www.maledatimes.com የግብጽ መንግስት ልግስና እና የወያኔ የፖለቲካ ኪሳራ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የግብጽ መንግስት ልግስና እና የወያኔ የፖለቲካ ኪሳራ

By   /   May 10, 2015  /   Comments Off on የግብጽ መንግስት ልግስና እና የወያኔ የፖለቲካ ኪሳራ

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 2 Second

ባሳለፍነው ሳምንት የግብጽ መንግስት በሊቢያ የሚገኙትን ኢትዮጵያውያኖችን ታፍነው ከነበረበት የኢሚግሬሽን ካምፕ ውስጥ ከሊቢያ መንግስት ጋር በመደራደር በራሱ ወጭ ወደ ሃገሩ በመውሰድ ከዚያም ወደ ሃገራቸው ኢትዮጵያ መመለሱን በአለም አቀፉ ሚዲያም

ጭምር ሲነገር የነበረ እና የአለምን ህዝብ ትኩረት የሳበ ወሬ እንደነበር ይታወሳል ።

ታዲያ እንዲህ ሆኖ ሳለ የግብጽ መንግስት እና የኢትዮጵያ መንግስት ባደረጉት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይሆናል ተብሎ የህብረተሰብን ቀልብ ከመሳቡም አንጻር የኢትዮጵያ

መንግስት ለዚህ ከፍተኛ ልእልና ለግብጽ መንግስት ዳጎስ ያለ  ገንዘብም ሆነ የአባይ ግድብ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ለየት ያለ ነገር ያቀርባል ተብሎ የተገመተበት  ሁኔታ ነበር ።ይህም ብቻ ሳይሆን ለዚህ ለመጭው ምርጫ ሲባል የፖለቲካ መጠቀሚያ ዘመቻ ያደርገዋል ተብሎ የተጠበቀውን የፖለቲካ ሂደት ፣የግብጽ መንግስት እንዳኮላሸበት ያሳያል ።ይሄውም መንግስት እንደ አገር አስተዳዳሪነቱ ህዝቡን ወይንም ዜጋውን የመጠበቅ ግዴታ እና መብቱም እንደመሆኑ መጠን አለማድረጉ ትልቅ የፖለቲካ ኪሳራ የግብጽ መንግስት አድርሶበታል ።

የግብጽ መንግስት ይህንን ጉዳይ ባደረገ እለት የማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል ወደ ግብጽ ኤምባሲ ስልክ በመደወል የቆንጽላ ጽህፈት ቤቱን ሃላፊ እና የህዝብ ግንኙነቱን ጭምር አነጋግሮ በቂ የሆነ ምላሽ ሰጥተውታል ። ለዚህም ምላሽ የወያኔ ኢሃዴግ አስተዳር ለህዝቡ ምን ይላል የሚለውን በመጠባበቅ ላይ የነበረ ሲሆን በተለይም የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ዶ/ር አቶ ቴወድሮስ አድሃኖም በተለያዩ የማህበራዊ ግንኙነት ወይንም ሶሻል ኔትወርኮች ላይ የሚለጥፏቸውን የፖለቲካ ጠመዝማዛ ጉዞ ምን ይመስላል የሚለውን በሰከነ ኧምሮ ሲመለከት ቆይቷል ታዲያ ለዚያም ምላሽ ለመስጠት ያስችለው ዘንድ የተወሰኑ ቀናቶችን መጠበቅ ግዴታው ስለነበር ሲጠብቅ ቆይቷል ታዲያ የወሬው መቆርፈድ አይፈለግም እና ወቅቱን ጠብቆ ማቅረብም ተገቢነቱን ያምናል እና ይህንን ለማቅረብ መሰናዶውን አጠናቆ ለማቅብ ተገዶል።

ከግብጽ አምባሳደሮች ጋር ያደረገው ውይይት ለ፴ ደቂቃ የቆየ ውይይት የነበረ ሲሆን በሁለት ቀን የተከፈለ የጥያቄና መልስ ዝግጅት ነበር ። በእነዚህም ጊዜያቶች ውስጥ  የቀረቡት ጥያቄዎችን ቃል በቃል በድምጽ ከማቅረብ ይልቅ በጽሁፍ ማቅረቡ አንባቢያኖችን

ይበልጥ ግልጽ እንዲሆንላቸው ያደርጋል ብለን ስላመንን  እንዲህ ቀርቦአል ።

የተከበሩ አምባሳደር የግብጽ መንግስት ለኢትዮጵይ ህዝብ ያደረገው ይህ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ከምን የተነሳ ነው ስደተኞቹን ለምን መሰብሰብ ፈለገ?

አምባሳደር ስደተኞቹ በቅድሚያ ታግተው የነበረው በሊቢያ መንግስት ስር ነው ። በሊቢይ መንግስት ስር ላይ ወድቀው ምንም አይነት እዳታም ሆነ አስፈላጊውን ድጋፍም አልተደረገላቸውም

ይህ ብቻም አይደለም የሊቢያ መንግስት ጋር አብረው የሚሰሩት የሰኩሪቲ ኤጀንቶች ከኢይሲስ ጋር በመስራት ጥምር የሆነ አገልግሎታቸው ብዙ ጥፋት እንዲጠፋ እያእረገ ነው ።በዚህም ሁኔታ የግብጽም ሆነ የኢትዮጵያ ዜጎች በሰኩሪቲዎቻቸው የተያዙ ሰዎች ናቸው የተሰውት ።ግማሾቹም በለሊት ከታሰሩበት ተወስደዋል ግማሾቹም ከየመኖሪያ አካባቢያቸው ተጠልፈዋል።

ይህ አድራጎታችሁ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያላችሁን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያጠናክረዋል ብላችሁ ታስባላችሁ ?

አምባሳደር ፦የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ጎዳና ከግብጽ ጋር ያላት ልዩ ግንኙነት የዛሬ አይደለም በ1956 ጋማል አብዱል ናስር ከመመረጡ በፊት ግብጽ በንጉሳዊ አስተዳደር በምትገዛበት ወቅት ግብጽ የጠበቀ ግኑኝነት ከኢትዮጵያ ጋር ነበራት ፣ይህ ማለት የቅርብ ጊዜ ትውስታ የምንለው ሲሆን  ዛሬም ነገም ሊኖራት ይችላል ።እንደ ጎረቤት አገርነታችን ግንኙነታችንን ምንም ነገር ያደርፈርስብናል ብለን አናምንም ። ይኅንንም ስንል ያደረግነው ነገር ከጥቅም ፍለጋ ጋር የተያያዘ ሳይሆን በሊቢያ ያሉት መንግስታቶች የማፍያ ስብስብ ስለሆነ ማንኛውንም ስደተኛ የሆኑዜጎችን ህይወት ለማትረፍ ያደረግነው ጥረት ነው ።ለዚህም መንግስታችንን እና ህዝባችንን ልናመሰግን ይገባል።ይህ የመልካም አስተዳደር ጥምር ስራ እንደሆነ ያስረዳል።

በሌላስ መልኩ ከአባይ ግድብ ጋር ባላችሁ የመግባባት እና ያለመግባባት ስሜትን ወደ መልካም ጎዳና እንዲወስድ ያደረጋችሁት ነው ተብሎ ይገመታል ይህንንስ እንዴት ያውታል ክቡር አምባሳደር ?

አምባሳደር፦ ይህ የእኛ አላማ አይደለም ዋነኛው ጉድያችን ከሊቢያ መንግስት ጋር በጋራ ከሚሰሩት የማፍያ ቡድን ጋር ያለውን ነገር ማኮላሸት ሲሆን በአገራችንም ሆነ በሌሎች ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመከላከል የምናደርገው ሽፋን ነው እንጂ በአባይ ጉዳይ ላይ ሊነሳ የሚችል አዳችም ነገር የለንም ።ይህንንም አስመልክቶ መንግስታችን ያደረገው ምንም የጥቅም ጣልቃ ገብነት የለም ;በራሳችን ተነሳሽነት ያደረግነው ነገርን ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ የሚያስወስደው ነገር የለም ።አባይ የጋራ ሃብታችን እንደሆነ እናምናለን ።

በቀጣዩ የኢትዮጵያ ምርጫ ላይ የግብጽን ስራ ልክ መንግስት በራሱ ፈቃድ እንደሰራ አድርጎ ለፖለቲካዊ ቅስቀሳ ልጠቀምበት ይችላል እና እናንተ ጋር ያደረጋችሁት ዲፕሎማሲያዊ መንገድ የት ድረስ ነው ?

ከኢትዮጵያ ጋር ባሳለፍናቸው ወራቶች የተለያዩ የቅርርብነት ስራ ሰርተናል ሆኖም ግን ስደተኞቹን አስመልክቶ የሃገራችን መንግስት የተፈራረመው ነገር የለም ይህንንም ስልህ በድንበራችን አቋርጠው እንዲገቡ የተጠየቁ ስደተኞች ካሉ እንደንቀበል ተጠይቀናል ይህንንም ፈቃዳችንን ሰጥተናል እንደዚያም ሆኖ በሞት መካከል ደፍሮ አገር አቋርጦ ከሊቢያ ወደ ግብጽ የመጣ የለም ፣ መንግስትም ይህንን ውሳኔ ለእኛ በጥያቄ መልክ ሲያቀርበው በጣም ገርሞን ነበር ምክንያቱም ግመል በመርፌ ቀዳዳ እንደማሹለክ መሆኑን አስበው ፣ከአንበሳ መንጋጋ አምልጦ አሌክዛንደርያ መድረስ ከባድ ነው ።ስለዚህ ማንኛውም ስደተኛ ከሊቢያ የመውጣቱ ጉዳይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው ያለው ወደ ጎረቤት አገሮች ለመሸጋገር እሚያስችለው መንገድ የለውም ፣ለምን የሚል ጥያቄ ከማምጣትህ በፊት ምላሹን ልስጥህ እነዚህ ገዳዮች በሙሉ በዳር ድንበሮች ላይ ናቸው ያሉት ለዚህም ነው ግብጽ የጥቃት አላማዋን ለመሰንዘር የቻለችው አሁንም የምንዘጋጀው ቀዳሚውን የሆነውን የሰላማችንን አድፍራሽ ነገር ለማጥፋት ቀድመን ልንጠነቀቅ በሚያስችለን መልኩ ስደተኞችን ለመሰብሰብ ከሊቢያ ጋር እየተስማማን ያለነው ። ስለዚህ በግብጽ መንግስት ስራ ላይ የተደረገ ድፕሎማሲያዊም ሆነ ፖለቲካዊ ግፊት ያለው እርምጃ ከኢትዮጵያ መንግስት አለምጣም ።

የግብጽ መንግስት በኢትዮጵያን ክርስትያኖች ላይ አይሥስ የወሰደውን እርምጃ እንዴት ያየዋል? በሌላስ በኩል የኢትዮጵያ መንግስት በህዝቦቹ ላይ የፈጸመውን ጥቃት እንዴት ይመለከቱታል?

እንደምታውቀው በተለያዩ አቅጣጫዎች አይሥስ የሰዎችን ህይወት እየቀጠፈ ነው ።ግብጾችንም ኢትዮጵያውያኖችንም ፣ኢራቅም፣ሴርያም በየቦታው ህይወታቸውን ያጥ ብዙሃኖች አሉ በጣም ያሳዝናል።ይህ የነፍሰ ገዳዮች ጥርቅም እንጂ የጤነኛ ሰው ስራ አይደለም እና የግብጽ መንግስትም ሆነ የመላው አለም ህዝብ በተገደሉት ዜጎች በጣም አዝⶈል ፣ይህንንም ትኩረት ለመስጠት እና ሌሎችን ለማዳን ስንል ነው  ፣ከሊቢያ እጅ ነጥቀን ወደ ሃገራችን ማስገባት የፈለግነው  ቅድም እንደነገርኩህ ከሊቢያ የሰኩሪቲ ኤጀንትም ጋር ሆነ ከፖሊሶች ጋር በጋራ በመሆን የሚሰሩ የአይሲስ አባላቶች እንዳሉ ተገንዘብ የሰውን ህይወት አሳልፎ ለመስጠት በጣም ቀላል ነው ለነሱ ስለዚህ ማንኛውም ንጹሃን ዜጋ ያለምንም ጥፋቱ ማለፍ የለበትም።

በሁለተኛ የጠየከኝን ጥያቄ ሙሉ ምላሽ ባይኖረኝም ግን ትክክል ይሆናል ብዬ አላምንም ።

ሰለሰጡኝ ትልቅ ጊዜ ከልብ አመሰግናለሁ ክቡር አምባሳደር

እኔም አመሰግናለሁ ሰር

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on May 10, 2015
  • By:
  • Last Modified: May 11, 2015 @ 12:20 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar