www.maledatimes.com የኢሳያስ አፈወርቂ ድመቶች ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የኢሳያስ አፈወርቂ ድመቶች !

By   /   March 5, 2015  /   Comments Off on የኢሳያስ አፈወርቂ ድመቶች !

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 54 Second
1
የኢሳያስ አፈወርቂ ድመቶች !
ነብርና የጥቢ ፍየል
ከአንበሳው ይብራ ፡
ቀጥሎ የምነግራችሁ ታሪክ ፤ እኔ የዚህ ፅሁፍ አቅራቢ በኤርትራ በቆየ
ሁበት ወራት
የተፈፀመ ነው ። ጊዜው 2010 ፈብሯሪ ወር ነው ። የአልጀዚራዋ ጋዜጠኛ ጄን ዳቶ
ን አስመራ
ከገባች ገና ሶስት ቀኗ ነው ። እነዛን ሶስት ቀናት ፡ ጋዜጠኛዋን ለማግባባት ብዙ
ስራ ተሰርቷል ።
እሷን ለማማለልና ወዳጃዊ የሆነ ጥያቄ ለፕሬዚደንቱ እንድታቀርብ ፤ ተገቢውን ስራ
እንዲሰራ
በጊዜው የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አሁን ግን ስደተኛው አቶ አሊ አብዶ ተመድቧ
ል ። አቶ
አሊ አብዶ ከኤርትራ ባለሰልጣናት ውስጥ ወጣትና ዘመናዊ አስተሳሰብ ያለው ነው ተብ
የሚገመት ሰው ነበር ። ከወጣት ማህበራቱ የፖለቲካ እርከን ወደ ሚኒስትርነት ደረጃ
የወጣ ሰው
ነው ። ወጣትነቱ ፤ ቁመናውንና መልኩም የሰጠ በመሆኑና በማራኪ ፈገግታው ጄን ዳቶ
ንን
ያማልላታል ተብሎም ተገምቶ ነበር ።
ሻእቢያ በሽፍትነቱ ዘመን ከእርዳታ አቅራቢ ድርጅት ሰራተኞች እስከ ኒ
ው ዮርክ ታይምስ
ጋዜጠኞች ድረስ ሴት ሴቶቹን በማማለል የሚፈልገውን ግብ ሲመታባቸው ቆይቷል ። ለም
ሳሌ
ያህል ፤ ከእነዚህ ውስጥ አንዷ ፤ የአውስትራሊያ እርዳታ ድርጅት ነርስ የነበረችው
ነች ። ይህች
ነርስ እ.አ. አ በ1973 ዓ . ም ለድርቅ እርዳታ ወደ ኢትዮጵያ ገብታ የነበረ
ችና ከፖርት ሱዳን
በሻእቢያ ተወካይ አማላይነት ተመልምላ በአውሮፓና በአሜሪካ ጋዜጦች አስተያየቷን
ደጋግማ
እንድትፅፍ ተደርጋ ነበር ። ጊዜው የደርግ ዘመን ስለነበር በፀረ ደርግ ፅሁፏና በ
አንፃሩ የሻእቢያን
ተጋድሎ እያጎላች በመፃፍ ለአንዳንድ የምዕራብ ጋዜጦች የአፍሪቃ ቀንድ ሪፖርተር እ
ስከመሆን
ደርሳ ነበር ፤ ከሻእቢያ ጋር እስክትቆራረጥ ድረስ ። በመጨረሻም አንዴ ራሱ ኢሳያ
ስ አፈወርቂ
በግል አንድ ጉዳይ እንድትፈፅም ፖርት ሱዳን ውስጥ ሆኖ ጥያቄ ያቀርብላታል ፤ ወ
ደ ህሊናዋ
የተመለሰችው የዛሬዋ መሊካ የቀድሞዋ ቫሊሪይ ብራውኒንግ ለኢሳያስ የሚፈልገውን
እንደማትፈፅምለት እቅጩን ትነግረዋለች ። “ድሮውንም ቢሆን የፈጠርንሽ እኛው ነን
፤ አንቺ
ካለኛ ምንም አይደለሽም” ብሎ ያባርራታል ። ይህች ሴት ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ
አፋር
አግብታ መሊካ የሚል ስም ወጥቶላት በአፋር ክልል የበጎ አድራጎት ስራ እየሰራች የ
እርጅና ጊዜዋን
በመግፋት ላይ ትገኛለች ።
ወደ ጄን ዳተን ልመለስ ። ቀደም ሲል እንዳነሳሁት ሁሉ ፤ ከተቻለ በዚህ
ስሌት ካልተቻለ
በጓደኝነት ደረጃ የአልጀዚራዋን ጄን ዳተንን አግባብቶ ጥያቄዋን ረገብ እንድታደርግ
አስፈላጊውን
ሁሉ እንዲያደርግ አሊ አብዶ ታዟል ። ጄን ዳተን አስቀድማ ኤርትራ ከመግባቷ በፊት
ዶሃ ኳታር
ከሚገኘው የኤርትራ እምባሲ ፤ ከፕሬዚደንቱ ጋር ፕሮግራም ይያዝላት ዘንድ ጠይቃ
ነበር
ወደአስመራ የተጓዘችው ። አሥመራ ከደረስች በኋላ ግን ፕሬዚደንቱ አስቸኳይ ስራ
አጋጥሞአቸዋል በሚል ሰበብ የተያዘላት ፕሮግራም ተላለፈና ከተማችንን እናስጎብኝሽ
በሚል
ማግባቢያ የጥያቄ አቅጣጫዋን ለመረዳት በአሊ አብዶ በኩል አስፈላጊው ሁሉ ተፈተሸ
።ይህች
የነጠረች ባለሙያ ጋዜጠኛ ፤ የተያዘላት ፕሮግራም መተላለፍ ማለት ምን ማለት እን
ደሆነ ሙያዊ
ልምዷ ፤ በሚገባ ነግሯታል ። ሻእቢያ በዚህ ሲዘጋጅ ጄንም የራሷን ዝግጅት እያ
ደረገች እንደሆነ

2
የገመተ ግን አልነበረም ። ከሁለት ቀናት የአስመራ ቆይታ በኋላ ፤ ፕሬዚደንቱ ለስ
ራ ወደምጽዋ
ወርደዋልና ወደዚያ መሄድ ትፈልግ እንደሆነ ተነገራት ።
ከአሥመራ እስከ ምፅዋ ያለው ቁልቁለታማ መልክዓ ምድር ፤ በየኪሎ ሜት
ሩ ርቀት
የሚለዋወጥ ድንቅ ትዕይንት ነው ። ቁልቁለቱን ወርዶ ከነፋሲት በታች እስከምፅዋ ድ
ረስ
የሚለበልብ ሙቀት አለ ። አየሩ ይሙቅ እንጂ ጃንዋሪና ፌብሯሪ ላይ ምፅዋ ውብ የሆ
ነ ለብ ያለ
አየር ያላት ከተማ ናት ። ዛሬ አንድ ቅንጣት ቱሪስት ለምልክት እንኳ ዝር የማይል
ባት ከተማ
ብትሆንም ፤ ከዲሴምበር ጀምሮ እስከ ፌብሩአሪ ለጎብኚዎች ምቹ ናት ።
ተልዕኮዋን ሳትጨምርም ሳትቀንስም ፤ ለመወጣት ጄን ዳተን ምፅዋ ወረ
ደች ።
ኢሳያስንም እንድታገኘው ተደረገ ። የአለም አቀፍና የአገር ወስጥ መረጃዎችን ሰብስ
ባ የመጣችው
የአልጀዚራዋ ጋዜጠኛ ጄን ዳተን ፤ የኤርትራ ኮብላይ ስፖርተኞችን ጉዳይ ጨምራ
አምባገነኑን
ኢሳያስን በምፅዋ ጉርጉሱም ቤተ መንግስት ፤ ፍልሚያ ገጠመችው ። “ፍልሚያ ገጠመች
ው”
የሚለውን ቃል የተጠቀምኩበት ዋናው ምክንያት ፤ ቃለ-መጠይቁ የቦክስ ሪንግ ላይ የ
ተገኛኙ
ባላንጣዎች ፍልሚያ አይነት ይመስል ስለነበር ነው ። አንድ የገረመኝን ጥያቄዋንና
ኢሳኢያስ
የሰጣትን መልስ ላስታውሳችሁ ። “አገርህ ውስጥ ችግር ከሌለ እንዴት የኤርትራ እስፖ
ርተኞች
ቡድን ስፖርተኛች እንዳሉ በየሄዱበት አገር ጥገኝነት ይጠይቃሉ?” ትለዋለች ። “እ
ኔ አሁን
የምትይውን ሰምቼ አላውቅም” ብሎ አይኔን ግምባር ያድርገው ሲል ይሸመጥጣል ። እኔ
ይህን
ስሰማ በአለም አቀፉ የአልጀዚራ ሪንግ ላይ ጄን ዳተን ኢሳያስን ስትዘርረው ስእሉ
ታየኝ ። እረ
እንዲያውም እሷ የአልጀዚራ ነብር ፤ እሱ ደግሞ የጥቢ ሳር የጠገበች የኤርትራ ፍየ
ል ነው
የመሰሉኝ ። ራሴም ሳስበው ሳቄ መጣብኝ ። በምጽዋው ጉርጉሱም ቤተ- መንግስት ጊቢ
ውስጥ
ስታሯሩጠው ። ወይ እመት ነብሪትና አይተ ፍየል ?
ወድ አንባቢዬ ፤ ይህን የአልጃዚራ ቃለ ምልልስ ስትመለከቱ ፤ ኢሳያስ ስ
ለተናደደ
“ኡኽ….ኽ….ኡኽ….ኽ……ኡኽ….” እያለ ደጋግሞ ሲተነፍስ ትሰሙታላ
ችሁ ፤ ታዩታላችሁ ።
ጭንቅላቱ ላይ እሳት ሲነድና ሲቃጠል ይሰማችኋል ። የት ቦታ ያራግፈው ይሆን ? ነ
ው የምትሉት
። ጄን ዳተን ሙያዊ የጋዜጠኝነት ስራዋን ካጠናቀቀች በኋላ ወዲያውኑ ነው ቤተ-መን
ግስቱን ለቃ
የወጣችው ። አሊ አብዶ ፤ ጄን ዳተንን ለማግባባት የተሰጠውን ስራ በሚገባ ስላል
ተወጣና
ይሆናሉ ብሎ ለኢሳኢያስ አፈወርቂ ያቀረባቸው ግምታዊ ጥያቄዎችም አንዳቸውም በአልጀ
ዚራዋ
ጋዜጠኛ ስላልቀረቡ ፤ ኢሳያስ ፤ አሊ አብዶን ቤተ መንግስቱ ውስጥ በቦክስ ሲቀጠቅ
ጠው
የጋዜጠኛዋ እግሯ ከግቢው ገና አልወጣም ነበር ። ገላጋይ አይደፍር ተው አይባል
ነገር ሰዎች
አይናቸው እያየ ኢሳያስ እስኪደክመው ድረስ አሊ አብዶን ደበደበው ። ኢሳያስ እኮ
በቅርቡ
ያሉትን ሰዎች ይቅርና ፤ በአጋጣሚ የተጣሉት የመሰሉትን ሌሎች ተራ ዜጎችን እመንገድ
ላይ
መደብደብ የመጀመሪያው አይደለም ። ፕሬዚደንት ሆኖ በአስመራ ቡና ቤቶች እየዞረ ከ
ረምቡላ
ሲጫወት በተጋጣሚው ከተሸነፈ ፤ ተጋጣሚውን እያባረረ እንደሚደበድብ ድፍን አስመራ
የሚያውቀው ፀሃይ የሞቀው ሃቅ ነው ።
ዛሬ አመተ-ምህረቱን በትክክል ባላስታውሰውም በ2003 ወይም በ200
4 እ .አ.ዓ. ም
አካባቢ ነው ። አንድ ወጣት ቡና ቤት ውስጥ ሊዝናና ሲገባ ኢሳያስን ያየዋል። ፕሬ
ዚደንቱን
ወጣቱ በማየቱ ይደሰትና ልጋብዝህ ብሎ ይጠይቀዋል ። ኢሳያስም አንዳችም ምላሽ ለወ
ጣቱ
ሳይሰጠው ጀምሮት የነበረውን ኮሮምቦላ ጨዋታ ይቀጥላል ። በኋላም ኮሮምቦላ ጨዋታው
ይጨርስና ወጣቱ የተቀመጠበት ጠረጴዛ ላይ ሄዶ ከውጣቱ ፊትልትፊት ይቀመጣል ። ወጣቱ
በደስታ ተፍለቀለቀ ። “ግብዣየን በመቀበልህ አመስግናለሁ” ብሎ የሚጠጣውን እንዲያ
ዝዝ
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on March 5, 2015
  • By:
  • Last Modified: March 5, 2015 @ 8:25 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar