www.maledatimes.com ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ

By   /   April 13, 2014  /   Comments Off on ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ

    Print       Email
0 0
Read Time:6 Minute, 13 Second

 

ሰማያዊፓርቲበአዲስአበባሰላማዊሰልፍጠራ

 

አዲስ አበባ፡ ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹የተነጠቁ መብቶችን እናስመልስ!›› በሚል መሪ ቃል ሚያዚያ 19/2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ከአሁን ቀደም የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት ምላሽ እንዲሰጣቸው ቢጠይቅም ጥያቄዎቹ ምላሽ ያልተሰጣቸው ከመሆኑም ባሻገር ጭራሹን እየተባባሱ በመምጣታቸውና ህዝብም እየተማረረ በመሆኑ ሰላማዊ ሰልፉን መጥራት እንዳስፈለገ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25 2005 ዓ.ም ያደረገውን ጨምሮ በአዲስ አበባና ሌሎች አካባቢዎች ሰላማዊ ሰልፎችንና ህዝባዊ ስብሰባዎችን ባደረገበት ወቅት የኑሮ ውድነት፣ የእምነት ጣልቃ ገብነት፣ ሉዓላዊነት፣ ዜጎችን ከቀያቸው ማፈናቀልና ሌሎችም መሰረታዊ ጥያቄዎችን አንስቶ የነበረ ቢሆንም ጥያቄዎቹ ምላሽ ሊያገኙ እንዳልቻሉ የህዝብ ግንኙነቱ ገልጸዋል፡፡ ከዚህ በተቃራኒ በእስልምና እና ኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች ላይ የሚደረገው ጣልቃ ገብነት፣ ዜጎችን ከቀያቸው ማፈናቀሉ፣ የኑሮ ውድነት፣ ሙስና አሁንም ድረስ ተባብሰው መቀጠላቸው ሰላማዊ ሰልፉን በመጥራት ህዝቡ እነዚህን የተነጠቁ መብቶች እንዲያስመለስ ማስተባበርና ማታገል የግድ በማለቱ ነው ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ ለገዥው ፓርቲ ስልጣን እንጅ ለህዝብ አገልግሎት የማይጨነቁት ተቋማት ስራቸውን በሚገባ ባለመስራትቸው ህዝብ ለከፈለው ክፍያ የሚገባውን አገልግሎት እያገኘ አለመሆኑም ሌላኛው ሰላማዊ የሰልፉ ምክንያት መሆኑን ተገልጹዋል፡፡ በተለይ የውሃ፣ የመብራት፣ የቴሌኮሚኒኬሽንና የትራንስፖርት አገልግሎቶች ህዝብን እያማረሩ መቀጠላቸው መፍትሄ ስለሚያስፈልገው የሰላማዊ ሰልፉን አስፈላጊነት እንዲሚያጎላው ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡Blue Advert April 12

ምንም እንኳ ‹‹የህዝብ መብት መነጠቅና የአግልግሎቶች እጦት ሰላማዊ ሰልፉን ወቅታዊ ቢያደርገውም የሰማያዊ ፓርቲ በአመት ውስጥ ከያዛቸው ፕሮግራሞች መካከል አንዱ ህዝብ የተቀማቸውን መብቶች ማስመለስ መሆኑንና ይህም በተደጋጋሚ በተለያዩ ሚዲያዎች መገለጹን›› አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ ገልጸዋል፡፡

ሰላማዊ ሰልፉ እሁድ ሚያዚያ 19 ከቀኑ 4 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት ካሳንቺስ ከሚገኘው የፓርቲው ጽህፈት ቤት እስከ ጃን ሜዳ እንዲሆን የተወሰነ ሲሆን ጃን ሜዳ የተመረጠበት ምክንያትም መብቱን የተነጠቀውና ማህበራዊ አገልግሎቶችን በሚገባ ማግኘት ያልቻለው ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ጥያቄዎቹን እንዲያነሳ ሰፊ ቦታ በማስፈለጉ ነው ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በየ ክፍለ ከተማው የሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ተቋቁሞ ሰላማዊ ሰልፉን ለማድረግ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ የገለጹት ኃላፊው ‹‹በሀይል የተቀሙትን መብቶችን ለማስመለስ በሚደረገው ጥረት ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ማህበራት፣ ሚዲያውና እያንዳንዱ ዜጋ ተሳትፎ በማድረግ አገራዊ ግዴታውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Source: – ነገረ ኢትዮጵያ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on April 13, 2014
  • By:
  • Last Modified: April 13, 2014 @ 9:46 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar