www.maledatimes.com መገናሳ ጎረቤቴ! ሙንትሃ ሸረፋ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

መገናሳ ጎረቤቴ! ሙንትሃ ሸረፋ

By   /   August 29, 2014  /   Comments Off on መገናሳ ጎረቤቴ! ሙንትሃ ሸረፋ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 28 Second
ሙንትሃ ሸረፋ


___________________

መገናሳ ጎረቤቴ ነው። የሀብታም ልጅና በእውቀት የታጨቀ አህምሮ ነበረው። የዚያ እውቀቱ የመጨረሻ ውጤት ግን አሳበደውና መገኛው አማኑኤል ሆስፒታል ሆነ።

መገናሳ አንድ ጊዜ ጥርሱን እስኪደክመው ጫት ቃመ። ሳንባው እስኪነካ ድረስ ሲጋራ አጨሰ ። አስካሪ መጠጥ ቂጡን ደፍኖ ጠጣ(ሞልቶ እንዳይፈስ)። ግን አንድ ቀን ሰክሮ ተወላግዶና ወድቆ አያውቅም።

መገናሳ ከቤተሰቡ ጋር ነው የሚኖረው። ታዲያ ሁል ጊዜ ቤቱ የሚደርሰው ለሊት ስለሆነ በር ከማንኳኳት ብሎ የግንቡን አጥር ዘሎ ነው ወደጊቢው የሚገባው። ታዲያ ዘወትር በግንቡ አጥር ወደቤቱ ዘሎ ከመግባቱ በፊት ያስለመደው አንድ ልምድ አለ። የመጨረሻውን የሚያጨሰውን ሲጋራ የግንቡ አጥር ጫፍ ላይ ሆኖ ያጨሰዋል። ከዚያም ተጭሳ ያለቀችውን ሲጋራ ወደ ውጪ ጥሎ እሱ ደግሞ ወደቤቱ ጊቢ ውስጥ ይወድቃል። ይቺ ልምዱን ሁልጊዜ ነው የሚተገብራት። ሲያደርገው እርካታ የሚያገኝበት ልምድ። ካላደረገው ቅር ቅር ይለዋል!!

አንድ ጊዜ ግን ቀኑን ሙሉ ኃይለኛ ጫት ሲቅም ነበር የዋለው። መጠጡንም ከልኩ በላይ ጠጥቶ ሰክሮ ነበር። ከዚያም እንደምንም ብሎ የጊቢያቸው የግንብ አጥር ጫፍ ላይ ወጣ። እንደለመደውም የግንቡ ጫፍ ላይ ሆኖ የመጨረሻውን ሲጋራ አጣጥሞ አጨሰ። ሲጋራውን ካጨሰ በኋላ ግን ሁልጊዜ እንደሚያደርገው ያጨሳትን ሲጋራ ወደ ውጪ ጥሎ እሱ ደግሞ ወደ ግቢው አልገባም። የሆነው ነገር ፍፁም ተቃራኒ ነበር። መጨረሻ ያጨሳትን ሲጋራ ወደ ጊቢው ውስጥ ጥሎ እሱ ደግሞ ወደውጪ ወደቀ!!

እኔም ጧት ወደስራ ለመሄድ ከቤት ስወጣ መገናሳ ከአጥሩ አጠገብ ባለው ትቦ ስር ዘና ለጠጥ ብሎ ለሽሽሽ ብሏል።

እኔም “መገናሳ” ብዬ ልቀሰቅሰው ብል አይኑን እንደጨፈነ “ብርድ ልብስ ለምንድነው ያላለበሳችሁኝ? አንተ አሁን ወንድሜ ነህ!? ደመኛዬ ነህ!! የማትረባ ነህ እሺ!!” ይለኛል።እኔም በንግግሩ በሆዴ እየሳቅሁኝ “መገናሳ እኔ ወንድምህ አይደለሁም። ጎረቤትህ ነኝ። አሁን እኮ ያለኸው ቤት ውስጥ ሳይሆን ትቦ ውስጥ ነው” ብዬ ጉዶን አረዳሁት። እሱ ሆዬ ገና ስካሩ አለቀቀውም መሰለኝ በስካር ስሜት ውስጥ ሆኖ “በቃህ! አሁን ጆሮዬ ላይ አትለፍልፍብኝ። በጣም ነው የበረደኝ ስለዚህ የአባቢን ብርድልብስ ደርበህ አልብሰኝና የመኝታ ክፍሌን በር ዘግተህ ውጣልኝ!!!!” ብሎ ጮኸብኝ።

እኔም ለቤታቸው ሰራተኛ ትቦ ውስጥ ለተኛው መገናሳ ብርድ ልብስ እንድትደርብለት ነግሬያት ወደስራዬ ሄድኩኝ።

“ከመጠጥ ደስታ ይገኛል ብላችሁ
መጠን አትለፉ ትቃጠላላችሁ” lol

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on August 29, 2014
  • By:
  • Last Modified: August 29, 2014 @ 11:42 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar