www.maledatimes.com መራር ናፍቆት!! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

መራር ናፍቆት!!

By   /   August 29, 2014  /   Comments Off on መራር ናፍቆት!!

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 8 Second
ሙንትሃ ሸረፋ


_________________

በጣም ነው የምወዳት ከህይወቴ አስበልጬ!! የእኔ እስትንፋስ መኖሮና እንደሰው ቆሞ መንቀሳቀስ የእሷ ታላቅ አስተዋፅኦ አለበት። ያለሷ ህይወቴ ባዶ ነበር የሚሆነው ። የመኖርን ትርጉም ያወቅሁት በሷ ነው። አንድ ጊዜ በትንታ ከመሞት አድናኛለች። ስቆሽሽ አጥባ አፅዳታኛለች። የደረቀ ከንፈሬን አለስልሳልኛለች። ከፈጣሪ ቀጥሎ የእሷ መኖር ለእኔ ግድ ነው። ህይወቴ ላይ የመወሰን ሙሉ መብት አላት!!

አሁን ግን ከአጠገቤ ከተሰወረች ይኸው ወራቶች ተቆጠሩ። ብዙ ቦታ ፈለግኳት የለችም። የአዲስ አበባ ሰፈር፣ቅያስ፣መንደር፣ጉራንጉር፣ ሻይ ቤት፣ስጋ ቤት፣ትልልቅ ሆቴል፣በመንግስት መስሪያ ቤት፣በግል መስሪያ ቤት………ያልፈለግኳት ቦታ የለም። ፈልጌ አስፈልጌ አጣኋት። ለብዙ “ቁልፍ” ለሚባሉ ሰዎች ራሱ ፈልገው ያመጡልኝ ዘንድ ጉቦ ሰጥቼ ነበር። ግን ይኸው የበላት ጅብ አልጮህ አለ።

አሁንስ በጣም ናፍቃኛለች። ምንም ነገር እንደዚህ ናፍቄ አላውቅም። እንድበላው የቀረበልኝን ምግብ ከጉሮሮዬ አልወርድ እያለ አንድም ጉርሻ ሳልጎርስ እመልሰዋለው። ይኸው እሷን ብቻ እያሰብኩኝ እራሴን ጥያለው። እሷ ከጠፋች ጀምሮ አካላቴን አንፅቼ አላውቅም። እሷ ከጠፋች ጀምሮ የለበስኩትን ልብስ ሰውነቴ ላይ እንደተሰፋ ሁሉ አልቀየርኩትም። ቆሻሻውና እድፉ ሰው በሩቁ እንዲሸሸኝና እንዲፀየፈኝ ያደርጋል።

ለወራት በመጥፋቷ ምክንያት ነው መሰለኝ እንደምወዳትና እንደምናፍቃት ታወቀኝ፣ተገለጠልኝ!! ማንንም በህይወቴ እንደሷ ናፍቄ አላውቅም። ማንንም!!
:
:
:
:
:
:
ውሃ!!

ኧረ! ባክሽ ልለምንሽ የኔ ውድ ውሃዬ ተመለሺ!!

ውሃ ሆይ ናፍቀሺኛል።

ውሃ ህይወቴ እኮ ነሽ!!

ውሃ የመኖሬ ምስጢር እኮ ነሽ!!

ውሃዬ ምግቡም ካላንቺ እኮ ከጉሮሮዬ አልወርድልህ አለኝ።

ውሃ ያለ አንቺ እንዴት መኖር ይቻለኛል? በፍፁም!!

ውሃዬ በእናትሽ
ውሃዬ በአባትሽ
ውሃዬ በምትወጂው ሁሉ ይሁንብሽ……ለወራት ከጠፋሽበት እስቲ ብቅ በይና “አለሁ…መጥቻለው …ሁሌም ካንተ ጋር ነኝ” በይኝ!!

ኦ! ውሃ
ኦ! ውሃ
ኦ! ውሃ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on August 29, 2014
  • By:
  • Last Modified: August 29, 2014 @ 11:44 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar