www.maledatimes.com ከአምስት በላይ የሰማያዊ ፓርቲ አባሎች እና የሸዋሮቢት ነዋሪዎች በእስር ላይ መሆናቸው ተገለጸ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ከአምስት በላይ የሰማያዊ ፓርቲ አባሎች እና የሸዋሮቢት ነዋሪዎች በእስር ላይ መሆናቸው ተገለጸ

By   /   July 29, 2015  /   Comments Off on ከአምስት በላይ የሰማያዊ ፓርቲ አባሎች እና የሸዋሮቢት ነዋሪዎች በእስር ላይ መሆናቸው ተገለጸ

    Print       Email
0 0
Read Time:59 Second

በሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ ሸዋሮቢት ከተማ የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አባሎች እና ወጣት የለውጥ አራማጅ የፓርቲው አቀንቃኞች በመንግስት ሃይል ታፍነው ወደ እስር ቤት ከተወረወሩ ከወር በላይ መሆናቸውን ከክልል ሶስት ሰሜን ሸዋ ዞን የሸዋሮቢት ከተማ አስተደር ነዋሪዎች የሆኑ እና የፓርቲው አባሎች እና አመራሮች ለማለዳ ታይምስ የአባሎቻቸውን መታሰር ጠቁመዋል ።

እነዚህ የሰማያዊ ፓርቲ አባሎች በየትኛው ቦታ እና እንዴት እንደታሰሩ ለመጠየቅ ቢሄዱም የመንግስት ሃይሎች ምንም አይነት መረጃም ሊሰጧቸው እና ያሉበትንም ሁኔታዎች ሊያሳውቋቸው ባለመቻላቸው በከፍተኛ በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዲስ አበባ የሚገኘውን የሰማያዊ ፓርቲ ዋና መስሪያ ቤት ለማግኘት እና ስለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው መግለጫ እንዲያወጡ ለመጠየቅ በደጋግሚ ቢጥሩም ምንም ምላሽ ሊሰጧቸው አለመቻሉ እራሱ አሳሳቢ ከመሆኑም በልይ በክልሉ ለሚገኙት አባሎች እራስ ምታት መሆኑን ገልጸዋል ።

የፓርቲው አመራር ምላሽ መስጠት ሲገባቸው እንደ ወያኔ መንግስት ለአባሎቻቸው ዝምታን መፍጠሩ ለለውጥ የተዘጋጁ ሳይሆኑ ለጥቅሞቻቸው የተነሱ ሃይሎች መስለው ነው የታዩን ብለው የተናገሩት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁት እና የቀወት ወረዳ የሰማያዊ ፓርቲ የወጣት መልማዮች ዋና ሃላፊ በዛሬው እለት ይህንን መግለጭ ወደ ግል መገናኛ ብዙሃን ልናመጣው የቻልነው ሰሚ አካል ብናገኝ ጥሩ ነው በሚል ምክንያት ነው ሲሉም አክለው ገልጸዋል ። ከአንድ ወር በፊት የታሰረውን ወጣት ቴዎድሮስ ሃብቴ እስካሁን ያለበትንም ሁኔ ካለማወቃችን የተነሳም ለፍርድ እንኳን አቅርበው ጥፋተኝነቱንም ህነ የተከሰሰበትን ሁኔታ ለመረዳት አልቻልንም የሌሎችንም ወጣት የዘርፍ ክፍሎቹንም ለመከታተል አልቻልንም ሲሎ ገልጸዋል ።ማለዳ ታይምስ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on July 29, 2015
  • By:
  • Last Modified: July 29, 2015 @ 10:43 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar