www.maledatimes.com ይድረስ ማስተዋል ላልተሳናቸው ሰዎች በሙሉ፡፡ ከፍሬሂወት አሰፋ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ይድረስ ማስተዋል ላልተሳናቸው ሰዎች በሙሉ፡፡ ከፍሬሂወት አሰፋ

By   /   November 27, 2014  /   Comments Off on ይድረስ ማስተዋል ላልተሳናቸው ሰዎች በሙሉ፡፡ ከፍሬሂወት አሰፋ

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 41 Second

ከሁሉ አስቀድሜ እንደነ አርቲስት አዜብ ወርቁ እና ጥቂት መሰል ታዋቂ ሰዎቻችን እና የሴቶች ጉዳይ መ/ቤት / ስሙን በትክክል ባለመፃፌ በጣም ይቅርታ/ በሀና ጉዳይ እያደረጋችሁት ላለው ዘመቻ በጣም ላመሰግን እወዳለሁ፡፡ ግን ልክ እንደነአዜብ ሁሉ ምነው ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝብ ሀብቴ… የሚሉት መሰል “ፌመሶች/ እህ…ታዋቂዎች/” መነሳት ተሳናቸው፡፡ከሀብታቸው መካከል እኮ ሀናም አንዷ ነበረች፡፡ እውነት ሀብታቸው ከሆነ ማለቴ ነው፡፡ ድርጅቶች ነን ባዮችሽ የሚቦጫጨቅ ገንዘብ ካልተመደበ በስተቀር ትናንሽ ምክንያት እየፈጠሩ በግማሽ ሚሊዮን ብር እንደሚጨወቱበት ጢባጢቤ አሳሳቢ ሳይሆን ቀርቶ ነው ነገሩ ገሸሽ የተደረገው?፡፡ የሀናን ቤት ያንኳኳ አውሬ ነገ የእነሱን ቤት ማንኳኳቱ የሚቀርላቸው መስሏቸው ይሆን?

ሰሞኑን በፊት መጽሐፋችን (facebook) በተገጠገጡ አስተያየቶች ላይ ሀና በግፍ ወደ ሞት በመውረዷ የማይጸጸቱ እንዳሉና “የእጇን ነው ያገኘችው” የሚሉ እንዳሉ አነበብኩ ልበል?
አያሳዝንም የሰው ልጅ ፍርደገምድልነት? ለነገሩ “አባት የገዛ የ3 ዓመት ህፃን ልጁን ደፍሮ እናት እንዳትናገር አስጠንቅቃ ገረፈቻች” ፣ እናት ህፃን ልጇ ባላት አቅምም ቢሆን ሆዱን እንደማጥገብ ተርቦ ወስዶ ለበላው “ቁራሽ ዶቦ ሰርቆ በላ ብላ ሰውነቱን በጋለ ቢላ አቃጥላ ተለተለችው” እየተባለ በሚወራበት ሀገር ውስጥ እንዲህ አይነት “እሰይ የእጇን ነው ያገኘችው” የሚል ወሬን መስማት ብርቅ አይደለም፡፡
ከዚህ ቀደም ምንም የራቀ ቢመስለንም ነገር ግን መቼም ልንዘነጋቸው የማንችላቸውን የእነ ሔርሜላ እና የእነ ካሚላት የፍርድ ቤት ውሎ በአንድ ወቅት ወንድና ሴት ጎራ ለይቶ ነበር፡፡ የሚገርመው እስከአሁን ድረስ የተሰሙት ዜናዎች ወንጀል ፈጣሪዎቹ ወንዶች ናቸው ፡፡ ወንዶቹ ወንድ ስለሆነ ብቻ ለወንጀለኛው ፣ ሴቶቹ ደግሞ ነገ በእኔ በማለት ለተበዳይዋ ቆመው ነበር፡፡ ፍርዶቹ የተዛቡ በመሆናቸው ተመሳሳይ ወንጀሎች ቀጠሉ ፡፡ እንድ እህታችንን በተመሳሳይ የአይሲድ መድፋት ህይወቷን አጣች ፡፡ ፍሬህይወት የተባለች አንዲት ወጣት በአደባባይ መስቀል ፍላወር አካባቢ በጥይት እሩምታ የሞት ጽዋው ደረሳት፡፡
አበራሽ የአይን ብርሀንዋን አጣች፡፡ … ከሁሉ የሚበልጠው ደግሞ ስለእውነት ያልተነሱ ፣ ነበልባሉን ብቻ በማየት ሮጠው ሄደው የሚነድ እሳት መሆኑን ሲያውቁ በላዩ ላይ ጋዝ አርከፍክፈው እነሱ የሚሞቁ፣ እኛ የእናንተ ድምጽ ነን በማለት በሌላው ሀዘን ላይ የገበያ ማማቸውን የሚያደላድሉ ውይ … ስለእነሱስ …. አምላክ አሁንም እነዚህን የፓለቲካ እና የፍቅር መጽሔት ተብዬዎች ጠራርጎ ያጥፋልንና ድምፃዊት ሀይማኖት በአንድ ወቅት በትዳርዋ ላይ ባጋጠማት ግጭት ምክንያት እንኪያ ሰላምታ በማሟሟቅ ለከፋ አደጋ ዳርገዋትም ነበር፡፡ ”የወንጀለኞች የተደበቀ ሚስጢር” ፣ “ያልተሰማለት እውነታ” ፣ “ሰዎች እንዲያውቁለት” ፣ “ከፍርድ ቤት ከወንጀለኛው ለተጎጅዋ የተፃፈ” ፣ ወንጀለኛው የኢትዮጵያ ህዝብ አንዲያውቅለት የሚፈልገው ነገር” ምናምን እያሉ ፍርድን ለማዛባት ብዕር ሳይሆን ጦራቸውን የቀሰሩት የሚዲያ አካላት ኢትዮጵያ ውስጥ እየኖሩ ኢትዮጵያዊያን ያልሆኑ ፣ ከሰው ተፈጥረው አውሬ የሆኑ ፣ ጎረቤት ሲያለቅስ እነሱ የሚያስቃቸው ምን አይነት ልቦና ቢኖራቸው ነው፡፡ ሆዳም ጠበቃ ነኝ ባይም ፍጥጥ ያለውን ወንጀላቸውን የውሸት ካባ አልብሶ ነፃ ለማውጣት አንቀጽ ያጣቅሳል፡፡ ለሆዱ ያደረም ዳኛ ከሆነ ምን አገባው ከርሱ ይሙላ እንጂ ምን አገባው፡፡
በመግቢያዬ ላይ ለመግለጽ አንደሞከርኩት ቢያንስ እናንተ በድፍረት በፊት መጽሐፋችን ላይ እንኳን እየጮሀችሁ ነው ያላችሁት ፡፡ ሌላውስ ለእይታ ብቻ አለሁ አለሁ ብሎ እጁን አጣጥፎ ለምን ይቀመጣል፡፡ አርቲስቱም ብር ያለበት ብቻ ወሸባ ማብዛት ይወዳል፡፡ ይሄኔ ለዚህ ጉዳይ ይሄንን ያህል በጀት ተመድቧል ቢባል አቤት የኘሮኘዛል መዓት! ፡፡ እንትና ኘሮሞሽን በዚያ ወፍራም ክንዱ ማማውን ይቆናጠጥና ቲቪ ላይ እረጭ እረጭ ብሎ ኪሱን ያደልባል፣ ከዚያ ኮንሰርት ምናምንም ይልና መድረክ መምራቱን ፣ ማስተባባሩን ፣ ማስታወቂያ መስራቱን አረ ምኑ ቅጡ ሜዳውም ፈረሱም የእርሱ ብቻ ሆነ እንዳሻው ይጋልባል፡፡
እውነታውን ግን እንገንዘብ፡፡
ወንድና ሴት ከስሜት መፈላለግ የዘለለ ምን ያህል የጋራ ትስስር አንዳለን ማናችንም የገባን አይመስለኝም፡፡ ወንዶች ይቅርታ አድርጉልኝና በአብዛኛውን ወንዶች ሴቶች የጭን ገረድ አድርጎ ከማሰብ የዘዘለ የተለየ ለህይወታችን ልዩ እገዛ ፣ ድምቀት ፣ ደስታ፣ ውበት የምትሰጠንን የእናትነት ፣ የእህትነት ፣ የሚስትነት ስሜት ሊሰማቸው እንደሚችል አላውቅም፡፡ ሁሌም በምሰማቸው ዜናዎች አዝናለሁ፣ አለቅሳለሁ፡፡
እንኳን ትንሽ ልጅ ይቅርና ማንም ትልቅ ሰውም ያጠፋል ፣ ይሳሳታል፡፡ የፈለገ ቢሆን ግን ለሞት የሚዳርግ ቅጣት መቅጣት የእኛ የሰዎች ስልጣንም ተግባርም መሆን አይገባውም፡፡
እስኪ ወደ አዳምና ሔዋን አፈጣጠር እንመለስ አዳም ያለሔዋን ባዶ ስለሆነ ሔዋን ተሰጠችው፡፡ ሔዋንም ብቻዋን መቆም ውበት ስለሌላት ከጎኑ ተሸጉጣ ተገኘች፡፡ አዳም አለም ሁሉ በእጁ ሆኖ ሁሉ እያለው በምንም ያልተደነቀው ሔዋንን ሲያት ግን አደነቃት፡፡
አሁን ተረት ላወራ አልያም እምነት ልሰብክ ፈልጌ ሳይሆን እስኪ የእኔ በሚል ስሜት እንተሳሰብ እንዋደድ፡፡ በጣም የሚገርመው የሀና አውሬዎች የአንድ ቀን አውሬነታቸው ሳያንሳቸው ስቃይዋን እያዳመጡ በየቀኑ የግል ስሜታቸውን መወጣጫ ማድረጋቸው ነው፡፡ ከዚህ የበለጠ አውሬነት ከየት ይምጣ፡፡ ሞት የአምላክ ፍርድ ብቻ ቢሆንም ለእነዚህ ሰዎች ግን ሞት ይገባቸዋል፡፡ ሞት ቅጣት ሆኖ አይደለም፡፡ የእነሱ ሞት ሀናን ከሞት አይመልስም፣ የሀና ቤተሰቦችን ቁስል አይሽርም፡፡ ነገር ግን በምድር ላይ ኖረው ሌሎችንም የከፋ ግፍ እንዳይፈጽሙ ይረዳል፡፡
ግን አሁንም አንድ እውነታ ማወቅ አለብን፡፡ ወንድ ያለ ሴት ጋን ውስጥ ያለ መብራት ማለት ነው፡፡ የፈለገ ቢለፋ ቢታትር አንድ እርምጃ መራመድ አይችልም፡፡ ሴትም ያለ ወንድ ብታምር ብትደምቅ ከንቱ ነው ፡፡ እንኳን ሰው ጋር ደምግባትዋ ገኖ ሊታይ ይቅርና ለእርስዋም እራሱ አስቀያሚ ነው የሚሆነው፡፡ የአንድ ወንድ ስኬት ሴት ናት፡፡ የዚያ ስኬትማ ወንድ ውበትና ክብር ደግሚ በሴቲቲ ደምቆ አብረው ያበራሉ፡፡
ቢያንስ አንባቢ እንሁን፡፡ አለማዊ ብንሆንም የትኛውም የአለም መጽሐፍ እንዲህ አይነት ግፍ ፈጽም አይልም፡፡ ሀይማኖተኛ ከሆንም የትኛውም እምነት በሴት ላይ አውሬትን አያስተምርም፡፡
እንኳን ቁልጭ ያለ እውነትን ቀርቶ ኤችአይቬ ኤድስንም እኮ እጅ ለእጅ በመስራት ታሪክ አድርገነዋል፡፡ የአንዳችን ቁስል ለሌሎቻችንም ይሰማ የግድ በእኛ ላይ መድረስ የለበትም፡፡ ሀና እና ሌሎች የሰለባው ተጎጅዎችን በእኛ ቦታ እናስቀምጣቸው፡፡ የወንድ ሀይለኝነት ይብቃ፡፡ እንፋቀር ፣ እንዋደድ፡፡ በአምላክ ስም ልለምናችሁ፡፡
ለሁላችንም እግዚያብሔር ልቦና ይስጠን ፡፡ የተፈጠርንበትን አላማ እንድነዳ አይነልቦናችን ይብራልቀን፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on November 27, 2014
  • By:
  • Last Modified: November 27, 2014 @ 10:49 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar