www.maledatimes.com የኢትዮጵያ ወመዘክር ቀደምት መጸሃፎች ሽያጭ ኣነጋጋሪ ሆኖኣል - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የኢትዮጵያ ወመዘክር ቀደምት መጸሃፎች ሽያጭ ኣነጋጋሪ ሆኖኣል

By   /   November 17, 2014  /   Comments Off on የኢትዮጵያ ወመዘክር ቀደምት መጸሃፎች ሽያጭ ኣነጋጋሪ ሆኖኣል

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 37 Second

ባሳለፍነው ሳምንት ባገኘነው መረጃ መሰረት የኢትዮጵያ ታሪካዊ መጸሃፍትን በመዝገብ ደረጃ ለዘመናት ያቆየው የመጸሃፍት ቤት በኣዲስ አንዲተኩ ትእዛዝ የተላለፈበት ሲሆን ለነዚህ መጽሃፎች ትእዛዝ  ያስተላለፉትን የመዛግብቱን ባለስልጣን  ለማናገር የሞከርን ሲሆን ለመመለስ ፍቃደኛ ኣለመሆናቸውን እና እናንተ እነማን ናችሕ ይህንን ጥያቄ ልትጠይቁኝ የምትችሉት የሚል ምላ ያስተናገዱ ሲሆን  ጉዳይ  ሲሉ  ቁመዋል ::
የአጼ ቴዎድሮስ፤ የአጼ ሚኒሊክ፤ የአጼ ዮሐንስ ደብዳቤዎችን ጨምሮ ሁለት ሺህ ኪሎ የሚመዝኑ ታሪካዊ ፋይዳቸው ከፍተኛ የሆኑ መጽሃፍትና ጋዜጦች ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መጽሃፍት በኪሎ ፳ ብር ተቸበችብዋል።

 

እነዚህ ጥንታዊ፣ ጥናታዊ፣ አብዛኛው በአይን ምስክር ላይ ተመስርተውና ምርምር ተካሂዶባቸው ጉልበት ጊዜ መዋዕለ ንዋይ ፈሶባቸው በምሁራን የተጻፉ፤ ሃገራችንን ጎብኝተው፤ ከማሕበረሰቡ ጋር ተግባብተውና ባሕልና ልምዱን ቀስመው፤ ልምዱን ተላምደው ለታሪክና ለትውልድም እንዲተላለፍ በማለት በዚያ መጓጓዣ እንደአሁኑ አልጋ ባልጋ ባልሆነበት ዘመን፤ ሽያጭ ያዋጣል አያዋጣም የሚለው ጥያቄ ባልታወቀበትና፤ ተጉዘው ያዩትንና የተረዱትን ላላዩትና እድሉ ላልገጠማቸው ሁሉ እንዲሆን ብለው ጽፈው ለሕትመት ያበቋቸው የሃገራችን ታሪካዊ ሰነዶች በኛው በዜጎቻችንን እንዲጠፉና እንዳይነበቡ ከቤተመዘክራችን ወጥተው አንዱን በ16ኛው ክፍል ዘመን የተጻፈውን መጽሐፍ ከአንድ ኪሎ ሽንኩርት ባነሰ ዋጋ በኛ ዘመን መሸጡ ያሳፍራል፤ ያናድዳል፤ ያሰቆጫል።እነዚህ የሃገርን ታሪክ፤ የሕዝብን ማንነት የሚዘክሩ የታሪክ ቅርሶች እንዲሸጡና ከኢትዮጵያዊያን እንዲርቁ መደረጉ ተተኪው ትውልድ ስለሃገሩ እንዳያውቅና ማንነቱን ጨርሶ እንዲዘነጋ ሆን ተብሎ የሚደረግ ደባ ነው

 

“ጥቅም የላቸውም፤ አርጅተዋል፤ቦታ አጣበቡ፤ ከደራሲያን ማሕበርና ከዩኒቨርሲቲ ምሑራን አይተው እንዲሸጡ የወሰኑት ነው፤ ኮሚቴ ተቋቁሞ ረጂም ጥናትና ምርምር አድረጎበት የወሰነው ነው” ተብሎ ለሽያጭ፤ ያውም በኪሎቱ 20 ብር ከተቸበቸቡት የታሪክ ምስክሮቻችን በጥቂቱ እነሆ:

 

  1. A NEW HISTORY OF ETHIOPIA JOB LUDOLF 1682
  2. HISTORE DE ETHIOPIA GREEN LOPO 1728
  3. JOURNAL OF A VISIT TO SOME PARTS OF ETHIOPIA GEORGE WADDING ESA 1822
  4. LIFE IN ABYSSINIA MANSFIELD PARKYNS 1856
  5. HISTRE EN ABYSSINIA D’ABADDI 1867
  6. NARRATIVE OF THE BIRITISH MISSINO TO THEODROS KING OF ABYSINIA HARMUZD RASSAM 1869
  7. CARDINAL MASSAIA 35 ANNI DI MISSIONE IN ALTA ETHIOPIA 1885
  8. LE NEGUS MENELIK J.G VANDER HEXNI 1899
  9. FIRST FOOT STEPS IN EAST AFRICA –EXPLORATION OF HARRAR CAPT, SIR RICHARD T BURTON 1925
  10. VAT CHRONIQUE GEBRESELASI 1930

 

ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ በያለበት ይህን ድርጊት ሊያወግዘውና የብሔራዊ ቤተመዘክር ወመጻሕፍትን ሃላፊ የመጽሃፉን ሽያጭ የፈቀዱትን ባለፊርማ ለሕግ ማቅረብ ቀዳሚ ተግባሩ ሊያደርገው ይገባ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on November 17, 2014
  • By:
  • Last Modified: November 17, 2014 @ 8:18 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar