www.maledatimes.com የህወሃት ስብሰባ ተጠናቀቀ የአባላቶች ምርጫም ጥቅቅሞሽ ነበር ሲሉ አንዳንዶች ተናግረዋል ። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የህወሃት ስብሰባ ተጠናቀቀ የአባላቶች ምርጫም ጥቅቅሞሽ ነበር ሲሉ አንዳንዶች ተናግረዋል ።

By   /   March 21, 2013  /   Comments Off on የህወሃት ስብሰባ ተጠናቀቀ የአባላቶች ምርጫም ጥቅቅሞሽ ነበር ሲሉ አንዳንዶች ተናግረዋል ።

    Print       Email
0 0
Read Time:12 Minute, 45 Second

ሰሞኑን መቀሌ ፣ ባህር ዳር ፣ ሃዋሳ እና አዳማ ከተሞች ላይ ጉባኤያቸውን ሲያካሂዱ የሰነበቱት የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ሊቀ መንበሮቻቸውን በመምረጥ ጉባኤያቸውን አጠናቀቁ ይህ ምርጫም የተጠበቁት ሰዎች ሳይሆን የተመረጡት የራሳቸውን አካላት እና የሚፈልጓቸውን ሰዎች በመጠቃቀም ነው ሲሉ አንዳንድ የወያኔ አባሎች በስብሰባው ላይ የተሳተፉት በአማራም ደቡብ እና ትግራይ ክልል ስብሰባውን ያዩ ቅሬታቸውን መግለጻእውን የማለዳ ታይምስ ዘጋቢ ጠቁሞአል።

የህወሃት አመራር አካላቶች ባካሂያዱበት መቀሌ ላይ ጉባኤውን ሲያካሂድ የሰነበተው ህወሃት አቶ አባይ ወልዱን ሊቀ መንበር እንዲሁም ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤልን ምክትል ሊቀ መንበር አድርጎ መርጧል ለዚህም የምርጫው ሚዛናዊነት ምን እንደሆነ እንኳን የተገለጸበት ደረጃ የለዉም በእጅ ብልጫ ብቻ እንዲካሄድ በተወሰነው መልኩ መከናወኑ አሳፋሪ ነው ሲሉ አያይዘው ጠቁመዋል።

ለዓመታት ፓርቲውን በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት  ያገለገሉት እና ፈላጭ ቆራጭ በመሆን አገሪቱ ላይ ከፍተኛ በደል ፈጽመዋል ተብለው ጥርስ የተነከሰባቸው ፣በተለይም ከኢትዮ ኤርትራ ጦርነት በኋላ የባድመ ድንበር ተመልሶአል በማለት በአደባባይ የተናገሩት እና የኢትዮጵያን ህዝብ ዋሽተዋል በሚል ከኢትዮጵያ ህዝብ ጥላቻን ያተረፉት  አምባሳደር ስዩም መስፍን የተባረሩ ሲሆን ሌሎችም ተከትለዋቸው ከስልጣን ቦታቸው መባረራቸውን ከስፍራው የነበረው ባልደረባችን ዘግቦአል እነ ፣ አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ ፣ አቶ አርከበ ዕቁባይና አቶ ዘርዓይ አስገዶምን ጨምሮ ፥ ዘጠኝ አባላት እንዲገለሉ የተደረገ ሲሆን የወያኔ መንግስት ግን  ባቀረቡት ጥያቄና ፓርቲው እየተገበረ ባለው የመተካካት ሂደት መሰረት ፤ በአዲስ አባላት እንዲተኩ የተወሰነ ሲሆን አንጋፋ አባላቱ በክብር ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ተሰናብተዋል ሲል መናገሩን ቀጥሎአል ።

ዘጠኙ ነባር አባላት በኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ  በድምፅ ተወክለው እንዲሳተፉም የተወሰነ ሲሆን እዚያው ላይ አልሸሹም ዞር አሉ ነው ሲሉም አንዳንዶች ይገልጻሉ  ።

በሌላም በኩል በኢሃዴግ ህወሃት በጉባኤው 45 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ምርጫን ጨምሮ ፥ አቶ አባይ ወልዱ ፣ ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ፣ አቶ በየነ ምክሩ ፣ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ፣ ወይዘሮ አዜብ መስፍን ፣ አቶ ቴዎድሮስ ሃጎስ ፣ አቶ ገብረመስቀል ታረቀኝ ፣ አቶ አለም ገብረዋህድ እና ወይዘሮ ትርፉ ኪዳነማርያም የኢህአዴግ እና የህወሃት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው ተመርጠዋል።

ይህ በ እንዲህ እንዳለ የወያኔ ጅራት እየተባለ የሚጠራው የአማራክልል ላይ ስብሰባውን በባህርዳር ላይ ጉባኤውን ያካሄደው ብአዴን አቶ ደመቀ መኮንን ሊቀ መንበር እንዲሁም አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ምክትል ሊቀ መንበር አድርጎ መርጧል።

አቶ ደመቀ መኮንን ፣ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ፣ የኤርትራውን ተወላጅ እና የዘር ግንዱን ከተለያዩ ቦታዎች እየጨፈለቀ አማራ ነኝ ብሎ የሚናገረው እና በትክክል የዘር ግንዱን ደፍሮ የማይናገረው አቶ በረከት ስምኦን በዚሁ ስብሰባ ላይ የስራ አስፈጻሚነቱን ቦታ ከሌሎቹ ጋር ተጋርቶ ይገኛል ፣ አቶ አለምነው መኮንን ፣ አቶ አዲሱ ለገሰ ፣ አቶ አያሌው ጎበዜ ፣ አቶ ተፈራ ደርበው ፣ አቶ ብናልፍ አንዷለም ፣ አቶ አህመድ አብተው ፣ አቶ ካሳ ተክለብርሃን ፣ አቶ መላኩ ፈንታ ፣ ዶክተር አምባቸው መኮንን እና አቶ ጌታቸው ጀምበር የንቅናቄው ስራ አስፈጻሚ አባል ሆነው ተመርጠዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ድርጅቱን ወክለው በ9ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ አባላትንና 65 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ምርጫንም አካሂዷል።

በተመሳሳይ ሃዋሳ ላይ  ጉባኤውን ሲያካሂድ የሰነበተው ደኢህዴን አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን ሊቀ መንበር አቶ ሽፈራው ሽጉጤን ደግሞ ምክትል ሊቀ መንበር አድርጎ መርጧል።

በደቡብ ኢትዮጵያ የተካሄደው ጉባኤ መለስ ደንግጦ ሲሞት በቁሙ የሞተ እየተባለ በኢትዮጵያ ህዝብ የሚወረፈው  አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝን ባለበት እና ተመራጭ በሆነበት በዚህ መድረክ ላይ ፣ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ፣ አቶ ሬድዋን ሁሴን ፣ አቶ መኩሪያ ሀይሌ ፣ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ፣ ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም ፣ አቶ ዓለማየሁ አሰፋ ፣ አቶ ደሴ ዳልኬና አቶ ተስፋዬ በልጂጌ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሆነው ተመርጠዋል ። ከግል የጥቅም አኳያ ጥቅም አስፈጻሚ የሚሏቸውን አባሎቻቸውን የኢሃዴግ አስፈጻሚ በማለት መምረጣቸውን ተጠቁሞአል ።ዘጠኙን የኢህአዴግ  ስራ አስፈፃሚ  አባላትን ጨምሮ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ  ፣ አቶ መለሰ ዓለሙ ፣ ወይዘሮ ሙፍሪያት ካሚል ፣ አቶ ታገሰ ጫፎ ፣ አቶ ደበበ አበራና አቶ ሳኒ ረዲን ደግሞ ለደኢህዴን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት በመምረጥ ጉባኤውን ያጠናቀቀ ሲሆን  የተሰብሳቢዎቹን ውሎ አበል ለመክፈል አልደፈረም ሲሉ ወቀሳቸውን አቅርበዋል።

በሌላ በኩል በተያያዘ ዜና አዳማ ላይ መደበኛ  ጉባኤውን ሲያካሂድ የሰነበተው የኦሮሞ  ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት / ኦህዴድ/ ፥ አቶ ዓለማየሁ አቶምሳን  የድርጅቱ ሊቀ መንበር አቶ ሙክታር ከድርን ደግሞ ምክትል  ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል ። በዝምታው ይልፈ እየተባለ የሚጠራው የኦህዴድ ድርጅት ለማጨብጨብ ሳይሆን ምንም ስራ ሊሰራ ያልተፈቀደለት አጋር ድርጅት ቁጥር ማደራጀት ብቻ የበቃ ነው እየተባል በሰፊው ይነገርለታል ይህ ድርጅት ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ሰዎችን ከአመራር ደረጃ ላይ ከመለዋወጥ በስተቀር ለኦሮሞው ህዝብ ምንም ነገር የፈጠረ እና የሰራ አይደለም በማለት ኦሮሞዎች ከፍተኛ ጥላቻን ያተረፈ ድርጅት ነው ።

የድርጅቱ ሊቀመንበርና  ምክትል ሊቀመንበርን ጨምሮም ፥ ወይዘሮ አስቴር ማሞ ፣ አቶ ወርቅነህ ገበየሁ ፣ የሃረሪውን ተወላጅ አቶ ሱፍያን አህመድ ፣ አቶ ድሪባ ኩማ ፣ አቶ አብዱልቃድር ሁሴን ፣ አቶ ኡመር ሁሴንና አቶ አበራ ሀይሉ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ  ምክር ቤት አባላት ሆነው ተመርጠዋል ።በተያያዘ ዜና እነዚህ ስራ አስፈፃሚዎች በሚካተቱበት የኦህዴድ ስራ አስፈፃሚ  ኮሚቴ አባልነት አቶ ዋቅ ቤካ ፣ አቶ አብዱልአዚዝ መሀመድ ፣ አቶ ኑሬ ቀመር ፣ አቶ ሰለሞን ቁጩ ፣ አቶ በከር ሻሌና አቶ እሸቱ ደሴ ተመርጠዋል የዚህን አመት የስበሰባ አጠናቀው ተሰነባብተዋል ። የዜናው ልዩ ጥንቅር ይህንን ይመስል ነበር ።

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on March 21, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 21, 2013 @ 4:44 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar