www.maledatimes.com ዛሬ፣ በእነሀብታሙ አያሌው ጉዳይ ማረሚያ ቤት ላይ ክስ ቀረበ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ዛሬ፣ በእነሀብታሙ አያሌው ጉዳይ ማረሚያ ቤት ላይ ክስ ቀረበ

By   /   August 25, 2015  /   Comments Off on ዛሬ፣ በእነሀብታሙ አያሌው ጉዳይ ማረሚያ ቤት ላይ ክስ ቀረበ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 7 Second


ሰኔ 01 ቀን 2006 ዓ.ም በሽብርተኝነት ወንጀል ከተጠረጠሩ በኋላ፤ በእነዘላለም ወርቅአገኘሁ የክስ መዝገብ፣ ከአንድ ዓመት በላይ ጉዳያቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ሲታይ ቆይቶ ባለፈው ሳምንት ነሐሴ 14 ቀን 2007 ዓ.ም በነጻ እንዲሰናበቱ በችሎቱ ትዕዛዝ ከተሰጣቸው አምስት ግለሰቦች መካከል 2ኛ ተከሳሽ ሀብታሙ አያሌው እና 7ኛ ተከሳሽ አብርሃም ሠለሞን እስከአሁን ድረስ ከቂሊንጦ እስር ቤት መፈታት ባለመቻላቸው የተነሳ፣ በዛሬው ዕለት ማረሚያ ቤቱ ላይ ክስ መቅረቡ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የቀረበው ክስ እንደሚያስረዳው ከሆነ፣ ከላይ በተጠቀሰው ቀን፤ ፍርድ ቤቱ፣ በክሱ ከተራ ቁጥር 2-5 እና 7ኛ ተከሳሽ ክሱን መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ እንዲሰናበቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት የመፍቻ ትዕዛዙን በ15/12/2007 ዓ.ም ለማረሚያ ቤቱ ቢደርስም ተከሳሾቹ እስከአሁን ድረስ ከእስር ሊለቀቁ አለመቻላቸውን ይጠቅሳል፡፡
በመሆኑም ‹‹ፍርድ ቤቱ ይህንን ባደረጉ የማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች ላይ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ባለማክበራቸው ሕጋዊ እርምጃ ከመውሰድ ጋር ተከሳሾቹን እንዲለቅ ጥብቅ ትዕዛዝ እንዲሰጥልኝ በማክበር አመለክታለሁ›› ሲሉ ለ2ኛ ተከሳሽ ሀብታሙ አያሌው ባለቤቱ ወ/ሮ ቤተልሄም አዛናው እና ለ7ኛ ተከሳሽ አብርሃም ሠለሞን ወላጅ እናቱ ወ/ሮ መሠረት ገ/ጊዮርጊስ በዛሬው ዕለት ትዕዛዙን ለሰጠው ችሎት ክሳቸውን ማቅረባቸው ታውቋል፡፡
ፍርድ ቤቱ በነጻ ካሰናበታቸው ተከሳሾች መካከል አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋና ዳንኤል ሺበሺ ችሎት በመድፈር ወንጀል ሁለት ጊዜ ያህል መቀጣታቸው የሚታወስ ሲሆን ባለፈው ሳምንት ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ውሳኔ ተከትሎ አቃቤ ሕግ በአምስቱም ተከሳሾች ላይ ይግባኝ ጠይቆ ከእስር እንዳይፈቱ ዕግድ አቅርቦ ነበር፡፡ እንዲሁም የተቀሩት አምስት ተከሳሾች እንዲከላከሉ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ መስጠቱ ይታወቃል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on August 25, 2015
  • By:
  • Last Modified: August 25, 2015 @ 11:58 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar