www.maledatimes.com ሰማያዊና ቴዲ አፍሮ የስልጠናው የልማታዊ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ትግላችንንን ፈተናዎቹ አጀንዳ ሆነዋል (ሰነዱን ይመልከቱት) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ሰማያዊና ቴዲ አፍሮ የስልጠናው የልማታዊ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ትግላችንንን ፈተናዎቹ አጀንዳ ሆነዋል (ሰነዱን ይመልከቱት)

By   /   August 29, 2014  /   Comments Off on ሰማያዊና ቴዲ አፍሮ የስልጠናው የልማታዊ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ትግላችንንን ፈተናዎቹ አጀንዳ ሆነዋል (ሰነዱን ይመልከቱት)

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 47 Second

ሰማያዊና ቴዲ አፍሮ የስልጠናው የልማታዊ ዲሞክራሲያዊ ስራት ግንባታ ትግላችንንን ፈተናዎቹ አጀንዳ ሆነዋል
#Ethiopia #university #blueparty #tedyafro #eprdf #MinilikSalsawi

ሰማያዊ ፓርቲ እና የቴዲአፍሮ ጥቁር ሰው አልበም በወያኔ ተብጠልጥለው ተወንጅለዋል።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
‹‹ኢህአዴግ ራሱ በአኖሌ ስም እየነገደ ለእሱ የሚቀርቡት አካላት ከእነ ቴዲ አፍሮና ሰማያዊ ፓርቲ ጋር አላትሞ መውቀሱ የሚያስገርምና ውይይት ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ያስነሳ ነው›› የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ጥቁር ሰው አልበም በስልጠና ሰነዱ ላይ ለአክራሪነት ምሳሌ ተደርጎ የቀረበ ሲሆን ተማሪዎችም ቴዲ አፍሮ ለአገር አንድነት የቆመ መሆኑን በመግለጽ መከራከራቸውን ገልጸውልናል፡፡
Image
በኢህአዴግ ጽ/ቤትና በትምህርት ሚኒስትር ትብብር ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እየተሰጠ ባለው ስልጠና ሰማያዊ ፓርቲና ቴዲ አፍሮ አጀንዳ መሆናቸውን ሰልጣኞች ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ‹‹የልማታዊ ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ትግላችንና ፈተናዎቹ›› በሚለውና በአሁኑ ወቅት ከአዲስ አበባ ውጭ በየ ክልሉ እየሰለጠኑ ለሚገኙት ተማሪዎች እየተሰጠ ባለው ስልጠና ሰማያዊ ፓርቲና ቴዲ አፍሮ ለልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባታ ፈተናዎች ተብለው ቀርበዋል፡፡ አሰልጣኞቹ ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹መንግስት የእምነት ነጻነት ያክብር!›› እያለ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች በአክራሪነት የፈረጀ ሲሆን ቴዲ አፍሮም ‹‹ጥቁር ሰው›› በሚል ለህዝብ ያደረሰው አልበም ተመሳሳይ ውንጀላ ቆርቦበታል ሲሉ ሰልጣኞቹ ገልጸዋል፡፡

ሰማያዊና ቴዲ አፍሮ በተለይ በውይይት ወቅት ከአሰልጣኞቹ ሰፋ ያለ ወቀሳና ውንጀላ እንደደረሰባቸው ሰልጣኞቹ ገልጸዋል፡፡ ተማሪዎቹ በበኩላቸው ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ እንደ አንድ ለህዝብ እንደቆመ ፓርቲ መንግስት በእምነት ጣልቃ እንዳይገባ መጠየቅና መታገል መብቱ ብቻ ሳይሆን ግዴታው ነው፡፡›› ብለው እንደተከራከሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ጥቁር ሰው አልበም በስልጠና ሰነዱ ላይ ለአክራሪነት ምሳሌ ተደርጎ የቀረበ ሲሆን ተማሪዎችም ቴዲ አፍሮ ለአገር አንድነት የቆመ መሆኑን በመግለጽ መከራከራቸውን ገልጸውልናል፡፡ ተማሪዎቹ አክለውም ‹‹ጥቁር ሰው የሚለው ተወዳጅ ዘፈን በገዥው ፓርቲ ቁጥጥር ስር ከሚገኙት ውጭ በአብዛኛዎቹ ሚዲያዎች በስፋት ይለቀቃል፡፡በስልጠናው እያየነው እንዳለነው ግን ገዥው ፓርቲ ቴዲ አፍሮን ብቻ ሳይሆን ሚዲያዎቹንም በአክራሪነት እየከሰሰ መሆኑ አሳዛኝ ነው፡፡›› ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ አስተያየታቸውን ገልጸዋል፡፡
Image
በሰነዱ ‹‹ጠባብና ትምክተኛ ተብለው የተፈረጁ ኃይሎች ተመጋጋቢ ናቸው›› ተብለው የቀረቡ ሲሆን ‹‹የትምክት አስተሳሰብ የተጠናወተው ሚዲያ ‹‹ጥቁር ሰው›› በሚል ዘፈን ሚኒሊክን ሲያሞካሽ በጠባብነት የተለከፈው ሚዲያ የአኖሌን ግፍ ህዝብን ለመለያየት ይጠቀምበታል›› ሲል ሁለቱንም በጅምላ ይወቅሳል፡፡ ይህን ስልጠና እየወሰዱ ያሉ ተማሪዎች ‹‹ኢህአዴግ ራሱ በአኖሌ ስም እየነገደ ለእሱ የሚቀርቡት አካላት ከእነ ቴዲ አፍሮና ሰማያዊ ፓርቲ ጋር አላትሞ መውቀሱ የሚያስገርምና ውይይት ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ያስነሳ ነው›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ‹‹እራሱ ህዝብን በተለያዩ መንገዶች ህዝብን እየነጣጠለና የከፋፍለህ ግዛ ስርዓት አስፍኖ በኢትዮጵያ አንድነት የሚያምኑትን አካላት በማይገባቸው ክስ መክሰሱ የዪኒቨርሲቲ ተማሪዎች አላዋቂ አድርጎ መውሰዱንና ንቀቱን የሚያሳይ ነው፡፡›› ብለዋል፡፡ ሰልጣኝ ተማሪዎች የላኩልንን የሰነዱን አካል እንደሚከተለው አያይዘነዋል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on August 29, 2014
  • By:
  • Last Modified: August 29, 2014 @ 9:12 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar