www.maledatimes.com የማለዳ ወግ …” ሳውዲና ኢትዮጵያ የሰራተኛ ውል አልተፈራረሙም!” - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የማለዳ ወግ …” ሳውዲና ኢትዮጵያ የሰራተኛ ውል አልተፈራረሙም!”

By   /   September 18, 2015  /   Comments Off on የማለዳ ወግ …” ሳውዲና ኢትዮጵያ የሰራተኛ ውል አልተፈራረሙም!”

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 24 Second

==================================
* ” የሳውዲና የኢትዮጵያ የሰራተኛ ውል ተፈረመ! “ወገን ለወገን – በሳውዲ ” ፊስ ቡክ ገጽ
* ትክክለኛ መረጃ ህይዎት ነው ፣ የተሳሳተ መረጃ ጎጅ ነው!
*  የተሳሳተ መረጃ እንዳይጎዳን የመንግስት ተወካዮች ለመረጃ በራቸውን ይክፈቱ !
* በአዲሱ ኮንትራት ዙሪያ ባለድርሻው ስደተኛ ይምከርበት

ከቀናት በፊት የሳውዲ ታዋቂ ጋዜጣ አረብ ኒውስ #arabnews  ያወጣውን መረጃ ተከትሎ በርካታ ኢትዮጵያውያን  በቀረበው መረጃ ዙሪያ ግራ የተጋቡ መረጃዎች ግራ እንዳጋባቸው በተለያዩ መንገዶች ገልጸውልኛል ።  ይህንኑ   በአረብ ኒውስ የቀረበውን መረጃ ተከትሎ  የሳውዲ ሰራተኛ ቀጣሪዎች ከኢትዮጵያ ሰራተኛ ማስመጣት እንደሚችሉ መመሪያ መሰጠቱንና የሁለት ዓመት እግዱ መነሳቱን በማለዳ ወጌ መረጃ ማቅረቤ አይዘነጋም ። የአረብ ኒውስ #arabnews መረጃ እንደተለቀቀ በበርካታ ማህበራዊ ገጾች ውሉ ስለመፈረሙ ተጨማሪ ዝርዝርና የተሳሳቱ መረጃዎችን በመሰላቸው መንገድ ሲያሰረጩ ተስተውሏል !  አንዳንዶችማ የተለያዩ ያልተጨጡ ትንታኔዎችን በመጨመር ” ሳውዲና ኢትዮጵያ የሰራተኛ ውሉን ተፈራረሙ ! ” በሚል መረጃ በማቅረብ ወደ ሳውዲ ለመምጣት የቋመጡትን ወገኖች ነፍስ አማልለዋል  ።

እንደኔው ሳውዲ ላለን ስደተኞች መረጃ በማቀበሉ ረገድ እየተጋ ያለ አንድ የመረጃ አቅራቢም የተሳሳተ መረጃ ማቅረቡን ታዝቤያለሁ ።   የአንድ ወገን የፖለቲካ ፓርቲ ዘመም መረጃ ቅበላውን አሻሽሎ አሁን አሁን ወደ ህዝባዊና ሚዛናዊ የመረጃ ቅበላ ደረጃውን ከፍ እያደረገ በመጣው  የ“ወገን ለወገን – በሳውዲ ” ፊስ ቡክ ገጽ ” የሳውዲና የኢትዮጵያ የሰራተኛ ውል ተፈረመ! “ በሚል መረጃ ማቅረቡ ይጠቀሳል።  የ“ወገን ለወገን – በሳውዲ ”  መረጃ ጉዳዩን ሲያብራራ እንዲህ ይላል ” በመስከረም ወር ይፈረማል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረውን የኢትዮጵያና የሳውዲ አዲሱ የኮንትራት ሰራተኞች ውል ተፈረመ። የሳውዲ ሰራተኛ ጉዳይ ሚኒስትር ከሶስት ሀገሮች ጋር ተፈራረምኩ አለ። ከነዚህ ሶስት ሀገሮች በግልፅ ይፋ የተደረገው የኢትዮጵያ ስም ብቻ ቢሆንም ከኢትዮጵያ ሌላ ከሁለት ሀገሮች መፈራረሙን ግን ይፋ አድርጓል። “ ሲል አረብ ኒውስን በመረጃ ምንጭነት ጠቁሟል ።  ከላይ የጠቀስኩት በማለዳ ወግ ያቀረብኩት መረጃና የ“ወገን ለወገን – በሳውዲ ” “ውሉ ተፈረመ !” የሚለው መረጃ ምንጭ የሳውዲ ታዋቂ ጋዜጣ አረብ ኒውስ ሆኖ እያለ የተለያየ መረጃ መቅረቡ ነዋሪውን ግራ አጋብቶ ሰንብቷል!

በርካቶች ይህን መረጃ ተከትሎ ከሀገር ቤት ሳይቀር ወደ ሳውዲ መምጣት ለሚፈልጉ ኤጀንሲዎች ምዝገባ መጀመራቸውን ተሰምቷል ። በስምምነቱ ዙሪያ የተፈረመ ውል ይኖር እንደሁ በሳውዲ የመንግስ ት ኃላፊዎች በኩል ያደረግኩት ማጣራት የሁለቱ ሀገራት የስምምነት ውል አለመፈረሙን ማረጋገጥ ችያለሁ።  በ” ወገን ለወገን – በሳውዲ “ ምንጭነት የተጠቀሰው  አረብ ኒውስ  ስለ ውሉ መፈረም የጠቀሰው ምንም መረጃ የለም።  የአረብ ኒውስን ዘገባ የሚያትተው በማለዳ ወግ የመረጃ ግብአት እንደ ጠቆምኩት የሳውዲ ሰራተኛ ቀጣሪዎች ከኢትዮጵያ ሰራተኛ ማስመጣት እንደሚችሉና የሁለት ዓመት እግዱ መነሳቱን ከመጥቀስ  ባለፈ የሳውዲና የኢትዮጵያ የሰራተኛ ውል ተፈረመ የሚል መረጃ አላቀረበም !

የአረብ ኒውስን ዜና የተሳሳተ ትርጉም እየተሰጠው ሲሰራጭ መረጃውን እውነት ያስመሰለው በአዲሱ አመት 2008 ዓም ከመግባቱ አስቀድሞ በሳውዲ የኢትዮጵያ ኢንባሲ አንድ ሃላፊ ”  የኢትዮጵያ መንግስት በአዲሱ ዓመት ከሳውዲ መንግስት ጋር የሰራተኛ ውሉን ይፈራረማል! ” በሚል የሰጡት መግለጫ መሆኑ ይጠቀሳል ። በአዲሱ አመት የሰራተኛ ስምምነት ውሉ ይደረጋል የሚለው በሪያድ የኢትዮጵያ ኢንባሲ ያያኔ መግለጫ በፋናና በተለያዩ የኢትዮጵያ መንግስት ዜና ምንጮች ቀርቦ ነበር ።

ይህ በእንዲህ  እንዳለ በአረብ ኒውስ መረጃው ኢትዮ ጵያ ተጠቅሳ ስለሰራተኞች ማስመጣት መረጃ ከተሰረጨ ወዲህ በተለያዩ ማህበራዊ መገናኛ ገጾች ” የሰራተኛ ውል ተፈርሟል ” የሚል መረጃ መተላለፉን በሪያድ የእትዮጽያ ኢንባሲ ”  ሀሰት ነው !”  ብሎታል ። መረጃው መሰረተ ቢስ  መሆኑን የጠቀሰው ኢንባሲው ባወጣው ማስታዎቂያ ስምምነቱ በሁለቱም መንግስታት ህግ አውጭዎች ከጸደቀ በኋላ በድርድር የሚፈጸም መሆኑን ጠቁሟል !

ትክክለኛ መረጃ ህይዎት ነው ፣ የተሳሳተ መረጃ ጎጅ ነው ! የተሳሳተ መረጃ እንዳይጎዳን የመንግስት ተወካዮች ለመረጃ በራቸውን ይክፈቱ ፣ በስምምነቱ ዙሪያም ሆነ በተለያዩ ወቅታዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መረጃ ያቀብሉ ! በአዲሱ ኮንትራት ዙሪያ ባለድርሻው ስደተኛ ይምከርበት !

ቸር ያሰማን  !

ነቢዩ ሲራክ
መስከረም 6 ቀን 2008 ዓም

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on September 18, 2015
  • By:
  • Last Modified: September 18, 2015 @ 11:03 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar