www.maledatimes.com ነጻነትን በማሳጣት ዜጎችን ለስቃይ፣ለእስራትና ለስደት የዳረገውን መንግስት ልናስወግደው ይገባል - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ነጻነትን በማሳጣት ዜጎችን ለስቃይ፣ለእስራትና ለስደት የዳረገውን መንግስት ልናስወግደው ይገባል

By   /   August 29, 2014  /   Comments Off on ነጻነትን በማሳጣት ዜጎችን ለስቃይ፣ለእስራትና ለስደት የዳረገውን መንግስት ልናስወግደው ይገባል

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 14 Second

Gezahegn Abebe (ገዛኸኝ አበበበ ከኖርዌ ሌና)
Imageወያኔ ኢህአዲግ የስልጣን ወንበሩን በሀይል ከተቆናጠጠበት ጊዜ ጀምሮ በስልጣን በቆየባቸው በሃያ ሶስት አመታቶች በየጊዜው በህዝባችን ላይ የሚያደርሰው ግፍ እና ጭቆና ከእለት ወደ እለት እየጨመረ መምጣቱ በአደባባይ የሚታይ እውነታ ሲሆን ከዚህም ጨቋኝና ገዳይ ስርዓት የተነሳ የሀገሪቷ ዚጓች በሀገራቸው ላይ በሰላም መኖርና የነጻነትን ሀየር መተንፈስ በማይችሉበት ክፉ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ::ለሰው ልጅ ነጻነቱ እየተገፈፈና መብቱ እየተረገጠ እንደ መኖርን የመሰለ አስቀያሚ ህይወት ያለ አይመስለኝም::ስለዚህ ነው በአሁኑ ጊዜ ከማንኛውም ጊዜ በተለየ መልኩ በሀገራችን ኢትዮጵያ ገበሬው፣ ተማሪው፣ ፣ አስተማሪው ፣ ነጋዲው፣ ጋዜጠኛው ፣ ስፖርተኛው፣ ዘፋኙ፣ አርቲስቱ፣ ወዘተ……በማንኛውም እርከን ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በሀገራቸው ላይ በነጻነት መኖርን ስላልቻሉ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ሀገራቸውን ትተው እየወጡ በየጊዜው ለስደት ሲዳረጉ የሚታዩት::

ከሰሞኑ እንኳን እንደተመለከትነው አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ ይገኙ የነበሩ ቁጥራቸው አስራ ሁለት የሚሆኑ ጋዜጠኞች የወያኔ መንግስት ስራቸውን እንደ ሚገባ እንዳይሰሩና በነጻነት አላንቀሳቅስ ስላላቸው ሀገራቸውን ጥለው ለስደት እንደተዳረጉ ሁላችንም የተመለከትነው ነገር ነው በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ቁጥራቸ ቡዙ የሆኑ ጋዜጠኞች በአንድ ጊዜ ውስጥ ሀገራቸውን ጥለው ለስደት መዳረጋቸው ቡዞዎቻችንን የሚያስገርምና የሚያስደነግጥ ክስተት ሊሆን ይችላል ነገር ግን ለሰዎች ሁሉ የስደት ምንጭ የሆነው የወያኔ መንግስት ከስልጣኑ እስካልተወገደ ድረስ አፈና፣ እስራት፣ግድያው ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ በየትኛውም እርከን ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች መቺም ቢሆን ለስደት መዳረጋቸው የማይቀር እውነታ ነው :.

ሌላው አንድ የታዘብኩት ነገር ሀገራቸውን ጥለው ለስደት ስለተዳረጉ ስለእነዚህ ጋዜጠኞች በተለያዩ ሰዎች የተጻፉትን ጹሁፉችን ተመልክቻለው አንዳንድ ሰዎችም የእነዚህ ጋዜጠኞች ከሀገር ለቁ መወጣት ስላልተዋጠላቸው የተለያዩ ትችቱችንና አስተያየቶችን ሲጽፉና ሲሰጡ ተመልክቻለው መቼም ቢሆን ማንኛውም ሰው በሀገሩ ላይ መማርን ፣መስራትንና፣ መኖርን የሚጠላ ሰው ያለ አይመስለኝም :: እነዚህን ጋዜጠኞች ከሌሎች ጋዚጠኞች ጋር እያነጻጸሩ ለምን እንደ እገሌ እዛው ሀገር ቤት ቁጭ ብለው አልታሰሩም ነበር ብሎ መፍረድ አግባብነት ያለው ፍርድ አይመስለኝም :: ማንም ሰው በሀገሩ በነጻነትና በሰላም መኖር ቢሆንለት ስደትን አይፈልግም :: ምክንያቱም ዜጓች በሀገራቸው በተረጋጋ ሁኔታ ለመኑር የሚያስፈልጋቸው ዋንኛውና ቁልፉ ነገር ሰላም እና ነጻነት ነውና::ማንኛውም ሰው በሚኖርበት ሀገር በሚኖርበት ሰፈር ወይም አካባቢ እና በሚኖርበት ቤት ውስጥ ሳይቀር በሰላምና በነጻነት መኖርን ይፈልጋል:: ነጻነት በምንም ዋጋ ሊተመን የማይችል ትልቅ ጸጋ ነውና:: ሰላም እና ነጻነት በሌለበት ሀገር የሚኖሩ ዜጓች፣ መብታቸው ይረገጣል ፣ ነጻነታቸው ይታፈናል ዜጓች ለእስር፣ ለሞት፣ እና ለስደት ይደጋሉ::በሀገራችን ኢትዮጵያ የምናየውም በእነዚህ አስራ ሁለት ጋዜጠኞች ላይ የደረሰው ይሄው ነው::

እንደ አለመታደል ሆኖ ሀገራችን ኢትዮጵያም በአለም ላይ ካሉት ሀገራት በግንባር ቀደምነት የሰው ልጆች ነጻነታቸውን እና መብታቸውን ከሚገፈፉበት ሀገር ተርታ እንደምትገኝና የሀገሪቷ ዜጓች በጨቋኙ ገዥ ስርዓት ነጻነታቸውን ተገፈው ባሪያ ሆነው የሚኖሩበት ሀገር እንደሆነች በየጊዜው ከሚወጡ አለም አቀፍ ሪፖርቶች መረዳት ይቻላል::::

ዜጓች በከፍተኛ ሁኔታ ለስደት እየተዳረጉ ባሉበት በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚደረገው አፈና፣ እስራት እና ግድያው በከፍተኛ ሁኔታ ተባብሶ የሚገኝ ሲሆን ይህም በገሃድ እየታየ ያለ እውነታ ነው :: በእነዚህ ሃያ ሶስት አመታቶች በፋሺስቱ የወያኔ ቡድን ነጻነቱ እየተገፈፈና መብቱ እየተረገጠ ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብም ከእንግዲህ ወዲህ ይሂን የወረበሎች ቡድን እሽሩሩ እያሉ የመኖር አቅም ያለው አይመሰልም :.: በአሁኑ ጊዜ ከየአቅጣጫው ከሚሰሙ ነጻነት ናፋቂ የኢትዮጵያኖቸ ሕዝብ ጩኸት ድምጽ መረዳት እንደሚቻለው ሕዝባችን ለወያኔያዊ አንባገነን ስርዓት መገዛትን የጠላበትና ከመቺውም ጊዜ በተለየ መልኩ እምቢ አሻፈረኝ ብሎ ነጻነቱን ለማስመለስ በአንድነት ለመቋም የተነሳበት ዘመን ላይ የደረሰን በሚያስመስል መልኩ ከየቦታው የሚሰማው የነጻነትና የሰላም ናፋቂዎች የጀግንነት ድምጽ ምስክር ነው::

በቅርቡ እንኳን እንደምናየው የግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ጸሀፊ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ከየመን ታግተው በወያኔ እስር ቤት ታስረው በግፍ እየተሰቃዩ እንዳለ ይታወቃል የነጻነት ታጋዩ አቶ አንዳርጋቸው በወያኔ ሴራ ከየመን ታግተው በወያኔ እጅ ላይ መውደቃቸው ከተሰማ ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ የወያኔን አውሬነት በይበልጥ በመረዳት ከዳር እስከ ዳር በአንድነት መቋሙን እያስመሰከረ ሲገኝ የፖለቲካ ግለቱም ጨምሮ የአረመኔው የወያኔን ቡድን በከፍተኛ ሁኔታ አርበድብዶት እንደሚገኝ ወያኔ ከሚሰራው ስራና ከሚያደርጋቸው ድርጊቷች ማወቅ ይቻላል::የአቶ አንዳርጋቸውን መታሰር ተከትሎ እየከረረ ያለውን የሕዝብን ቁጭትና ቁጣ ለማጥፋት በሚያስመስል መልኩ ይኼ አረመኔው መንግስት በአሁኑ ጊዜ በሀገር ቤት በሰላማዊ መንገድ ለመብታቸው እና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነት በህጋዊ መንገድ እንኮን ሳይቀር እየታገሉ ያሉትን ሰዎች ከየመንገዱ እየለቀመ እስር ቤት አስገብቶ እያሰቃያቸው እንዳለ ይታወቃል ::ይህንንም ተከትሎ ሁላችንም እንደምናውቀው የአንድነት ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባልና ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ የፓርቲው ምክር ቤት አባል አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ የአረና የሕዝብ ግንኙንት ኃላፊ አቶ አብረሃ ደስታና የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ አቶ የሸዋስ አሰፋን ጨምሮ ሌሎችም እጅግ ብዙ ለየጻነታቸው የሚታገሉ ኢትዮጵያን ወገኖቻችን የወያኔ መንግስት በግፍ አስሯቸው እያሰቃያቸው እንደሚገኝ ይታወቃል::

ይኼ መንግስት እሱን የሚቃወሙትን ሰዎችንና በድፍረት እየተጋፈጡት ያሉትን የፖለቲካ መሪዎች አአሸባሪ የሚል የታርጋ ስም እየለጠፈላቸው ወደ እስር ቤት መወርወር የተጠናወጠው ክፉ ባህሪው ሆኖል:: የፖለቲካ መሪዎችንና የፖለቲካ ሰዎችን ማፈንና እየያዙ ወደ እስር ቤት መወርወር ይበልጥኑ ትግሉን እያከረረውና የኢትዮጵያን ሕዝብ ይበልጥኑ ለነጻነቱ በመታገል ለድል እያነሳሳው ነው እንጂ ፈጽሞ ከትግል ወደ ኋላ እይመለሰው እንዳይደለ የወያኔ ባለስልጣኖች ጠንቅቀው ሊያውቁት የሚገባቸው ነገር ይመስለኛል:: የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነትን ተጠምቷል ::Freedom is more than food በአሁኑ ሰአት በሀገር ቤትም ሆነው በሰላማዊ መንገድ እየታገሉ ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ይሁኑ ወይም በውጭ ሆነው በሁለገብ ትግል እየታገሉ ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች አላማቸውም ሆነ ጥያቄያቸው አንድ ነው የስልጣን ወይም የገንዘብ ሳይሆን የነጻነት ጥያቄ ነው :: የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነት ያስፈልገዋል ::እኛም ሰላምና ነጻነት የናፈቀን ህዝቦች መብታችንን ለማስከበር ለነጻነት ከሚታገሉ ድርጅቷች ጎን በመቆም ለነጻነታቸው ሲታገሉ በወያኔ አንባገነን ትህዛዝ ወደ እስር እየተወረወሩ እና በግፍ እየተሰቃዩ ላሉ ወገኖቻችን ከመንኛውም ጊዜ በተለየ መልኩ ሀገራዊ ስሜት ተሰሞቶን ልንጮህላቸውና የእነሱንም ፈለግ በመከተል ከሁለት አስርት አመታት በላይ የዜግነት መብታችንና እየረገጠና ነጻነታችንን እያፈነ ህዝባችንን ለስደት እያደረገ ያለውን ያለውን ይኼን ሰይጣናዊና አረመናዊ ስርዓት በማንኛውም መንገድ በመታገል፣እውነተኛ ሰላምና ነጻነት በኢትዮጵያ ምድራችን እንዲመጣ ለማድረግ የወያኔን መንግስት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ዳግም እንዳይነሳ አከርካሪውን ሰብሮ መጣል ይጠበቅብናል እላለው::የዜጎች ነጻነት ማጣት ፣መሰቃየት፣ መታሰርና መሰደድ ግድ ብሎን እያንዳንዳችን ትግላችንም ሆነ አላማችን በእውነተኛ የነጻነት ትግል በመነሳት የወያኔን መንግስት ጥሎ ነጻነትን ለመቀናጀት በኢትዮጵያዊ ስሜትና ተነሳሽነት ከሆነ ድልን የምንቀድጅበት ቀን ሩቅ መስሎ አይታየኝም::

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!
gezapower@gmail.com

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on August 29, 2014
  • By:
  • Last Modified: August 29, 2014 @ 9:17 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar