www.maledatimes.com ከአርባ ምንጭ ወደ ጅቡቲ የ1ሺ 231 ኪሎ ሜትር የተፈጥሮ ጋዝ ማስተላለፊያ ቱቦ ዝርጋታ ሊጀመር ነው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ከአርባ ምንጭ ወደ ጅቡቲ የ1ሺ 231 ኪሎ ሜትር የተፈጥሮ ጋዝ ማስተላለፊያ ቱቦ ዝርጋታ ሊጀመር ነው

By   /   September 22, 2015  /   Comments Off on ከአርባ ምንጭ ወደ ጅቡቲ የ1ሺ 231 ኪሎ ሜትር የተፈጥሮ ጋዝ ማስተላለፊያ ቱቦ ዝርጋታ ሊጀመር ነው

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 39 Second
  • የተገኘው የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ከሩሲያ ይበልጣል
  • ጁቡቲ በ2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ማከማቻና ማጣሪያ ተርሚናሎች

እየገነባች ነው

 

ከአርባምንጭ ወደ ጅቡቲ የ1ሺ 231 ኪሎ ሜትር የተፈጥሮ ጋዝ ማስተላለፊያ የቱቦ ዝርጋታ ሊጀመር መሆኑ የሰንደቅ ምንጮች ገለፁ።

የሚዘረጋው የተፈጥሮ ጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧ ከአርባምንጭ ተነስቶ በአዋሳ በድሬዳዋ አድርጎ በመጨረሻም ጁቡቲ ወደብ እንደሚደርስ ታውቋል። ይህን ስራ ለማስጀመር የሚስችል ፈንድ መገኘቱን እንዲሁም በኢትዮጵያ መንግስትና በጅቡቲ መካከል የስምምነት ውል መፈረሙም ታውቋል።

በአርባምንጭ የተገኘው የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት በዓለም ከፍተኛ ክምችት ካላት ሩሲያ የሚበልጥ መሆኑ ተገልጿል። ሩሲያ 47 ትሪሊየን 700 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት አላት።

በአርባ ምንጭ የተገኘው የጋዝ ክምችት አዋጭነቱ ከካቡል የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ጋር ፈጽሞ የማይገናኝና ለአበዳሪ ሀገራትም ከፍተኛ የሆነ መተማመን የፈጠረ በመሆኑ ለቱቦው ዝርጋታ ፈንድ እንዲለቀቅ አስችሏል። ኢትዮጵያም በዓለም ደረጃ ቁጥር አንድ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ባለቤት የሚያደርጋት ከመሆኑም በላይ በቀጣይ በኢኮኖሚዋ ላይ አይነተኛ ድርሻ ይኖረዋል ተብሏል።

ከካቡል ወደ ጅቡቲ ወደብ 805 ኪሎ ሜትር ርቀት ያለውን ጋዝ የማስተላለፊያ ቱቦ ለመዘርጋት አሜሪካ ቺካጎ ተቀማጭ የሆነው ብላክሪኖ የተባለው ኩባንያ ከስምምነት ላይ ደርሶ እንደነበር ተነግሯል። ኩባንያው በራሱ ሙሉ ወጪ በ481 ሚሊዮን ዶላር ዝርጋታውን ለማከናወን ተስማምቶ የነበረ ቢሆንም በጥቅም ድርሻ ላይ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር አለመስማማቱ ተገልጿል። ኩባንያው ሰባ በመቶ የጥቅም ድርሻ ለመውሰድ ጥያቄ ቢያቀርብም በመንግስት በኩል ጥያቄ ውድቅ ተደርጎበታል። ስምምነት ላይ ለመድረስ ተደጋጋሚ ሙከራ ቢደርግም ከስምምነት መድረስ አልተቻለም ተብሏል።

የጁቡቲ መንግስት በበኩሉ የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ጋዝ ለማከማቸት፣ ለማጣራት እና ለዓለም ገበያ ለማቅረብ በ2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዳላር አዳዲስ ተርሚናሎች እየገነባ ነው። ጅቡቲ በዓመት ቢያንስ 10 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የተፈጥሮ ጋዝ ከኢትዮጵያ ወደ ቻይና ለመላክ እየተሰናዳች መሆኑም ተጠቁሟል።

እ.ኤ.አ. በ2013 በእንግሊዝ እና በጅቡቲ የንግድና ኢንቨስትመንት 8ኛ ፎረም ላይ የጅቡቲ ወደብ እና የነፃ ዞን ባለስልጣን ሚኒስትር አቡበከር ኡመር ሃዲ ባቀረቡት ሪፖርት የተርሚናል ማስፋፊያው ፕሮጀክት 2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር እንደሚፈጅ ማስታወቃቸው ይታወሳል።

ለጋዝ ማስተላለፊያ ቱቦው ፈንድ የፈቀዱ ሀገራት በግልጽ ባይታወቁም ከብሪክስ ሀገራት መካከል እንደሚሆኑ ይገመታል። የቱቦ ማስተላለፊያው ዝርጋታ እ.ኤ.አ. በ2016 ሙሉ ለሙሉ ይጠናቃቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የአርባምንጩን የተፈጥሮ ጋዝ እያለማ የሚገኘው አፍሪካ ኦይል ኮርፖሬሽን የተባለ የካናዳ ኩባንያ ነው። ኩባንያው በነዳጅና በተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋና ማምረት ላይ የተሰማራ ሲሆን፤ በአሁኑ ሰዓት ኩባንያው በኬኒያ፣ በኢትዮጵያ እና በፑንትላንድ ሥራዎቹን እያከናወነ ይገኛል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on September 22, 2015
  • By:
  • Last Modified: September 22, 2015 @ 6:15 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar