www.maledatimes.com እስክንድር ነጋ እስርና ወከባ (ጫና) በግርማ አንድሪያስ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

እስክንድር ነጋ እስርና ወከባ (ጫና) በግርማ አንድሪያስ

By   /   April 13, 2014  /   Comments Off on እስክንድር ነጋ እስርና ወከባ (ጫና) በግርማ አንድሪያስ

    Print       Email
0 0
Read Time:12 Minute, 31 Second

እስክንድር ነጋ
እስርና ወከባ (ጫና)
በግርማ አንድሪያስ
(ኔዘርላንድ፡ ኣምስተርዳም)

”….ጋዜጠኞችና ኣስታሚዎች በጥብቅ መታሰርና በገንዘብ መቀጣት የጀመሩት የፕሬስ ኣዋጁ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ
ከወጣ ከሶስት ወር በኋላ ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ የካቲት 1984 በኢትዮጵያ አቆጣጠር። ታስረው በፕሬስ ህጉ
የተከሰሱና ለመጀመሪያ ጊዜ በፍርድ ቤት ተከራክረው ነጻ የወጡት፣ በመንግስት ባለቤትነት የሚተዳደረው የ ኣዲስ ዘመን
ጋዘጣ ኣዘጋጆች ናቸው። አዘጋጆቹ የታሰሩትና የተከሰሱት በጋዜጣው ላይ በኢትዮጵያ የዲሞክራሲን ጎጂና ጠቃሚ
ገጽታዎች የሚዳስስ ጽሑፍ በማውጣታቸው ነው።”

ይህን ያገኘሁት ተድባበ ጥላሁን (ዲማፅ) ”የኢትዮጵያ የግል ፕሬስ አድገትና ችግሮቹ” በሚል የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና
ስነ ጽሑፍ ክፍል አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 1990 ” ካቀረበው ጥናታዊ የመመረቂያ ጽሑፍ ያገኘሁት ነው።
በነጻው ፕሬስ ኣባላቶች ላይ ዱላውን ለማዝነብ የተሰራው የመጀመሪያ ድራማ ይህን ይምሰል አንጂ፣ በውቅቱ ድራማ
መሆኑን ያስተዋለው ኣልነበረም። እንዲያውም በዚያን ወቅት የ ” ኣዲስ ዘመን ጋዜጠኞች ካለምንም ቅድመ ሁኔታ
የመጻፍና የመናገር መብታቸው ይጠበቅ” በማለት የነጻው ፕሬስ ኣባላቶች ጮኽውላቸዋል። በወቅቱ መንግስት የራሱን
ሰዎች አንደሚፈታቸው ኣውቆ… የከተታቸው በመሆኑ፣ በሚጮሁት የነጻው ፕሬስ ውጤቶችና ኣባላቶች ላይ
ተሳልቆባቸዋል። ኣላግጦባቸዋልም። ታስረው የተፈቱት የመንግስቱ ልሳን ኣዘጋጆች የነበሩትም፣ የነጻው ፕሬስ ኣባላቶች
ላይ ብዕር ለመቀሰር ጊዜ ኣልወሰዱም።

በዚያን ጊዜ ከመጀመሪያዎቹ ሰለባዎች የነበረው… እስክንድር ነጋ ነበር። አስከኣሁንም መከራው ከላዩ ላይ ኣልወረደም።
ተድባበ ጥላሁን (ዲባጽ):- የብዙ ጋዜጠኞችን አንግልት ስቃይና ውጣ-ውረድ በግንባር አየቀረበ ጊዜ ወስዶ ባዘጋጀው
ጥናታዊ የመመረቂያ ጽሑፍ ”…ከዚህ በታች ባለፉት 6 ዓመታት ከ 22 ጊዜ በላይ የታሰረና የተፈታ፣ በዋና ኣዘጋጅነት፣
በአሳታሚነት የሰራና በኣሁኑ ውቅት በኣሳታሚነት የሚሰራ ጋዜጠኛ የደረሰበትን ለናሙናነት አንመልከት” ይላል
”HABESHA” የሚባለውን የእንግሊዝኛ ጋዜጣ በዋና ኣዘጋጅነት በኣስታሚነት አየሰራ፣ ”አበሻ” በሚል ስም
የአማርኛ ጋዜጣ ለማሳተም በዝግጅት ላይ አያለ ነበር ጥር ወር 1988።
ቃለ መጠይቅ እስክንድር ነጋ
”…ጠዋት አሰሩኝና ባዶ ቤት ኣስቀመጡኝ …ሌሊት ፮ ሰዓት ላይ በሩ ተንጓጓ፣ መብራቱ ጠፋ…. ኣንድ ሰው በብርድ
ልብሽ ተሸፋፈን ኣለኝ። ግን ላየው ኣልቻልኩም። ጭንቅላቴን በብርድ ልብስ ጠመጠመው… ትከሻየን ኣንጠለጠለና
ከክፍሉ ኣስወጣኝ። ኣቅጣጫውን ባላውቅም ፎቅ ላይ ወደ ኣንድ ክፍል ኣስገባኝ። የሌላ ሰው ድምጽ ይሰማኛል። ቁጭ
ኣደረጉኝና በመጀመሪያ አጄን የፊጥኝ በካቴና ኣሰሩኝ… ኣስተኙኝና በኮረንቲ ገመድ ይመስለኛል አግሬን ኣሰሩኝ። ብቻ
ኣንድ ሲስተም ነበር…በኋላ ብድግ ሲያደርጉኝ አግሬ ተነሳላቸው…ውስጡን በኣለንጋ መደበደብ ጀመሩ…ለስንት ጊዜ
አንደሆነ ኣይታወቅኝም በኋላ ኣቁመው ብድግ ኣድረጉኝ። ”አክችዋሊ” ሰውነቴ ኣይችልም ነበር…ሁዋላ ኣንጠልጥለው
ክፍል ጣሉኝ…ጠዋት ሃኪም መጣ። ከዛ አስካገግም ድረስ ወር ሙሉ ከምንም ዓይነት ሰው ጋር ሳልቀላቀል ሰው
ሳላይ…ከተሻለኝ በኋላ ፍርድ በት ወሰዱኝ። ፍርድ ቤቱ ሰውነቴ መጎዳቴን ኣይቶ ለቀቀኝ። በዚህም ጉዳይ ቃል
ኣልሰጠሁም። ክስም ኣልተመሰረተብኝም። ከዛ በኋላ ስራ ኣቆምኩ። ”

ከላይ ያነበብነው ከ 12 ጊዜ እስር በኋላ፣ ኣጥኚው እስክንድርን ቃለ መጠይቅ ኣድርጎት የተናገረው ነው… ይህ ሁሉ
በዚህ ወጣት ጋዜጠኛ ላይ የሆነው ከጅምሩ ነው። እስክንድር በራሱ ላይ ብዙ ጉዳቶች ደርሶበታል። ግን በግሉ
የሚደርስበትን ኣይናገርም። ይልቅስ በሃገሩ የሚደርሰው ስንዝር ጉዳት… ያመዋል። የወገኑ ሰቆቃ… ያናግረዋል።
ያጽፈዋል። ሌላ ዓላማ ያልነበረው አስክንድር ያልተናገረውን …ኣንድ ህመም እኔም ላክልበት።

ሰባ ደረጃ …
በነበረን ቢሮ እስክንድርም የራሱን ስራ እኔም የራሴን ስራ እሰራለሁ። ፍቃድ ኣውጥተን በግልጽ ከምንሰራው ስራ የተለየ
ኣጀንዳ ኣልነበረንም። እስክንድር ከዚህ በፊት በለቀቀው ጽሑፉ አንደገለጸው ሁሉም ነገር ጥድፊያ ነበር። አንዲያም
ተጣድፈን ሌሊቱ ኣይበቃንም ነበር። ስለዚህም ማደር የግድ ነው። የብዙዎቹ የነጻው ፕሬስ ውጤቶች ኮምፒውተር ስራ
አኔ ዘንድ ሲለሚሰሩ… ከእነዚሁ ውስጥ ኣንዱ የእስክንድር ጋዜጣ ነበር። ሃበሻ።
እስክንድር ከጎኔ ሆኖ ይጽፋል። እኔ ከስር-ከስር እስራለሁ። ከዚያም ሊነጋጋ ሲል ወደ ጠዋቱ …” አኔ እስክመጣ ይህቺን
ሰርተህ ጨርሳት፣ አርግጠኛ ነኛ ለማተሚያ ቤት እንደምንድረስ…”በማለት ስራዎቹን ትቶልኝ ሄደ። እስክንድር በዚያ
ጠዋት ሁሌም አንደሚያደርገው ‘ሰባ ደረጃ’ ን እላይና እታች ስፖርት ለመስራት ነው። የእስክንድር መዝናኛ
ከማንኛውም ሰው ጋር መወያየትና ስፖርት ነበርና። ነገር ግን እስክንድር የደከመባቸውን ስራዎች አኔ ብጨርስለትም
ማተሚያ ቤት ይዞ ለመሔድ ኣልታደለም። ስፖርት በሚሰራበት ሰባ ደረጃ ላይ አየደበደቡት ነበር።ያለ ብዕር ምንም
የሌለውን ጋዜጠኛ በስርዓቱ በተሰማሩና የኣጋዚ ሲቪል ለባሾች አጁን ሰባብረው፤ ሁለመናውን አንዳልነበረ ኣድርገው
ጣቢያ ነበር የጣሉት።

እስክንድር ግን ስለደረሰበት አንዲህ ያሉ ኢ-ሰብኣዊ በደሎች ቅድሚያ ሰጥቶ ሲያወራ ኣይደመጥም። የራሱ በሆኑት
የህትመት ውጤቶቹም ቢሆን ብሶቱን ሲያላዝን ኣይስተዋልም። ”ጅራፍ አራሱ ገርፎ አራሱ ይጮሃል” አንዲሉ… የፕሬስ
ኣዋጁ ከታወጀ ከ 1984 ጀምሮ እስክንድር ነጋ በገመድ ይታሰራል፣ በኤሌክትሪክ ገመድ ይታሰራል፣ በጭለማ
ይታሰራል፣ በብርሓን ይታሰራል፣ በብርድ ይታሰራል፣ በጸሓይ ይታሰራል። አስክንድር ግን… ኣይጮህም!…ያሰሩት
ይጮሃሉ… የሚገርፉት ያለቅሳሉ… ፊት ለፊት አየተራመዱ ይገላመጣሉ።ጥላቸውን ኣያምኑም። እንቅልፋቸው ህልም-
የለውም። የዶሮ እንቅልፍ ነው። ይሄን ጊዜ ታዲያ እስክንድርን ኣስታውሰዋለሁ። በተፈረደበት እስር ቤት ሆኖ፣ ያሰሩትን
በፈገግታ ሲመለከታቸው። በጭለማ ውስጥ ኣይደል ብርሓን መኖሩን የምንለየው? እስክንድር የሚያየው ጭላንጭል
ብርሓን ውስጥም…. ብዙ ነገር ኣለ። ትልቅ ሰላም።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on April 13, 2014
  • By:
  • Last Modified: April 13, 2014 @ 12:12 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar