www.maledatimes.com ሕወኃት /ኢህአዲግን/ ለማፍረስ የተጀመረውን ሕዝባዊ ሃይላችንን እናጠናክር! ለምን? ሐና ገለታ ከኖርዌይ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ሕወኃት /ኢህአዲግን/ ለማፍረስ የተጀመረውን ሕዝባዊ ሃይላችንን እናጠናክር! ለምን? ሐና ገለታ ከኖርዌይ

By   /   April 15, 2014  /   Comments Off on ሕወኃት /ኢህአዲግን/ ለማፍረስ የተጀመረውን ሕዝባዊ ሃይላችንን እናጠናክር! ለምን? ሐና ገለታ ከኖርዌይ

    Print       Email
0 0
Read Time:19 Minute, 14 Second

ኢትዮጵያ ባለፉት አመታት ጨካኝ አምባገንን መንግስትና የመንግስት ስርአቶች አስተናግዳለች::እነዚህም
ስርአቶችን ለማስወገድ ከፍተኛ መስዋትነት ተከፍሉል አሁንም እየተክፈለ ይገኛል:: አሁን ኢትዮጵያን
አስተዳድራለው የሚለው የወያኔ ቡድን ከሁሉም የባሰውንና በታሪኩ አይቶ የማያውቀውን ከፍተኛ ግፍ
በደል ጭቆናና ውርደት በሕዝቡ ላይ እያደረሠበት ይገኛል:: አምባገነኑና ፋሽስታዊው የወያኔ ቡድን
ላለፉት 22 አመታት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እጅግ በጣም አስከፊና ሁዋላ ቀር የህዝብን ጥቅም
የማያስጠብቅ ጭከናና ኢሰብኣዊ የአገዛዝ ስርአት በመጫን የስልጣን ዕድሜውን ማራዘም አገርን
ማፈራረስና የኢትዮጵያዊነትን ታሪክና ባህልን የማጥፋት ተልኮውን መፈጸም እና የህዝብን የሀገር ሀብት
መዝረፍ በስፋት እየፈጸመ ይገኛል:: ህዝቡን በጠብመንጃ በማስፈራራትና ከታች የተዘረዘሩትን ተፈጥሮዊና
ህገመንግስታዊ መብቶችን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በመከልከል የባንዳነት እኩይ ተግባሩን በመፈፅም ላይ
ይገኛል::

1. ኢትዮጵያውያንን በመከፋፈል በጋራ ችግሮችን እንዳንፈታ ማድረግ
ህዝቦችን በዘር በብሄር በቋንቋ በሀይማኖት በቀለም ብሎም ጎጠኝነትን በማስፋፋት እንዲለያዩ ማድረግና
ክፍተኛ የጥላቻ ፖለቲካ ቅስቀሳ በህዝቡ ዘንድ ማሰረጨት:: እርስ በእርስ እንዳይስማሙ አንድነት
እንዳይፈጥሩ ማህበራዊ ፖለቲካዊና እኮኖሚያዊ ችግሮቹ እንዳይፈቱ የሀገር ውስጥና የውጭ ጥላቶቹን
ለመታገል አቅምና ስምምነት እንዳያጎለብት በዘር ፖለቲካ እንዲወጠሩ ማድረግ ከአንዳንድ ብሄረሰብና
ሀይማኖተኞች ለግል ጥቅማቸው ያደሩትን ጥቂት ግለሰቦችን አቅፎ እምነትህ ባህልህ እና ጥቅምህ
ተከብሮልሀል ብሎ በህዝብ ላይ መሳለቅ::
2. የሰውን ልጅ ተፈጥሮዋዊና ህገመንግስተዊ መብቶችን መከልከል
በርካታ የህዝብን ተፈጥሮዊና ህገመንግስታዊ መብቶችን የመናገር የመፃፍ የመሰብሰብ በቡድን የመደራጀት
ሀሳብን በአደባባይ ወጥቶ የመግለጽ በሀገሩ ላይ የመሬት ባለቤት መሆን የፈለገውን እምነት መከተልና
የመሳሰሉትን በኢትዮጵያ ተፈፃሚ እንዳይሆኑ ማድረግ ወይንም በመሸራረፍና ለጥቂት የወያኔ አባላትና
ደጋፊዎች ብቻ ተፈፃሚነት እንዲሆን ማድረግ::

3. በሕብረተሰቡ ተቀባይነትና ተሰሚነት ያላቸውን ግለሰቦች ማጥፋት
ታዋቂና ለወደፊት ለአምባገነኑና ለፋሽስቱ ለወያኔ ቡድን የስልጣን ቆይታ አደገኛ ሊሆኑ ይችላሉ ብሎ
የሚያስባቸውንና በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትና ታማኝነት ያላቸውንና አላቸው ብሎ
የሚጠረጥራቸውን የተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎችን አባላቶችን ደጋፊዎችንና የደጋፊ ቤተሰቦችን ምሁሮችን
መምህራኖችን ጋዜጠኞችን ዘፋኞችን ነፃ አሳቢ ዜጎችንና በተለያዩ የዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ላይ
የሚሳተፉ ግለሰቦችን በአሸባሪነት በመፈረጅ በማስፈራራትና በእስር በማሰቃየት በአካልና በስነልቦና ላይ
ጉዳት ማድረስ ንብረትን መውረስ መዝረፍ ማውደም አስፈራርቶ ከሀገር እንዲሰደዱ ማድርግ የት
እንደደረሱ እንዳይታወቅ ማድረግ መግደልና ሌሎችንም የመሳሰሉ ወንጀሎችን በመፈፅም ሀገር የማፈራረስ
ህዝብንና ሀገርን የማዋረድና ማቆሚያ የሌለው ኢሰብአዊ የባንዳነትተልኮውን መወጣት::

4. ስለሰብአዊ መብት መልካም አስተዳደር እና የሕግ የበላይነት ግንዛቤ እንዳይኖረው ማድረግ
ለህዝብ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ለምሳሌ በሰብአዊ መብት በመልካም
አስተዳደር በህግ የበላይነትና የመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ መጥነኛም ሆነ ጥልቅ ግንዛቤ እንዳያገኝና እንዳይኖረው
ተግተው በመስራት ህዝቡ በዲሞክራሲያዊ ስርአቱ ግንባታ ላይ ምንም አይነት ተሳትፎ እንዳይኖረው
ማድረግ:: ስለ ሰብአዊ መብት መልካም አስተዳደር የህግ የበላይነትን ለህዝቡ በማስተማር ላይ
የተሰማሩትን መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ነፃ ጋዜጦች የራዲዮና የቴሌ ፕሮግራሞችን ሆን
ብሎ የተለያዩ አፋኝና ሰንካላ እንዲሁም የብዙሀኑን መብት የሚያቀጭጩ የጥቂት ቡድኖችን ስልጣን
የሚያፋፋ ህጎችንና መመሪያዎችን አውጥቶ ለህዝቡ እውነተኛ መረጃ እንዳይደርስ ማድረግ ህዝቡም
መብቶቹን እንዳያውቅና እንዳይጠቅም ማድረግ::

5. የሐገር ሐብትን ለባእዳን አሳልፎ መስጠት
የኢትዮጵያን ህዝብ የሀገር የመሬትና የንብረት አልባ አድርጎ የወያኔ አባላት ብቻ የመሬትና የንብረት ባለቤት
እንዲሆኑ ማድርግ:: ሀገርንና መሬትን ለባእዳን መሸጥና ለጎረቤት ሀገሮችም ትላልቅ መሬቶችን ቆርሶ
መሸጥና አሳልፎ መስጠት እኛ በቅርጽና በመጠን የምናውቃትን ታሪካዊ ኢትዮጵያን ማጥፋት ህዝቡም
በሀገሩ ላይ ስለ መሬት እንዳይጠይቅ በጠመንጃ ማስፈራራትና በሕዝብ ላይ ንቀቱን መግለፅ::

6. የሐገርን ባህልና ታሪክ ማጥፋት
የኢትዮጵያን የ 3000 አመት ታሪክ መካድ አሳፋሪ በሆነ መልኩ ማቅረብ ታሪክን መበረዝ የፈጠራ ታሪክ
መፍጠር የኢትዮጵያን ህዝብ ባህል ስብእና ዕምነት ኩራት ማንነት ብሄራዊ እሴቱን አንድነቱንና ብሄራዊ
መገለጫዎቹን ማጥፋት:: የኢትዮጵያን ታሪክ የወያኔን ታሪክ ብቻ አድርጎ በካድሬዎቹና ለጥቅማቸው ባደሩ
ተራ ግለሰቦች በገንዘብ እያማለለ ማፃፍ:: ልክ እንደ ውጭ ጠላቶች ኢትዮጵያዊነትን ማዋረድ ማጥላላት
ማናናቅና የመሳሰሉትን አስነዋሪ የቅጥረኝነቱን ተግባር እየፈፅመ ይገኛል::

7. የሙስና መስፋፋት በብሄርና በጎጥ የተደራጁ ጥቂት የወያኔ ማፊያዎች የሌብነት ተግባራቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ለማስፈፅም
ዘራፊ ድርጅት በማቋቋም ህዝቡንና ሀገሪቱን መዝረፍ በከፋ ሁኔታ ሕዝብን ማደህየት ለዘመናት ከኖሩበት
ስፍራ በማፈናቀል ለርሀብ መዳረግ የበዪ ተመልካች ማድረግ በዘመናዊ ቤት መኖር የብዙ ቤቶች ባለቤት
መሆን ዘመናዊ መኪናዎችን መቀያየር በመቶ ሚሊዮኖች የሚገመት ህንፃና ፋብሪካዎች መገንባት ለወያኔ
ብቻ የተፈቀደ እስኪመስል ድረስ ማግበስበስ:: በጣም በረቀቀና በአስከፊ ሁኔታ ከሀገርና ከህዝብ
የሚዘረፈውን ከፍተኛ ሀብት ከኢትዮጵያ ማሸሽና በተለያዩ የውጭ ሀገር ባንኮች መደበቅ ይህም ሳያንስ
በባእዳን ሀገር በቢሊየን የሚቆጥሩ ዶላሮችን አውጥቶ ህንፃ መገንባትን ሥራዬ ብለው ተያይዘውታል::

8. የሚዲያ አፈና
የኢትዮጵያ ህዝብ ትክክለኛ እውነተኛና ሚዛናዊ መረጃዎችን እንዳያገኝና በኢኮኖሚ በማህበራዊ በፖለቲካ
በዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ እንዳይሆን ማድረግ:: እኔ አውቅልሀለው የምነግርህን
ብቻ ተቀበል ብሎ ህዝብን በወያኔ የመረጃ ማሰራጫዎቹ ማደንቆር:: ትክክለኛ እውነተኛና ሚዛናዊ
መረጃዎችን ለህዝቡ የሚያደርሱትን የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የመረጃ ተቓማትን ማለትም የግል
ጋዜጣዎችን አታሚ ድርጅቶችን መዝጋት ፍቃድ መከልከል ባሰቤቶቹን መስፈራራት ማዋከብ መደብደብ
ማሰር ከሀገር እንዲሰደዱ ማድረግ እንዲሁም በሬዲዮ ቴሌቪዥን እና በድህረ ገዕች የሚሰራጩትን
መረጃዎች ከፍተኛ ገንዘብ በማውጣት ሞገዳቸውን ማፈን ::

9. ዘመነ ሌጋሲ
ከቀድሞ ጠ/ሚ በኃላ ለለውጥ ከመነሳሳት ይልቅ ሐገሪቱን የማፈራረስ እቅዳቸውን በከፍተኛ ሁኔታ የወያኔ
ጀሌዎች ተያይዘውታል በሰላማዊ እና በሰለጠነ መልኩ ለውጥ ፈላጊው የኢትዮጽያ ሕዝብ ጥያቄውን ይዞ
ቢነሳም ምላሹ ጥይት ማስፈራራት በእስር ቤት መታጎር አሰከፊ የሆነውን ጡንቻቸውንና የበላይነታቸውን
ማሳየት በከፍተኛ ሁኔታ ተያይዘውታል ለምሳሌ ሰማያዊ ፓርቲ በቅርቡ ያቀረባቸው ህገመንግስታዊ
ጥያቄዎችን ገዢው መንግስት ልክ ኣንደ አሸባሪ በመፈረጅ፤ ቢሮዋቸውን በወታደሮች በመዝረፍና የጠሩትን
ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በጠብመንጃ ኣስፈራርቶ በማስተጋጎል ኣምባገነንነቱን ኣስመስክሮዋል::
በመቀጠልም በአንድነት ፓርቲ ላይም ተመሳሳይ ድርጊት በመፈጸም ለማዳከም ኢሰብአዊ ድርጊቱን
ቀጥሎበታል:: ስለሆነም ወያኔ በጠመንጃ ስልጣን ላይ ከተቀመጠ ጀምሮ የኢትዮጵያ ህዝብ መብቶቹን
ለማስከበር ያላሰለሰ ትግል እያካሄደ ቢገኝም ወያኔ ሕዝቡን በጡንቻው እያስፈራራ ይገኛል ::ስለሆነም
እስከ አሁን የተደረገው የትግል መስዋትነት ብዙ ዋጋ ቢያስከፍለንም አሁንም የሚፈለገውን ድል
ለማምጣት የተለያዩ የትግል ስልቶችን በመጠቀም የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ድርጅቶች በጋራ ተቀራርቦ
በመስራት የፓርቲዎቹን አላማና የተለያዩ መረጃዎችን ሰብስቦ ወደ ህዝቡ ለማድረስ የሚያስችል ጠንካራ
ተቋም መፍጠር ይጠበቅብናል እንዲሁም አባላቶችና ደጋፊዎችን ማጠናከር አባላቶችና ደጋፊዎች
በገንዘብም ሆነ አስፈላጊ በሆነው ሁሉ ከፍተኛ ድጋፍ ማድረግ:: የወያኔን ዘረኛና ፋሽስታዊ የአገዛዝ ስርአት
ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ከስልጣን ለማስወገድ በመላው ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የእኩልነትና የፍትህ
ጥያቄዎች ከሁሉም አቅጣጫ እየጎረፈ ይገኛል:: ማንኛችንም የሀገሬ ሠላምና ደህንንት ይመለከተናል የምንል
ግለሰቦች የፖለቲካ ፓርቲ ድርጅት አባላትና ደጋፊዎች በጋራ ተሰባስበን የተቀጣጠለውንና እየተፋፋመ
የመጣውን ታላቅ የህዝብ አመፅ በሁለንተናዊ የትግል እስትራቴጂ እንዲታገዝ አድርጎ የወያኔን የማፊያ
ስርአት ከጫንቃችን ላይ አስወግደን እኩልነት ፍትህ ዲሞክራሲና እውነተኛ ፌደራላዊ ስርአት የሰፈነባት
ኢትዮጵያን ለመገንባት ከሌላው ግዜ በበለጠ መረባረብ ይጠበቅብናል:: የወያኔን ሀገር የማፍረስ የመዝረፍ
ታሪክን የማበላሸትና የማጥፋት ተልኮውን አሁን ተባብረን ለማስቆም የተጀመረውን ትግላችንን
እናጠናክር!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on April 15, 2014
  • By:
  • Last Modified: April 15, 2014 @ 3:49 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar