www.maledatimes.com የሚሊዎኖች ድምዕ ለመሬት ባለቤትነት - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  AFRICA  >  Current Article

የሚሊዎኖች ድምዕ ለመሬት ባለቤትነት

By   /   April 20, 2014  /   Comments Off on የሚሊዎኖች ድምዕ ለመሬት ባለቤትነት

    Print       Email
0 0
Read Time:7 Minute, 22 Second

የተከብራችሁ የአንድንት ለዲሞክራሲና ለፍትህ የድጋፍ ማህበር ዓባላትና ደጋፊዎች። እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ! የአንድነት የድጋፍ ማህበር በስዊድን ከኢትዮጽያ ድምዕ ራዲዎ ጋር በመተባበር ”የሚለዮኖች ድምዕ ለመሬት ባለቤትነት” በሚል መርሆ አንድነት ፓርቲ የጀመረው የቅስቀሳ ሥራ ..እንድትደግፉ ጥሪውን ያስተላልፋልunnamed

ውድ ኢትዮጲያኖች!
የድጋፍ ማህበራችን የአንድነት ፓርቲ የነደፈውን የትግል መስመር ለማገዝ ከስዊድን የኢትዮጵያ ራዲዎ ጋር በመተባበር የርዳታ ማሰባሰብያ ፕሮገራም ይጀምራል። አንድነት ፓርቲ በነደፈው ፕሮገራም መሰረት በሃገራችን ፍትህና ዲሞክራሲ እንዲኖር በከፍተኛ ደረጃ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ፓርቲው እስከዛሬ ያካሄደውን መራራ ትግል በመቀጠል በሰላማዊ ሰልፎች በአዳረሽ ሰብሰባዎችና አሁን ደግሞ በመላው ኢትዮጵያ “የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነት” በሚል መርሆው የሃገር አንድነት የህዝብ አኩልነትና ዲሞከራሲያዊነት በኢትዮጵያ እስኪረጋገጡና እስኪከበሩ ድረስ ህዝቡን ለትግል በማነሳሳት ላይ ይገኛል። የአንድነት የድጋፍ ማህበር በስዊድን ከማንኛውም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያኖች ጋር በመሆን በሃገራችን ሰላም ፍትህና ዲሞክራሲ ለማምጣት የሚታገል የሃገር ወዳድ ማህበር ነው። የድጋፍ ማህበራችን ለዚህ ዓላማ ከሚታገሉ ማህበራትና ተቁዋማት ጋር በመተባበር ሢሠራ የቆየ ማህበር እንደመሆኑ አሁንም የአንድነት ፓርቲ የሚለዮኖች ድምዕ ለመሬት ባለቤትነት በሚል መርሆ የጀመረውን እንቅስቃሴ ለመደገፍ ከስዊድን የኢትዮጵያ ሬድዮ ጋር በመተባበር ለመስራት ወስንዋል። ከሃገር እርቀን የምንኖር ኢትዮጵያውያን በትንሹ ልናደርግ የሚገባንና ልናደርግም የምንችለው በሃገር ውስጥ ለሚካሄደው ትግል የሞራልና የፋይናንስ ድጋፍ መስጠት ነው። አኛም በስዊድን የምንኖር ኢትዮጵያውያን ይህንን የተቀደሰ መርሆ ለመደገፍ የአንድነት የድጋፍ ማህበር ትግሉን ለመደገፍ በየወሩ መጨረሻ ቅዳሜ በሚያዘጋጀው የውይይት ቀን (የጌትቱጌዘር የውይይት መድረክ) በተለይ የሚለዮኖች ድምዕ ለመሬት ባለቤትነት መርሆንና ዓላማ የተጀመረውን ትግል ለማገዝ አፕሪል 26 ቀን 2014 ከ14፡00 ሰዓት ጀምሮ የርዳታ ማሰባሰብያ ፕሮገራም ይጀመራል። በሜይ 1 ቀን የዓለም ሰራተኞች ቀንም ከሚደረገው ሰላማዊ ሰለፍ መልስ ከ 1600 ሰዓት ጀምሮ የርዳታ ማሰባሰቢያ ዝግጅቱ ይቀጥላል። በሃገር ውስጥም ሆነ ከሃገር ውጪ የሚኖሩ ማንኛውም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የዚህ ትግል አካል ሊሆን ይገባል። በሃገራችን ለውጥ ለማምጣት የሁሉም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ተሳትፎ አሰፈላጊ ነው። የአንድነት የድጋፍ ማህበርና የስዊድን የኢትዮጵያ ራዲዮ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ በዚህ ቀን ሔገርሸቴን ቬገን 165 ቱነልባና አሰፑድን ወይንም ኦርንሽበሪ በሚገኘው አዳረሽ እንድትገኙና የፕሮግራሙ ተካፋይ እንድትሆኑ ባአክብሮት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። እርዳታችሁን በፖሰትጂሮ ለመክፈል ለምትፈልጉ የአድነት የድጋፍ ማህበር ፖሰትክጂሮ ቁጥር 399590-9 ወይንም በኢትኦጵያ ድምዕ ራዲዎ ፖሰትጂሮ ቁጥር 9251844-8 ማሰገባት የምትችሉ መሆኑን እያስታወቅን በገንዘብ ማስገቢያው ቅፅ መልክት መጻፊያ ቦታ ላይ ”milion vices” ብለው እንዲጠቅሱ በአክብሮት እናሳስባለን። በሚደረገው የርዳታ ማሰባሰብያ ፕሮገራም ቀናትም እጅግ ተደናቂ የሆነው የአቶ አንዱዓለም አራጌ መጽሃፍ *ያልተሄደበት መንገድ* የተባለው መጽሓፍ በሺያጭ ይቀርባል። መጽሃፉን በቀድሚያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0737885587 ቢደውሉ ለማግኘት ይችላሉ።
ከሰላምታ ጋር
የአንድነት የድጋፍ ማህበርና የስዊድን የኢትዮጵያ ራዲዮ

About Post Author

Abby

Internet reporter, freelancer and webmaster.
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on April 20, 2014
  • By:
  • Last Modified: April 20, 2014 @ 1:52 pm
  • Filed Under: AFRICA

About the author

Internet reporter, freelancer and webmaster.

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Traveler’s Alleged Crimes and Robbery at Bole Airport Raise Concerns

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar