እምነት ፍትህ ከሌለበት ሀገር ከፊታችን ካለው ምርጫ ምንም ይፈጠራል ብዬ የምጠብቀው ነገር ባይኖርም ግን ጥቂት የሚባሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች  ምርጫውን አስመልክቱ እየሰሩት ያለው ቅስቀሳ እና ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የወያኔን መንግስት ከስልጣኑ በማውረድ፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነት እየከፈሉት ያለው መስዋትነትና ሊያስመሰግናቸው ይገባል ባይ ነኝ ።  እርግጥ ነው ከሁሉም አቅጣጫ የሚስተጋባው የኢትዮጵያዊ ድምጽ ሀገርን ከመውደድ እና ለሀገር ነጻነት እንዲሁም ሉአላዊነት የሚከፈል መስዋዕትነት እስከሆነ ድረስ ትግሉ ይፋፋም ይቀጥል ያስብላል።

ፍትህ የሰፈነበት ምርጫ ሊካሄድ የተገባ መሆኑን ሁላችንም እንስማማበታለን። የሁላችንም የኢትዮጵያ ልጆች ናፍቆት ሰላም የሰፈነባት ሀገር ላይ ምርጫው የህዝብ እንዲሆን ነው። ይህም ህልም በምድራችን ላይ ተጨባጭ ይዞታ ኖሮት  ተግባራዊ ቢሆን ሀገራችን ምን አይነት ቅርጽ ሊኖራት እንደሚችል ማሰብ ከባድ አይደለም። ስለሆነም በአሁን ወቅት   በምድሪቷ ላይ እየገነነ የመጣው ግፋዊ  አገዛዝ ወደበለጠ ደረጃ ደርሶ እጅግ ከመክፋቱ በፊት የትውልድ ሁሉ ናፍቆት የሆነውን እኩልነት እና  ህዝብ ለብዙ ጥፋት ታልፎ በተሰጠበት እንዲሁም ከሀገሪቷ ፊት ለፊት ታላቅ የሆነ ክስረት ተጋርጦ ባለበት የአምባገነን ስርዐት ዘመን የሰከነና የተረጋጋ ህይወትን በኢትዮጵያ ላይ ለማምጣት ታላቅ የሆነ ርብርቦሽ ያስፈልጋል።

ይህንን በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የዘቀጠ የፓለቲካ ስርዐት ወደኋላ ከተጎተተበት ኢፍትሐዊ አሰራሩ ተናጥቆ ለማውጣት እና የሰለጠኑ ሀገራት ወደደረሱበት የነጻነትና እና የእኩልነት ክልል ለማድረስ ከጨዋታ ውጪ የተደረጉት የኢትዮጵያ ምሁራን እና ከማንኛውም የእድገት  እንቅፋቶች የጸዳ አላማ ያላቸው ሀገር ወዳዶች የተዘጋባቸው በር ክፍት ሆኖ  በሁሉም ሀገራዊ አቅጣጫ ጉዳይ ላይ ለምድራቸው የሚቻላቸውን አስተዋጾ እንዲያደርጉ በተለይም ደግሞ ከፊት ለፊታችን በወያኔ ቁጥጥር ስር ያለው ምርጫ በህዝብ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን የኢትዮጵያ ሊሂቃን እድሉ ያለምንም ተጽእኖ በነጻነት ተሰጥቷቸው እንዲሳተፉ ማድረግ ተመራጭነት አለው። ይህን መሰሉ ተግባር በምድሪቷ ላይ የጸና እስከሚሆን ድረስ  እንዲሁም የገዥውን ቡድን እድሜ መቀጠል ፣ የተመዘበሩ ኮሮጆዎች እና የምርጫ ዕቃ ዕቃ ጨዋታ ወቅታቸውን እየጠበቁ ያለፈውን ልማዳቸውን ለመድገም የሚደረጉት እንቅስቃሴዎች ተፈጻሚ ከመሆናቸው በፊት በሁሉም አቅጣጫ መታገል እንደሚገባን እና ከምርጫው በፊት ህዝባዊ አመጽ እንደ አማራጭ ከመውሰድ  በስተቀር በሌላ መንገድ ወያኔን ማክሸፍ እንደማይቻል ሊታወቅ ይገባል።

እውነታውን በመሸፋፈን  ወያኔ በምግብ ራሳችንን ችለናል እያለ  በሚቀልድበት በዚህ የረሀብ ዘመን ዘወትር ሽቅብ እየወጣ ሰማይ ለመንካት እየተመነጠቀ ስላለው የኑሮ ውድነት ህዝቡም ሲያወራ ወያኔም ስለ ‹‹11%›› እድገት ሲደሰኩር፣ ህዝብ ስለ ስራ-አጥነት እና  እርዛት ሲያወራ ወያኔ ‹‹ስለኢንቨስትመንት መስፋፋት›› ሲያብራራ፣ ህዝብ ስለረሃብ ሲያወራ መንግስት ‹‹ስለጥጋብ›› መፈክሩን ሲያሰማ ፤ ህዝብ ስለዳቦ ሲጮህ የወያኔ መንግስት ‹‹ስለመሰረተ ልማት›› እያወሩ እርስ በርስ መግባባት ተስኗ ቸው 23ኛ አመት ዐመት አልፎ ተጋምሷል ። ይህ ያላቻ ጋብቻ ይባላል። በድግሳቸው ቀን  አንዱ የደስታ ሌላኛው የሃዘን ሻማ በማብራት አክብረው አሳልፈዋል፡፡ ከእንደዚህ አይነት ስርዓት አልባ ገዢ ጋር ፍቺ ብቸኛ አማራጭ ነው። ምርጫውም ፍትሀዊ እና የህዝብ ካልሆነ በስተቀር ለኢትዮጵያዊያን የሚያመጣው ምንም አይነት ፈውስ እንደሌለው የታወቀ ይሁን። ይልቁኑም የከዚህ በፊቱን ውሸት እና ማስመሰል ረቀቅ ባለ ማደናገሪያው ለመድገም እየተሯሯጠ መሆኑ ግልጽ በሆነበት በዚህ ወቅት አምባገነኑን ወያኔን ከምርጫው ውጭ ለማድረግ በየትኛው ጎዳና ብንሔድ በትግላችን ግቡን እንደምንመታ  እና የተለያዩ የትግል ልምድ ስልቶች ልውውጥ አድርገን ሀይላችንን በማጠናከር በአንድ የተባበረ ኢትዮጵያዊ ክንድ ከምርጫው በፊት ህዝባዊ አመጽን  የሁላችን ምርጫ ይሁን በማለት መነሳት አለብን።

የኔ የግል ምልከታዬ በአሁን ሰአት ሀገራችን ባለችበት ደረጃ የትግላችን ኢላማ እና መድረሻው መሆን የተገባው አስቀድሞ በሐስት የወያኔ ነቢያቶች ለተነበዩለት   ምርጫ ተባባሪ ሆኖ በመሰለፍ አምባገነኑ አገዛዝ እንዲቀጥል አስተውጽኦ ማበርከት ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚወስነውሀገር የምትተዳደርበት ልማታዊ የሆነ ህግ በምድሪቷ ላይ የበላይ እንዲሆን የዜጎች እኩልነት እና ሰብዓዊነት የሚከበሩባቸው ስርዓት በማስፈን ወያኔ በጭቆና የተቆጣጠርውን ስልጣን በመቀማት የህዝብ የስልጣኑ ባለቤት ሆኖ  ፍጹም የሆነ ብሩህ ተስፋ የሚታየባትን ኢትዮጵያን መፍጠር  ነው።

መቼውንም ቢሆን ወያኔ ለነጻ ፍትሀዊ ምርጫ እና ለኢትዮጵያ ህዝብ የበላይነት ለምን አልቆመም ተብሎ አይጠየቅም። ምክንያቱም ይህ ቡድን “ከጅብ ጅማት የተሰራ ክራር ምንጊዜም ቅኝቱ እንብላ እንብላ ነው” እንዲሉ ከፅንሰቱም ፀረ ኢትዮጵያዊ መሆኑ የታወቀ ነው። ከዚህ አስከፊ ስርዓት መልካም የሆነ አስተዳደር መጠበቅ የሚታሰብ አይደለምና እንደገና ሌላ ምዝበራ በሀገርችን ላይ ከመፈፀሙ በፊት ምርጫው ጋር ሳንደርስ በፊት የህዝባዊ አመፅ ትግልን በመምረጥ ወደ ውጤት እንጓዝ።  ምርጫው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚመርጠው እና የሚወዳደረው እንጂ ለተሳትፎ ብቻ ብቅ ብሎ በወያኔ ሻጥር የሚሸነፍበት ሊሆን አይገባም።
ለውጥ የግድ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ሁሉንም የማይጠቅም ቢሆን እንኳን ለብዙኃኑ ሲባል የግድ መምጣት አለበት፡፡ የለውጥ ፍርሐትን አስወግደን በቂ ዝግጅት በማድረግ በተገቢው መንገድ ወያኔን ማስወገድ  ይቻላል፡፡ ለውጥ የሚመጠበትን መንገድ ፈርቶ እና ህዝባዊ አምፅን  ተቃውሞ  ለውጥን መጨበጥ ዘበት ነው፡፡ ‹‹መፍራት ያለብን ፍርሐትን ራሱን ነው›› እንዲሉ ፍራንክሊን ሩዝቬልት፡ የትኛውንም ወደኋላ የሚጎትተንን ፍርሀት ትተን ድጋሚ በምርጫው ከመጭበርበራችን በፊት አስቀድመን በህዝባዊ አመጽ መታገንልን እንምረጥ። ከምርጫው በፊት የኢትዮጵያውያን ምርጫ  በህዝባዊ አመጽ ትግል ለዘመናት በአንባገነንነት በስልጣን ላይ ተቀምጦ ህዝብን በማሰር ፣ በመግደል ላይ ያለውን አረመናዊ መንግስት ከስልጣን ላይ ማውረድ ይሆን ነው  መልዕክቴ ።
gezapower@gmail.com

የሕዝብ ትግል ያቸንፋል !!!

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on March 22, 2015
  • By:
  • Last Modified: March 22, 2015 @ 12:14 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar