www.maledatimes.com ሁለት የደህንነት መስሪያ ቤት የበታች ሃላፊዎች በጓዶች ስብሰባ ላይ ተገደሉ። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  AFRICA  >  Current Article

ሁለት የደህንነት መስሪያ ቤት የበታች ሃላፊዎች በጓዶች ስብሰባ ላይ ተገደሉ።

By   /   July 27, 2014  /   Comments Off on ሁለት የደህንነት መስሪያ ቤት የበታች ሃላፊዎች በጓዶች ስብሰባ ላይ ተገደሉ።

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 11 Second
 (ምንሊክ ሳልሳዊ)
ባለፈው ማክሰኞ ከምሽት ጀምሮ ቦሌ መስመር ወሎ ሰፈር ከአይቤክ ሆቴል ፊትለፊት ገባ ብሎ ከሚገኘው የደህንነት ቢሮ ውስጥ በተደረገ ስብሰባ ላይ በተፈጠረ የፖለቲካ አለመግባባት ከአቶ ኢሳያስ ወ/ጊ ጠባቂዎች በተተኮሱ ጥይቶች ሁለት ከአማራው ክልል በመጡ የደህንነት የበታች ሃላፊዎች ላይ ግድያ መፈጸሙን ታውቋል።

በአማራው ክልል ያሉ እና በህግ በተመዘገቡ ፓርቲዎች ሽፋን የህገወጥ ዲያስፖራ ፓርቲዎችን አላማ የሚያራምዱ የተቃዋሚ አመራሮች ላይ ከምርጫው ቀደም ብሎ ሊወሰድ ስለሚገባው እርምጃ ለመወያየት የተሰበሰበው የደህንነት ጓድ በስብሰባው ወቅት ከፍተኛ አለመግባባት ፈጥሮ እንደነበር የታወቀ ሲሆን በወቅቱም ከአዲስ አበባ ከ13 አመት በፊት ተመልምለው ወደ አማራው ክልል የተላኩት በክልሉ ምስጢራዊ የሆኑ የግድያ እና የአፈና እንዲሁም የስለላ መመሪያዎችን በመቀበል ለጽጥታ ሃይሎች በማስተላለፍ ሲያስፈጽሙ እና ሲፈጽሙየነበሩ እና በደህንነት ኮድ ስማቸው (አለልኝ እና ብቸናው) የተባሉ የደህንነት የበታች ሹሞች እዛው ስብሰባው መሃል በጸጸት እና በብሶት በቁጣ የተሞላ ጠንካራ ጥያቄዎች በማቅረባቸው በተፈጠረ አለመግባባት የማያዳግም እርምጃ እንደተወሰደባቸው ታውቋል።

የሕወሓት የደህንነት ከፍተኛ ሹሞች ምን ያህል በጥጋብ እና በትእቢት እንደተወጠሩ የሚያመለክተው ይህ ግድያ በስብሰባው ላይ ያሉትን የደህንነት ጓዶች ለማሸበር እና ለመጪው ምንም አይንት ጥያቄ እንዳያነሱ እና አለመግባባት እንዳይፈጥሩ ለማስደንገጥ የተደረገ እንደሆነ በግልጽ ያሳያል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሰራዊቱ ውስጥ እና በደህንነት ተቋማት ውስጥ ያሉ አገልጋዮች ጥያቄዎችን እያነሱ ሲሆን እንዲሁም ከአገር በሚወጡበት አጋጣሚ ሁሉ ወደ ሃገር ቤት እንደማይመለሱ ታውቋል። ባለፈው አመት ለደህንነት ትምህርት ወደ እስራኤል ከተላኩ 67 ጓዶች ውስጥ 23 ወዴት እንደጠፉ የማይታወቅ መሆኑን መረጃውን ያደረሱን ምንጮቻችን ገልጸውልናል።
ይህ በ እንዲህ እንዳለ ለግንቦት ሰባት ለአንድነት ፓርቲ እና ለወያኔ በጋራ እየሰሩ ተቃዋሚዎችን እያሳለፉ የሚሰጡ የተቃዋሚ አመራሮችን በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎች እየተዘግጁ ስለሆነ በቅርብ ጊዜ ይፋ አደርገዋለሁ።#ምንሊክሳልሳዊ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on July 27, 2014
  • By:
  • Last Modified: July 27, 2014 @ 5:51 am
  • Filed Under: AFRICA

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Traveler’s Alleged Crimes and Robbery at Bole Airport Raise Concerns

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar