www.maledatimes.com ማህበረ-ቅዱሳን የዜሮ ድምር ጫወታ ተረኛው ሰለባ ሆኖ ይሆን? - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ማህበረ-ቅዱሳን የዜሮ ድምር ጫወታ ተረኛው ሰለባ ሆኖ ይሆን?

By   /   April 9, 2014  /   Comments Off on ማህበረ-ቅዱሳን የዜሮ ድምር ጫወታ ተረኛው ሰለባ ሆኖ ይሆን?

    Print       Email
0 0
Read Time:13 Minute, 31 Second

ጀርመናዊ የፕሮቴስታን እምነት ተከታይ እና ፓስተር የነበሩት ማርቲን ኒሞለር በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በሃገራቸው በጀርመን ሰፍኖ የነበረውን የናዚዎችን የኢ-ፍትሃዊነት ድርጊትን ዝምታን በመምረጥ ተገቢ መሆኑን ማሳየት እና የዜሮ ድምር ጫወታ የአስተሳሰብ ስልት ስላስከተለው ቀውስ በ1968 በአሜሪካ ኮንግረስ ቀርበው የተናገሩትን አስተማሪ ንግግር ከኛ ሃገር ነባራዊ የኢ-ፍትሃዊነት ድግግሞሽ ወንጀልን በዝምታ የማበረታት እና ብሎም የሃገራችንን የዜሮ ድምር ጫወታ ሂደት በትክክል የሚያንፀባርቅ ሆኖ ስላገኘነው ልናካፍላችሁ ወደናል። ፓስተር ማርቲን ሲናገሩ …
ናዚዎች መጀመርያ ኮሚኒስቶችን አጠቁ እኔም ኮሚኒስት ስላልነበርኩ ምንም አልተናገርኩም
ከዛም ሶሻሊስቶችን አጠቁ ሶሻሊስት ስላልነበርኩ ምንም አልተናገርኩም
ከዛም የሰራተኛ ማህበራትን አጠቁ አባል ስላልነበር ዝምታን መረጥኩ
በማስከተል ይሁዶችን አጠቁ ይሁድ ስላልነበርኩ ስለነሱ ምንም አልተናገርኩም
በመጨረሻ እኔን እና ቤተክርስትያኔን ሲያጠቁ ሌላ ተናጋሪ እና አጋዥ ስላል ነበረ ብቻዬን ተመታሁ።

በተመሳሳይ ሁኔታ ታሪክ እራሱን ሲደግም። ኢ-ፍትሃዊ ድርጊትን በዝምታ ማጽደቃችን እና የዜሮ ድምር ጫወታችን ያደረሱብንን መከራ እና የፍትህ መጔደል እንደ ሚከተለው መግለጽ ይቻላል ።
ኢህአዴግ መጀመርያ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያንን ቃኖና በመጣስ ጳጳስ እያሉ ሌላ ጳጳስ ሲሾም ኦርቶዶክስ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያን ዝምታን መረጡ
ከዛም ኢህአዴግ 1994 በአንዋር መስጅድ በርካታ ሙስሊሞችን ገድሎ በርካቶችን ሲያስር ሌሎች ሙስሊም ያልሆን ዝምታን መርጠዋል
የዛሬ ሁለት አመት የተቀሰቀሰው የሙስሊሙ ህብረተብ የመብት ጠያቄዎችን ሲያጠቃ በጅምሩ ወቅት ሙስሊም ያልሆኑትን ዝምታን መርጠው ነበር
ዛሬ ደግሞ በማህበረቅዱሳን ላይ መንግስት ጥቃቱን ሲጀምር አንዳንድ የፕሮቴስታንት አማኝ ወገኖቻችን ዝምታን መምረጥ ብቻ ሳይሆን ተገቢነቱን ለማሳየት መሞከራቸው ነገ በነሱ ላይ ሲመጣ ብቻቸው እንደ ፓስተር ማርቲ ለጥቃት እንደሚጋለጡ ምነው ማስተዋል ተሳናቸው?

የዜሮ ድምር ጫወታ ውጤት ሁሉንም ተበዳይ ወገን ዜሮ ሲያከናንብ በዳይን 100% አሸናፊ በማድረግ የግፍ በትሩን ባሰኘው ግዜ እና ቦታ ያለ ተቀናቃኝ እንዲፈፅም ያስችለዋል።

ያለመታደል ሆኖ የኛ ኢትዮጵያውያን ኢ-ፍትሃዊ ድርጊትን በዝምታ የማበረታት እና የዜሮ ድምር ጫወታችን የፖለቲካ መድረክንም ሆነ ሌላኛውን የማህበራዊ ገፅታ መበከሉ ይኸው ከሁለት አስርተ ዓመታት ወዲህ የመንፈሳዊው መንገዶች ጭምር ለዚህ በሽታ በማጋለጡ የአንዱ መጎዳት ሌላኛውን እያስደሰተው ከዛም አልፎ ወገኑን ለመጉዳት መሳርያ እየሆነ ለኢህአዴግ ትምክህት የተሞላበት ኢ-ህገመንግስታዊ የመብት ጥሰት መሳርያ ሆኖ ሲያገለግል ቆይቷል። ይህ ክፉ አስተሳሰብ በህዝባችን ውስጥ የፈጠረው የአመለካከት ብክለት የአንድ ወገን መብት መገፈፍ ለሌላኛው ባላጋራችን ለምንለው መብት የሚጨምር እየመሰለን በተለያየ መልኩ አንድ የማህበረሰብ ክፍል ሌላኛውን ወገኑን ለአደጋ የሚያጋልጥ ኢ-ህገመንግስታዊ ጥሰቶችን አንዳንዴ አስፈጻሚ ካልሆነም ደግሞ የሚፈፀመውን ወንጀል ስናስተናንስ እና ተገቢ እንደሆነ ለማስመሰል ስንዳክር መቆየቱ መብት ነጣቂዎች ያለብዙ ድካም አንዱን ከሌላኛው በማጋጨት ከፈለጉት አላማ እንዲደርሱ እገዛ አድርገናል።
ይህ የአስተሳሰብ ዘይቤ ዛሬ ላይ የፖለቲካ መስመሮችን ብቻ ሳይሆን የእምነት ተቋማትንም እያመሰ ይገኛል። እንደምናውቀው ሰሞኑን የኢህአዴግ ተረኛው ሰለባ የማህበረ-ቅዱሳን ሆኖ ተገኝቷል። ይህ ድርጅት ከተመሰረተበት ግዜ ጀምሮ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያንን ሲያግዝ እና ምእመናንን በተለይም ወጣቱን ትውልድ ሃይማኖቱን በተገቢው መንገድ እንዲተገብር ፣ በእውቀት እንዲጎለብት እና መንፈሳዊ ሆነ ቁሳዊ ፍላጎቶችን ሲያሟላ ድጎማዎችን በስፋት ሲያበረክት ቆይቷል። ይህ ተግባሩ ድርጅቱን በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ትልቅ አመኔታ እና ክብር እንዲያገኝ አስችሎታል።
ነገር ግን ይህን መሰል የጎላ እና የሚደነቅ አስተዋፆ ለእምነቱ ተከታዮች ሲያበረክት የቆየው ይህ ተቋም በሌላ መልኩ ግን አባሎቹ የሌላ እምነት ተከታይ በሆኑ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ አሳዛኝ በደሎችን ስፈጽሙ መታየታቸው የዜሮ ድምር ጫወታችን መንፈሳዊውንም አለም ሳይቀር እንደ በከለ የሚያሳይ ነው። ስለዝህ ይህን ክፉ በሽታ ድል ለመንሳት ልንወስደው የሚገባን እርምጃ ቢኖር መተማመንን የምያጎለብቱ ድርጊቶች ላይ በማተኮር ለጋራ ደህንነት እና ፍትህ በጋራ መድረኮች መንቀሳቀስ እንደ አንድ አዋጭ ጅምር ልወሰድ ይችላል።
የዚህ ክፉ አስተሳሰብ ስልት ሰለባ መሆናችን በታሪክ ውስጥ ከተፈፀሙ ጎላ ያሉ ስህተቶች እንዳንማር ብቃት ስላሳጣን ዛሬ ሁላችንም በየተራችን የጨቋኞች መሳለቂያ ሆነናል። ይህ እየደረሰብን ያለው ሁኔታ ከመግቢያው ላይ ከሰፈረው በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት ከደረሰው የታሪክ ገጠመኝ ጋር ያለውን ተመሳሳይነት እስኪ በጋራ እንመልከተው።
በተመሳሳይ ሁኔታ ታሪክ እራሱን ሲደግም። ኢ-ፍትሃዊ ድርጊትን በዝምታ ማጽደቃችን እና የዜሮ ድምር ጫወታችን ያደረሱብንን መከራ እና የፍትህ መጔደል እንደ ሚከተለው መግለጽ ይቻላል ።
ኢህአዴግ መጀመርያ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያንን ቃኖና በመጣስ ጳጳስ እያሉ ሌላ ጳጳስ ሲሾም ኦርቶዶክስ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያን ዝምታን መረጡ
ከዛም ኢህአዴግ 1994 በአንዋር መስጅድ በርካታ ሙስሊሞችን ገድሎ በርካቶችን ሲያስር ሌሎች ሙስሊም ያልሆን ዝምታን መርጠዋል
የዛሬ ሁለት አመት የተቀሰቀሰው የሙስሊሙ ህብረተብ የመብት ጠያቄዎችን ሲያጠቃ በጅምሩ ወቅት ሙስሊም ያልሆኑትን ዝምታን መርጠው ነበር
ዛሬ ደግሞ በማህበረቅዱሳን ላይ መንግስት ጥቃቱን ሲጀምር አንዳንድ የፕሮቴስታንት አማኝ ወገኖቻችን ዝምታን መምረጥ ብቻ ሳይሆን ተገቢነቱን ለማሳየት መሞከራቸው ነገ በነሱ ላይ ሲመጣ ብቻቸው እንደ ፓስተር ማርቲ ለጥቃት እንደሚጋለጡ ምነው ማስተዋል ተሳናቸው?

የዜሮ ድምር ጫወታ ውጤት ሁሉንም ተበዳይ ወገን ዜሮ ሲያከናንብ በዳይን 100% አሸናፊ በማድረግ የግፍ በትሩን ባሰኘው ግዜ እና ቦታ ያለ ተቀናቃኝ እንዲፈፅም ያስችለዋል።

በሃገራችን ለተፈፀሙ ስህተቶች እውቅና ሰጥተን ዳግም ተመሳሳይ ስህተቶች የማይፈጸሙበትን ስልት በመቀየስ ለወደፊት ከጥፋት መጠበቅ
የአንዱ ወገን መበደል የሁሉም ዜጋ መበደል መሆኑን ተገንዝበን ለሁለንተናዊ ፍትህ መስፈን በጋራ በመቆም በዳዮችን ማሳፈር እና የተንኮል እቅዳቸው በጋራ ማጨናገፍ
ሁሉም ዜጋ የሃገራችን የእኩል ባለቤት መሆኑን በህሊናችን አስርጸን ለእኩልነት በአንድነት መቆም

በሃገራችን የህግ የበላይነት እንዲሰፍን በጋራ መፋለም ይበጃልና እናስተውል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on April 9, 2014
  • By:
  • Last Modified: April 9, 2014 @ 11:20 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar