www.maledatimes.com የአትሌት ቀነኒሳ በቀለ ሆቴል የሺሻ ማጨሻ ሆነ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የአትሌት ቀነኒሳ በቀለ ሆቴል የሺሻ ማጨሻ ሆነ

By   /   May 1, 2015  /   Comments Off on የአትሌት ቀነኒሳ በቀለ ሆቴል የሺሻ ማጨሻ ሆነ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 9 Second

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ያስገነባው እና ዘመናዊ ተብሎ የሚጠራቅ ቀነኒሳ ሆቴል በሺሻ ማጨስ የተለከፉ ወጣቶች መጠራቀሚያ እና ጥራቱን ያልጠበቀ ስራ በመስራት የሚታወቅ ሆቴል ሆⶈል ። በአዲስ አበባ ከተማ ወጣት ሴቶች ከተለያዩ ጓደኞቻቸው ጋር የሚቀጣጠሩበት ዋነኛ መድረክ የሆነው ሺሻ ወይንም ሁካ ማጨሻ ስፍራዎች ሲሆኑ ፣በአሁን ሰአት ግን ይህ ሆቴል የሆቴሎች አስተዳደር ድርጅት እና የአዲስ አበባ ስራ እና ከተማ ልማት ቢሮ የሰጠውን፡ሕጝ፡ጥሶ የሺሻ ማጨሻ ሱቅ ማድረጉ በጣም አሳፋሪ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገልጸዋል ።

ቀነኒሳ በቀለ ሆቴሉን ካሰራ በሁዋላ የፊት ለፊት ገጹን የስሙን ጽሁፍ በቻይንኛ ማሰራቱ በሃገሩ ቋንቋ እና በማንነቱ የማይኮራ ነው ሲባል የተወቀሰ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ፣በሌላም በኩል ከፍተኛውን ስራ የሰሩት ቻይናዎች ሲሆኖ ጫና አሳድረውበት ነው ሲሉ ገልጸዋል ;በሌላም በኩል በአማካሪው ግፊት ነው የቻይንኛ ቋንቋ የመሰለ ፊደል ሊጠቀም የቻለው ሲሉም

በተለይም እንደ አትሌት ቀነኒሳ አይነት የስፖርት ቤተሰብ የሆነ ሰው እና በህዝብ ዘንድ በስራው ገናናነትን ያተረፈው ድንቅ አትሌት ወጣቶችን ከእንደዚህ አይነት ድርጊት እንዲቆጠቡ መምከር ሲገባው በእራሱ ባሰራው ህንጻ ላይ ታዳጊ ወጣቶች እንዲበላሹ መጋበዙ አሳፋሪ እና ከእሱ ስራ እና ክብር የማይጠበቅ ነው ሲሉ ወርፈውታል ።

በሌላም በኩል ሆቴሉ የሚያቀርባቸው አግልግሎቶች ውስጥ ማናቸውም ከሁካ ወይንም ሺሻ ጋር የሚቀርቡ መጠጦችም፡ምግቦች ዋጋቸው የናረ ከመሆኑም በላይ መንግስት ያለቀረጥ የሚነግዱትን እንደሚያስር እና እንደሚቀጣ ሁሉ የአትሌት ቀነኒሳ ስራ ከማናቸውም ሆቴሎች ደረጃ በላይ ውድ መሆናቸው በላይም የመንግስት አስተዳደር ዝምታውን መምረጡ ተገቢ አይደለም ሲሉ አክለው ገልጸዋል ።

ሆኖም ግን በዚህ የሺሻ መሸጫ መደብር የሆነው የቀነኒሳ ሆቴል ውስጥ፡ባለ፡ስልጣናት እና የባለስልጣናት ልጆች ጊዜ ማሳለፊያቸው እና መዋያቸውንም መሆኑን ዘጋቢያችን ወይዘሪት ኢትዮጵያ ከስፍራው ገልጻለች ። ማለዳ ታይምስ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on May 1, 2015
  • By:
  • Last Modified: November 3, 2016 @ 9:09 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar