www.maledatimes.com በዓሉ ይመጣል ብዬ አሁንም በር በሩን አያለሁ ወ/ሮ አልማዝ አበራ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በዓሉ ይመጣል ብዬ አሁንም በር በሩን አያለሁ ወ/ሮ አልማዝ አበራ

By   /   September 25, 2014  /   Comments Off on በዓሉ ይመጣል ብዬ አሁንም በር በሩን አያለሁ ወ/ሮ አልማዝ አበራ

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 9 Second

 

የሰማዕቱደራሲበዓሉግርማባለቤት

( በቁምነገርመፅሔትቅፅ 13 ቁጥር 187፣ መስከረም 24/2007  የቀረበ ቃለ መጠይቅ)

በኢትዮጵያሥነፅሐፍውስጥስማቸውጎልቶከሚጠሩትደራስያንመካከልአንዱየሆነውደራሲናጋዜጠኛበዓሉግርማ ‹ኦሮማይ› በሚልርዕስባሳተመውመፅሐፉሳቢያመስዋዕትነትንየከፈለደራሲነው፡፡በአፃፃፍቴክኒኩ፤በአጫጭርአርፍተነገሮቹናበድርሰትመዋቅሩአዲስየአፃፃፍብልሃትንአምጠቷልተብሎየሚታመነውደራሲበዓሉግርማየካቲት 24 ቀን 1976 ዓ.ምከቀኑ 11 ሰዓትላይከቤቱእንደወጣየደረሰበትያልታወቀደራሲነው፡፡የበዓሉመጨረሻከዓመትዓመትሲያነጋግርናየቆየናያውቃሉየሚባሉሰዎችንምስክርነትእንደሻተእነሆ 30 ዓመትሞላው፡፡ይህኑመሰረትበማድረግየሙያአጋሩደራሲናጋዜጠኛአበራለማባለፉትሁለትተከታታይእትሞች ‹የማይጮሁትበዓሉንየበሉጅቦች › የሚልመጣጥፉንበቁምነገርመፅሔትላይ አስነብቦናል፡፡ይህንኑመነሻበማድረግየበዓሉግርማንባለቤትወ/ሮአልማዝአበራንየመፅሔቱአዘጋጅጋዜጠኛታምራትኃይሉበመኖሪያቤቷተገኝቶ ‹ህይወትከበዓሉበፊትናበኋላምንይመስላል?› ብሏታል፡፡ ‹መጨረሻውንየሚያውቁሁሉለህሊናቸውሲሉቢናገሩጥሩነው› የምትለውወ/ሮአልማዝባዶቤትሶስትልጆቹንትቶእንደወጣየቀረባለቤቷንየዓላማፅናትተጋርታልጆቿንአስተምራለወግለማዕረግያበቃችጠንካራሴትናት፡፡ ‹ በዓሉይመጣልብዬበርበሩንአሁንምአያለሁ› የምትለውወ/ሮአልማዝ ‹በዓሉመፅሐፉንሲፅፍምንሊመጣበትእንደሚችልያውቅነበር› ትላለች፡፡

ቁምነገር፡- ወ/ሮአልማዝበቅድሚያበመፅሔታችንላይእንግዳሆነሽስለባለቤትሽደራሲናጋዜጠኛበዓሉግርማናስላለፉት 30 ዓመታትህይወትለመነጋገርፍቃደኛስለሆንሽእጅግአድርጌአመሰግናለሁ?

ወ/ሮአልማዝ፡- እኔምአመሰግናለሁ፡፡

ቁምነገር፡- እስኪወደኋላልመልስሽናበዓሉበመፅሐፉሳቢያከስራከታገደበኋላለ6 ወራትያህልቤትውስጥነበርየሚውለው፤እንዴትነበርጊዜውንየሚያሳልፈውየሚለውንንገሪኝ ?

ወ/ሮአልማዝ፡- ምንምአይጨነቅምነበር፤ብዙጊዜውንቤትውስጥያሳልፍናከቤትወጥቶዞርዞርብሎይመጣል፤ቤትውስጥበነበረበትጊዜምንምአይጨነቀምመሳቅመጫወትነበር፡፡የትእንደወሰዱትአላውቅምእንጅአንዳንድነገሮችንይፅፍነበር፡፡ 6 ወርቤትውስጥሲቀመጥምንምአልተቸገርንምነበር፡፡እኔእንዲያውምበጣምነውደስያለኝ፡፡

ቁምነገር፡- ለምን?

ወ/ሮአልማዝ፡- ሥራላይበነበረበትጊዜየትአግኝተነውእናውቅናአሁንነውቤትመዋልሲጀምርበደንብቆምብለንማወራትልጆቹንምአንዳንድነገርማሳየትናማዝናናትየጀመረው፡፡ደሞዝየለንምግንየምንበላውአላጣንምነበር፡፡ሰውቤታችንመጥቶሲመለከትይገረመዋል፡፡ይህሁሉ ነገርሆኖ ”አንቺምአታዝኚምእሱምአያዝንም”ይለናል፡፡ ”እግዚአብሔርይመስገን”ነበርየምላቸው፡፡በዓልዬንተለይቼውአላውቅምነበርቤትውስጥሲቀመጥ፡፡እረፍትያለውሰውአልነበረም፤እሱእንደውምየኔንሁኔታእያየ ‹‹ደስአለሽአይደልአልሚቤትውስጥበመዋሌ›› ይለኝነበር፡፡እንደዚህምሆኖቀንቀንቤትአየዋለመሸትሸትሲልይወጣነበር፡፡ተውአትውጣስለውእሱምንምየሚፈራውነገርየለም፤እንደሚከታተሉትቢያውቅምአይፈራቸውምነበር፡፡ባዶእጁንነበርየሚወጣው፡፡ያኔስራላይበነበረበትጊዜእንኳሽጉጥእንኳየሚይዝሰውአልነበረም፤የኢሰፓደብተሩንምእኔጋርአስቀምጦነበር፣  የሚሄደው፡፡ከስራእንዳገዱትነውራሱሄዶየመለሰላቸው፤ ‹‹ምንምነውትንሽብትቆይ? ባትቸኩልሌላነገርእንዳያስቡብህ›› ስለው ”ባክሽተያቸውበቅቶኛል”ይለኝነበር፡፡

ቁምነገር፡- ፅሑፍላይግንእንዴትነበርየሚፅፈው፤ስለበዓሉከሰማኋቸውነገሮችመሀከልአንዱበዓሉማስታወሻሲይዝአይታይም፤ነገርግንአንድመፅሐፍፅፎለመጨረስጊዜአይወስድበትምነበርይባላል?

ወ/ሮአልማዝ፡- ትክክልነው፤በዓሉፅሑፍየሚጀምረውምየሚጨርሰውምጭንቅላቱውስጥነው፡፡ብዙጊዜአንድቦታተቀምጦይመሰጣል፤አትኩሮአንድነገርካየተመዘገበማለትነው፡፡ያንጊዜ”በዓልዬእየፃፍክነውአይደል?”አለዋለሁ፡፡ከዚህውጪወረቀትአያገላብጥምአንድጊዜለመፃፍከተቀመጠግንብዙገፅፅፎነውየሚነሳው፡፡

ቁምነገር፡- ብዙጊዜየሚፀፈውመቼነውምንሰዓትላይነው?

ወ/ሮአልማዝ፡- ከስራመልስነው፤ያውያለውጊዜያብቻነው፡፡መስሪያቤትከባድየሥራውጥረትነውያለበት፡፡ከስራከተመለሰበኋላልጆችበጊዜራታቸውንከበሉበኋላነውለመፃፍቁጭየሚለውልጆቹሲተኙቤቱፀጥይላል፡፡

ቁምነገር፡- በዓሉምንይወዳል?

ወ/ሮአልማዝ፡- ፀጥታይፈልጋል፤ዝምተኛነው፡፡ሁልጊዜዝምነውየሚለው፤ንፅህናይወዳል፡፡ጥሩቤትመኖርይወዳል፤ለሰውያዝናል፤ሙዚቃያደምጣል፤ገንዘብአይዝም፡፡እንደእሱያለውንገንዘብላገኘውሰውሁሉየሚሰጥሰውየለም፡፡የመፅሐፉንሽያጭእንኳበአግባቡየሚቀበልሰውአልነበረም፡፡አንድጊዜእንደውምምንሆነ መሰለህ? አንድመፅሐፉንእንዲያሳትምለትከአንድሰውጋርይዋዋላል፡፡ሰውየውመፅሐፉንሽጦለማተሚያቤትምመክፈልአልቻለም፡፡በዓሉነበርዋስአድርጎያስመዘገበው፡፡ታዲያማተሚያቤቱሰውየውንይከስናቤተሰቦቹንየሚያስተዳድርበትዳቦቤትነገርነበረው፡፡እናያዳቦቤትይሸጥናገንዘቡንይውሰድተባለ፤ሰውየውትንሽህመምተኛነበረ፡፡ሆዱእያበጠብዙጊዜታክሟል፡፡ከዛበዓሉጋርሰውየውይመጣና ”ይኽውልህእንዲህሆንኩልህበዛላይታምሜያለሁ”ይለዋል፡፡በዛጊዜበዓሉቤቱይሄዳል፡፡ሲሄድሚስቱልጆቿንይዛምሳሲበሉይደርሳል፡፡ ”እንዴትነው?” ብሎሲጠይቃት ”በቃቤታችንምሊሸጥነውመውደቂያየለንም”ትለዋለች፡፡በዛጊዜ ”በቃሀራጁነገነውእኔእመልሰዋለሁ፤ሰውሲሰቃይማየትአልፈልግም፡፡ዝምብላችሁተቀመጡልጆችሽንአሳድጊ፡፡”ብሏትወጣሀራጁንምአስቆመው፡፡ያውእሱዋስስለነበርለስንትዓመትያህልስንትሺህብርስገፈግፍኖርኩ፡፡በዓሉእንደዚህአይነትሰውነበር፡፡የተቸገረሰውአይቶማለፍአይችልም፡፡ስብሃትእራሱተናግሮታል ”የቸገረበዓሉካየቦርሳውይቀድመዋል”ብሏል፡፡ማድረግየፈለገውንየሚያደርገውከራሱተማክሮነው፡፡

ቁምነገር፡- የመጀመሪያልጃችሁመስከረምበዓሉበ1991 ዓ.ምገደማይመስለኛልአዲስአበባዩኒቨርሲቲበተዘጋጀፕሮግራምላይተገኝታአንድየተናገረችውነገርነበር፡፡ ”አባቴከአድማስባሻገርአበራወርቁጋርይመሳሰልብኛል፤በመፅሐፉላይአበራበ5 ዓመትዘጠኝየኪራይቤትቀያይሯልይላልእኛምያደግነውእንደዛነበር”ብላነበር?

ወ/ሮአልማዝ፡- ልክነው፤ቤትእንቀያይራለን፤ዘጠኝቤትቀያይረናል፡፡እቃችንንይዘንመዞርነው፡፡አንዳንድጊዜደግሞእቃችንእዛውትተንለአዲሱቤትየሚሆንሌላዕቃገዝተንነውየምንገባው፡፡ሰፊቤትሲገኝየመጀመሪያስራችንቦታውንበሜትርመለካትነው፡፡ከዛጋርየሚሄድሶፋገዝተንእንገባለን፡፡

ቁምነገር፡- ብዙጊዜየምትከራዩትቪላቤትነውወይስአፓርታማ?

ወ/ሮአልማዝ፡- ቪላቤትነበርበፊትየምንኖረው፡፡በኋላላይነው፣ እኔወደአፓርታማእንድንገባያደረግሁት

ቁምነገር፡- ለምን ?

ወ/ሮአልማዝ፡- ቪላቤትየተከራየንጊዜግቢውሰፊነው፡፡ግቢውንየሚጠብቁዘበኛነበሩ፡፡ዘበኛውየተለያዩስራእየሰሩሰውሲመጣበርቶሎአይከፍቱም፡፡እሱምበርላይብዙሰዓትይቆምነበር፡፡ከዛበቃአፓርታማእንግባብዬራሴፈልጌነውይህንንቤትያገኘሁት፡፡እሱምአፓርታማነውየሚወደውድሮስብዬአልነበረምብሎገባን፡፡

ቁምነገር፡- በዓሉከስራከታገደበኋላቤትውስጥሲውልችግርሊገጥመውእንደሚችልናከሀገርስለመውጣትአያስብምነበር ?

ወ/ሮአልማዝ፡- ከሀገርስለመውጣትፍፁምአያስብምነበር፤ችግርሊገጥመውእንደሚችልያውቅነበር፡፡ነገርግን ”ከዚህችሀገርንቅንቅአልልም”ነበርየሚለው፡፡ስለልጆቹምቢሆንወደፊትሲያድጉእውነቱንብቻእንዲናገሩአድርጊያቸውነበርየሚለኝ፡፡ከሀገርስለመውጣትአያስብምነበር፡፡

ቁምነገር፡- ግንኢምባሲአካባቢያሉሰዎችጠይቀውትነበርየሚባለውስ ?

ወ/ሮአልማዝ፡- ተጠይቋል፤በሞስኮኤምባሲ፣በአሜሪካኤምባሲአንተንብቻሳይሆንመላቤተሰቦችህንእናውጣችሁተብሏል፡፡ግንእምቢነውመልሱ፡፡ህንድኤምባሲምይሄነገርአጉልነውብትወጣይሻልሃልብለውትነበር፡፡እሱግንምንችግርአለውአስቤያደረኩነገርነው፡፡ ”ከሀገሬየትምአልወጣም!”ነበርመልሱ፡፡ወንድሜምውጭሀገርነበርሊያወጣውይችልነበር፤ግንሀገሩንለቆመውጣትአልፈለገም፤እዚሁመስዋዕትሆነ፡፡

ቁምነገር፡- ብዙጊዜለአለማቸውፅኑየሆኑሰዎችእንደዚህአይነትጥያቄሲቀርብላቸውባለመቀበልእራሳቸውንብቻነውመስዋዕትየሚያደርጉት፡፡ለልጆቻቸውናለቤተሰቦቻቸውግንየተሻለየሚሉትንነገርአድርገውነውያንንመስዋዕትነትየሚቀበሉ፡፡በዓሉለእናንተለልጆቹላይስለሚደርሰውነገርምንነበርሀሳቡ?

ወ/ሮአልማዝ፡- ልጆቹንበቃአንቺአሳድጊነበርየሚለው፤በመፅሐፉሳቢያየሚመጣውንችግርእዚህሀገርውስጥሆኖመቀበልስለሆነየወሰነውምንምነገርቢመጣልጆቹንእንደምንምብለሽአሳድጊነበርየሚለው፤እኔበሰራሁትስራከሀገርወጥቼልጆቼናሚስቴመቸገርመታሰርየለባቸውምነውየሚለው፡፡እዚምእዚያምተሯሩጬስራመስራትእንደምችልያውቃል፡፡በፊትማስታወቂያሚኒስቴርሰርቻለሁ፤ቴሌቪዥውስጥምሰርቻለሁ:: እኔባልኖርልጆቼንልታሳድጋቸውተትችላለችብሎይተማመንብኝእንደነበርነውየምረዳው፡፡ያለምንምጡረታያለምንምገንዘብባዶቤትነውትቶንበወጣበትየቀረው፡፡ግንእግዚአብሔርይመስገንልጆቼንእንደጓደኛአድርጌነውያሳደግኋቸው፡፡ያኔ ”አንተመፅሐፍስትፅፍእኔእየዞርኩእሸጥልሃለሁ”እለውነበር፡፡ደግሞምአድርጌያለሁ፡፡ያኔማስታወቂያሚኒስቴርስሰራበቀን 80 እና 90 ከአድማስባሻገርመፅሐፍንበየቢሮእያዞርኩእሸጥነበር፡፡ምሳሰዓትላይምሳለመብላትእንገናኛለን፡፡ ”ዛሬይኸውልህይህንያህልመፅሐፍሸጫለሁ”እለውነበር፡፡

ቁምነገር፡-በዓሉየቤትውስጥስራይሠራል ?

ወ/ሮአልማዝ፡- ይሠራል፤እኔነፍሠጡርስሆንየቤትውስጥስራዎችንይሠራነበር፡፡ምግብያበስላል፣ቤትማፅዳት፣አልጋማንጠፍየልጆችልብስመተኮስይሠራል፤ከስራየወጣጊዜእነዚህንየቤትውስጥስራዎችንይሠራነበር፡፡

ቁምነገር፡- ምግብየሚወደውምንድንነው?

ወ/ሮአልማዝ፡- ምግብየሚወደውሩዝነው፤የተወሰነዶሮወጥይወዳል፤ሱፕስቴክይወዳል፤ግንቀንየበላውንምግብማታቢቀርብለትአይበላም፡፡

ቁምነገር፡- መኪናይቀያይራልወይስ?

ወ/ሮአልማዝ፡- በፊትፔጆመኪናነበረችን፣ከዛእሷንሸጥንናያቺንአዲስቮልስዋገንገዛን፤ለኔምሌላመኪናገዝተንነበር፤ሁለትመኪናአንድቤትምንያደርጋልብለንሸጥናት፡፡

ቁምነገር፡- በዓሉማስታወቂያሚኒስቴርውስጥትልቅባለስልጣንነበር፤ቤታችሁአንዳንድትልልቅባለስልጣናትተጋብዘውይመጡነበር? እናንተስተጋብዛችሁትሄዱነበር?

ወ/ሮአልማዝ፡- ብዙምአይደለም፤ ግብዣቦታእሱምእንደነገሩነው፤እኔምሲጠሩኝየደርግባለስልጣናትጋርአልሄድምነበር፤ብቻውንሲሄድሚስትህስሲሉትእሷእኮእንደዚህአይነትነገርአይመቻትምነበርየሚላቸው፡፡

ቁምነገር፡- ኦሮማይመፅሐፍከወጣናበገበያላይተሰብስቦከተቃጠለበኋላኮለኔልመንግስቱቤተመንግስትድረስአስጠርተውትእንደተናገሩትለገነትአየለበሰጡትቃለምልልስላይተናግረዋል፤የዛንዕለትምንነበርየተነጋገሩት? ምንነግሮሽነበረበዓሉ ?

ወ/ሮአልማዝ፡- በእርግጥጠርተውትአነጋግረውታል፤ነገርግንበመፅሐፉላይሰውየውእንደሚሉትአይደለምየተነጋገሩት፤ውሸትነውየሚናገሩት፡፡የዛንዕለትተጠርቶየሄደውብቻውንአልነበረም፤የሸዋረንየተባለውየህንድሰውነበርአብሮት፡፡እንደገባሊቀመንበሩያሉት ‹‹ ምነውበዓሉከዚህበፊትበቀይኮከብጥሪአብዩቱንእንደዛአድርገህሳልከው፤አሁንደግሞበዚህመፅሐፍመንጋጋውስጥነውየከተትከን፤አንተምሁርነህ፤አብዩቱንስወታደሩንስለምንእንደዚህትላለህ?” አሉት፡፡ ”ሲጋራቸውንይዘውወዲያናወዲህይሉነበር”ብሎኛል… ”ለምንአላሳየኸኝምከመውጣቱበፊት”ምብለውትነበር፡፡

ቁምነገር፡- በዓሉምንአላቸው?

ወ/ሮአልማዝ፡- ምንምአላለ፤እንደዛእየተቆጡሲናገሩዝምብሎሲያዳምጥቆይቶ ”እኔዘመቻላይሆኜያየሁትንነውየፃፍኩት፤ወልደማርያምሀብተማርምብዬየተናገርኩትየጠቀስኩትሰውየለም፤እኔስለሀገሬነውየፃፍኩት፡፡እዛውስጥተጠቅስናልየሚሉሰዎችስራቸውንየሚያውቁትናቸው፡፡ኢትዮጵያየጋራሀገራችንናትብያለሁ፡፡እጅመሰንዘርምዋጋየለውም፤ከዚህውጭያልኩትነገርየለም”ሲላቸው ‹‹ይሄውነውአቋምህ?” አሉት፡፡ ‹‹አዎያሄውነው›› ሲላቸው ‹‹በቃሂድውጣ›› ብሎአስወጣው፡፡ከዛበኋላስራቸውንሰሩ፡፡ከስራየተሰናበተበትንደብዳቤእንኳሚኒስትሩሊሰጡትሲጨነቁ ”ግድየለምፈርሙበትናመጥቼእወስደዋለሁ”ብሎያላቸው ‹‹በዓሉይህነገርመጣእንዴትአድርጌጽፌልስጥህ?›› ብለውትስለነበር ነው፡፡

ቁምነገር፡- በዓሉየመንግስትከፍተኛባለስልጣንከመሆኑአንጻርየዚህአይነትውሳኔ /እርምጃ/ ላይይደርሳሉየሚልግምትነበረሽ ?

ወ/ሮአልማዝ፡- በዓሉባለስልጣንቢሆንምእኮበፍልጎትአይደለምየሚያሰሩትስልጣንየማይፈልግየማይወድሰውመሆኑንያውቃሉ፤እሱየሚፈልገውመፃፍብቻነው፤ግንየተማረሰውአጣንብለውነውበግድያስገቡት፡፡ቢሮውእንኳሲያመሽቢሮውመስኮትስርታንካቸውንእያስጠጉነበርየሚያስጠብቁት፤እንደማይወዳቸውያውቁነበር፡፡አንድጊዜእንደውምውጪሀገርእንግሊዝሀገርንግስትኤልሳቤትጋርደርሶሲመለስሊቀመንበሩ ‹‹ምንአለችህ?›› ብለውትበተናገረውነገርተናደውነበር፡፡

ቁምነገር፡- ምንድነው ?

ወ/ሮአልማዝ፡- የዛንጊዜየንጉሳውያንቤተሰቦችየታሰሩበትጊዜስለነበር፤ ”በኢትዮጵያእስረኞችበዝተዋል፤የንጉሳውያንቤተሰቦችንምብትለቋቸውእዚህእኔ ዘንድመጥተውይኖራሉ”ንግስቲቱማለቷንእንደመጣለሊቀመንበሩ  ነግሯቸውተቆጥተውነበር፡፡እንዲያውምበዓሉየንግስቲቱንሀሳብደግፎ”ይፍቀዱናሰዎቹንእንግሊዝሀገርአድርሻቸውልምጣ›› በማለቱ ”እንዴትነውየምትደፍረን?” ብለውታል፡፡በእንዲህእንዲህአይነትአጋጣሚዎችአቋሙንያውቁታል፡፡

ቁምነገር፡- በመፅሐፍድርሰትሥራቤተሰብንመምራትማኖርይቻላልየሚልእምነትነበረው?

ወ/ሮአልማዝ፡- የለውም፤ለስሜትያህልነውየሚፅፈውእንጂየድርሰትገቢያንያህልአይደለም፤ ”ገቢቢኖርምአሳታሚናማተሚያቤትነውየሚወስዱት፤ደራሲየሚያገኘውነገርየለም”ነውየሚለው፡፡

ቁምነገር፡- ከስራከታገደበኋላበሌላመ/ቤትሥራየመጀመርሀሳቡአልነበረውም ?

ወ/ሮአልማዝ፡- ጀርመኖችጋርስራአግኝቶመንግስትመ/ቤትከሚያገኘውደሞዝበሁለትሶስትእጥፍሊቀጥሩትሲሉነውየወሰዱት፤ከዛምበኋላወረቀትአግኝተናልየሚሉትይህንንየጀርመኖችድርጅትጋርየተፃፃፈውንወረቀትነው፡፡

ቁምነገር፡- ከቤትወጥቶከጠፋበኋላምንአደረግሽ ?

ወ/ሮአልማዝ፡-ምንአደርጋለሁ? ያወቃሉየምላቸውሰዎችጋርሄድኩ፡፡ምንምነገርየለም፤እዚህቦታሲሉኝተነስቼእሄዳለሁ፡፡ሸሚዝከአንድቀንበላይየማያደርገውበዓሉእስርቤትነውያለውሲሉኝየሸሚዝመአትይዤእዞራለሁ፡፡ሁሉምመልሳቸውአንድነው፡፡ከንፈራቸውንመጠውየለምነውየሚሉኝ፡፡ያክፉዘጠኝዓመትያለፈውበመከራነው፡፡በዛላይከቤቴወጥቼወደየትምብቻዬንመሄድአልችምነበር፡፡ 24 ሰዓትይከታተሉኛል፡፡ልጆቼንት/ቤትሳደርስይከተሉኛል፤የሆነገበያስሄድይከተሉኛልወደበኋላላይግንለመድኳቸውናሰውእንደሚከተለኝእንኳረሳኋቸው፤እኔመፃፍስለማልችልነውእንጂያሳለፍኩትህይወትራሱመፅሐፍየሚወጣውነው፡፡

ቁምነገር፡- የበዓሉግርማፋውንዴሽንያቋቋመውማነው?

ወ/ሮአልማዝ፡- መስከረምናዘላለምናቸውእዛውአሜሪካያቋቋሙት፡፡መስከረምበዓሉሲጠፋየ13 ዓመትልጅነበረች፡፡ግንአንዳንድነገሮችታውቅነበር፡፡ዘላለምትንሽልጅይሁንእንጂያውቃል፡፡እሷምእሱምማስተርስድግሪያቸውንከያዙበኋላነውፋውንዴሽኑንያቋቋሙት፡፡መስከረምበልጅነቷአንባቢልጅነበረችማስተርስድግሪዋንየሰራችውምበጋዜጠኝነትነው፡፡

ቁምነገር፡- ፋውንዴሽኑምንምንስራዎችንይሰራል ?

ወ/ሮአልማዝ፡-የተለያዩስራዎችንይሠራል፡፡ልጆቼእየተማሩስለነበረየፋውንዴሽኑስራየሚያንቀሳቅሱትእንደሚፈልጉትአልሠሩበትም፡፡ግንእስካሁንባለውጊዜበበዓሉስምየተለያዩደብተሮችንእስክርቢቶዎችንአሳትመውበሀገርውስጥለተለያዩችግረኛተማሪዎችአከፋፍለዋል:: ወደፊትደግሞቅርንጫፍጽ/ቤትእዚህየመክፈትሀሳብአላቸው፤የበዓሉየተለያዩሥራዎችናፎቶግራፎችአሰባስበውበሙዚየምመልክየማስቀመጥናቀጣዩትውልድእንዲማርበትየማድረግሀሳብመስኪአላት፡፡

ቁምነገር፡- የትውልድሀገሩኢሊባቡርጎሬበስሙት/ቤትተሰይሟልአይደል ?

ወ/ሮአልማዝ፡-የመንግስትት/ቤትነውበስሙየተሰየመለት፤ተጠይቄበደብዳቤአስፈቅደውኝነውየሰየሙትናበትውልድቦታውብዙልጆችየሚማሩበትት/ቤትነው

ቁምነገር፡- እናቱእዛነበርየሚኖሩት ?

ወ/ሮአልማዝ፡-አዎቅርብጊዜ ነውያረፉት፡፡አንድወቅትላይአዲስአበባአስመጥቻቸውነበር፡፡የኔእናትምበጣምተወደውነበርእዬዬእያለችነውየሞተችው፤እናቱየባላባትልጅስለሆኑሀብታምነበሩ፤አርሻናወፍጮቤትነበራቸው፡፡የቡናመፈልፈያምነበራቸው፤ተወርሶባቸውነበርኢህአዴግከገባበኋላነውእኔጠይቄየመለሰላቸው፡፡

ቁምነገር፡- 30 ዓመታትረዥምጊዜነው፤ምንከፉናደግነገርታስታውሻለሽከበዓሉበኋላ ?

ወ/ሮአልማዝ፡- ልጆቼንጥርሴንነክሼአሳድጌለወግማዕረግለማብቃትበመቻሌእግዚአብሔርንአመሠግነዋለሁ፡፡ልጆቼአባታቸውከቤቱወጥቶእንደቀረባቸውሳይሳቀቁየሚፈልጉትንነገርእያሟላሁላቸውየሚፈልጉትቦታበዓሉበነበረጊዜየምንወስዳቸውቦታሶደሬላንጋኖእየወሰድኩሳይሰማቸውነውእንዲያድጉያደረግሁት፡፡ሁለቱአሁንአሜሪካሀገርተምረውተመርቀውትዳርይዘዋልትንሹክብረበዓሉአብሮኝአለ፡፡ለዚህምእግዚአብሔርንአመሠግነዋለሁ፡፡ያነገርሆኗልከዛውጪያለውነገርየሚነሳአይደለምክፉጊዜነበር፡፡

ቁምነገር፡- መንግስትሲቀየርምንታስቢነበር፤በዓሉታስሮምከሆነየሆነ ቦታይገኛልብለሽታስቢነበር?

ወ/ሮአልማዝ፡- እጠብቅነበር፤ተስፋአደርግነበር፡፡ግንያውየዛንጊዜመንግስትእንደተቀየረበሬዲዮአንድነገርሲነገርሰማሁ፤አንድበወቅቱሹፌርነበርኩሊገረፍሲልአመላልሰውነበርያለሰውአውቃለሁየሚለውንሲናገርስሰማራሴንስቼወደቅሁ፡፡ከዛበኋላየማውቀውነገርየለም፡፡በኋላበቤታችንዙሪያእኔምንምሳላውቅ ‹‹ከቤቱእንደወጣየቀረውደራሲናጋዜጠኛበዓሉግርማ›› ብለውፎቶውንሁሉአባዝተውበየህንፃውላይለጥፈውተመለከትኩ፡፡ ”በዓሉየሚወዳትንሚስቱንትቶ፤የሚወዳቸውንሶስትልጆቹንትቶከቤቱእንደወጣለሀቅየወደቀሰውነው›› ይላልየተለጠፈውበከተማውላይ፡፡ሰዎችይህንንከተማላይየተለጠፈውንአይተውእያለቀሱቤቴድረስመጡ፡፡ እኔግንአሁንምድረስበዓሉይመጣልብዬበርበሩንነውየማየው፤ግንአንዳንድጊዜደግሞበግሌበነፍስካለበእኛላይእንዴትሊጨክንናሊጠፋይችላል? እላለሁግንአሁንምድረስእንዲህነውየሚልሰውአላገኘሁም፡፡

ቁምነገር፡-መንግስትእንደተቀየረየኢህአዴግባለስልጣናቱንአግኝተሸየበዓሉንግድያያውቃሉከሚባሉትሰዎችጠይቃችሁእባካችሁአሳውቁኝአላልሻቸውም ?

ወ/ሮአልማዝ፡- ብያለሁ፤ወዲያውእኮነውባለስልጣናቱከታሰሩበኋላለተቋቋመውልዩአቃቤህግክስሲመስረትቃሌንሰጥቻለሁ፤ለፍ/ቤቱየሰጠሁትቃልለታሪክተመዝግቦይገኛል፡፡መላየኢትዮጵያህዝብሁሉስለበዓሉመጨረሻየሚያውቁትእንደነግሩኝጠይቄያቸዋለሁ፤ግንአቃቤህጉ፤ ‹‹በዓሉግርማያለ ፍርድየተገደለነው›› ብለውደብዳቤፅፈውሰጥተውናል፡፡ምንያደርጋልበዓሉግርማለህዝብብሎለሀቅብሎየተሰዋደራሲነው፡፡ግንአንዳንድሰዎችያልሆነነገርሲናገሩሲፅፉአያለሁ፡፡ለምሳሌበዓሉግርማገዳምውስጥነውያለውብለውበሬዲዮሁሉቅርብጊዜሲናገሩነበር፡፡እዚህታይቷል፤እዚያነውያለውየሚሉናየሚፅፉመፅሔቶችአሉ፡፡የበዓሉንማንነትተረድተውሀቅቢያወጡነበርየምፈልገው፡፡የቤተሰቡሀዘንከመጨመርውጪዋጋየላቸውም፡፡ስለበዓሉየተፃፉማናቸውምነገሮችአያመልጡኝም፤ግንእውነቱንየሚናገርየለም፡፡የወደቀበትንየሚናገርየለም፡፡

ቁምነገር፡- ኦርማይመፅሐፉእንደወጣነበርየታገደውናከገበያላይየተሰበሰበውሰውእጅገብቶነበርለማለትይቻላል?

ወ/ሮአልማዝ፡-የገዙሰዎችእያከራዩያስነብቡነበር፤ሽያጭም 600 ብርደርሶነበር፡፡

ቁምነገር፡- መታገዱንያወቃችሁትእንዴትነበር ?

ወ/ሮአልማዝ፡-እኔመርካቶለቅሶለመድረስስሄድሰዎችየበዓሉግርማመፅሐፍከገበያላይእየተሰበሰበነውሲሉሰማሁ፡፡ደንግጪቦርሳዬንከነገንዘቡየትቦታእንደጣልኩትአላውቅም፤ስበርቤትስደርስ ‹‹ዳዲመጥቶነበር፤መፅሐፉከገበያላይእየተሰበሰበስለሆነአታስቢ›› ብሎሻልአሉኝልጆቼ፤እሱለካቀድሞአወቋል፡፡

ቁምነገር፡- በወጣበስንተኛውቀንመሆኑነው?

ወ/ሮአልማዝ፡-የተሸጠውለ10 ቀናትብቻነው፡፡ልክበ10ኛውቀንነውየሰበሰቡትናያቃጠሉት

ቁምነገር፡- ቤትውስጥመፅሐፉንአምጥቶትነበር?

ወ/ሮአልማዝ፡- ያውሁሌምእንደሚያደርገውለሰዎችበስጦታመልክየሚሰጠውንየተወሰኑመፅሐፍትአምጥቶነበር፤ልክያንንየሰማሁዕለትአንዷንመፅሐፍወስጄደብቄያትአሁንምድረስአለ፡፡

ቁምነገር፡- በታተመውእናበቀድሞውመፅሐፍመሀከልልዩነትአለየሚሉወገኖችአሉ፤የተቀነስነገርአለእንዴ?

ወ/ሮአልማዝ፡- ራሱነውየታተመው፤ያውኢህአዲግእንደገባየወቅቱየማስታወቂያውሚኒስትርአቶበረከትነውራሱጠርቶኝልክእንደወረደመፅሐፉይታተምለትብሎትዕዛዝየሰጠልኝ፡፡ያውድጋሚሲታተምለመታሰቢያይሁንብዬየሆነነገርማስታወሻፃፍኩለት፤አብሮ ታተመ፡፡

ቁምነገር፡- ቤቱንልቀቂተብለሽነበር ?

ወ/ሮአልማዝ፡-እነሱማበላዬላይሁሉሊያሽጉመጥተውነበር፡፡በርላይጠብቄዞር በሉአልኳቸው፤በማግስቱየኪቤአድዋናስራአስኪያጅጋርሄጄባለቤቴከቤትእንደወጣአልተመለሰም፡፡ ”ሶስትልጆቼንይዤየትልወድቅነው?” ስለው ”ባለቤትሽማነው?” አለኝ፤ ”አላውቅም”አልኩት፡፡ ”ወታደርነው?” አለአይደለም፡፡ ”ማነው?” ሲለኝ ”አልናገርም”አልኩት፡፡እሺለጊዜውሰውእያነጋገርኩነውከቢሮውጪጠብቂኝአለኝ፤ከቢሮስወጣፀሐፊውአየችኝ፤አወቀችኝከዛገብታነገረችውመሰለኝእንግዶችንከሸኙበኋላ ‹‹የበዓሉግርማባለቤትመሆንሽንለምንአልነገርሽኝም?›› አለኝ፤ ”ለምንእነግርሃለሁ?” አልኩት፡፡ ”የአንቺጉዳይበጣምከባድነው፡፡ለማናቸውምምንልርዳሽ?” ብሎ 100 ብርከኪሱአውጥቶሊሰጠኝእጁንዘረጋ፡፡ ”እኔልመናአልመጣሁም፤ምፅዋትህንቤተክርስትያንሄደህስጥ”አልኩትና ‹‹ባሌወንድነውእኔምየወንድልጅነኝእስኪማነውመጥቶየሚያስወጣኝአያለሁ›› ብየውወጣሁ፡፡ከዛበኋላአልመጡም፤ክትትሉግንእንዳለነበር፡፡

ቁምነገር፡- በመጨረሻያንክፉጊዜከነልጆቸሽስታሳልፊአይዞሽሲሉየነበሩአንቺንምበዓሉንምሳያውቁግንየሚቆረቆሩበብዕራቸውምየሚጠይቁሰዎችይኖራሉናየምታመሰግኚያቸውሰዎችአሉ ?

ወ/ሮአልማዝ፡-በጣምብዙሰዎችአሉ፤ያንጊዜእኮመንገድላይሁሉሰዎችይሸሹኝነበር፤ፊታቸውንሁሉየሚያዞሩነበሩ፡፡ስንትነገርአብረንያሳለፍንሁሉለእግዚአብሔርሰላምታይፈሩነበር፤የሆነሆኖያጊዜአለፈ፡፡በመጀመሪያየኢትዮጵያመፅሐፍትድርጅትባለቤትአቶተስፋዬዳባብዙመፅሐፉንያሳተሙለትባለውለታችንነው፤አቶአማረማሞ፣ደራሲአበራለማ፣አመሰግናቸዋለሁ፡፡ዶ/ርሙለጌታበዛብህየቅርብጓደኛውነውይጠይቀኛል፤የልጆችት/ቤትያግዘኝነበር፤አቶጌታቸውብናልፈውሳይፈራየሚጠይቀኝሰውነው፡፡አቶእስቂያስአገኘውቤተሰብነው፡፡ከኔያልተለየሰውነው፡፡እግዚአብሔርውለታቸውንይክፈላቸው፤ብድራቸውንይመልስላቸውነውየምለው፤ፕሮፊሰርመስፍንወልደማርያምቤተሰብነበር፤አሁንአሁንሲታሰርሁሌሄጄእጠይቀውነበር፤ከበዓሉጋርምይግባቡነበርየወንድሜምጓደኛነው፡፡

ቁምነገር፡- በወቅቱከነበሩመንግስትባለስልጣናትመሀከልአንዳንዶቹበአሁኑወቅትከሎኔልመንግስቱንጨምሮመፅሐፍእየፃፉነው፤ስለበዓሉግርማመጨረሻየሚያውቁትንነገርእንዲናገሩምንመልእክትታስተላልፊያለሽ ?

ወ/ሮአልማዝ፡- እኔየምላቸውነገርየለም፤የሚያውቁትንግንለኢትዮጵያህዝብቢናገሩእውነቱንቢያወጡጥሩነውለህሊናቸውቢሆንሀቁንቢያወጡደስይለኛል፡፡

ቁምነገር፡- ደርግግንይወድቃልብለሽታስቢነበር ?

ወ/ሮአልማዝ፡-ለምንአይወድቅም? ጃንሆይምወርደዋል፤ደግሞየእነሱግፍይበልጣል፣ግፉራሱይጥላቸዋልብዬነበርየማስበው፡፡

ቁምነገር፡- በዓሉከቤትከወጣበኋላመኪናውቃሊትአካባቢቆማነበርተብሏልእንዴትአገኘሻት ?

ወ/ሮአልማዝ፡- ያውበየዕለቱወዲያወዲህእያልኩበየእስርቤቱሁሉእጠይቅነበር፤በ10 ኛውቀንቃሊቲመንገድዳርቆማለችብለውነገሩኝ፤ሄጄጠይቄልወስድብዬአስፈቀድኩ፤መኪናተመድቦአጅበውኝመኪናዋንከቆመችበትአመጣናትናግቢውስጥአቋምኳት፡፡ጠዋትጠዋትባየኋትቁጥርመበሳጨትስላልፈለግሁሸጥኳት፡፡

ቁምነገር፡- አመሠግናለሁ፤

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on September 25, 2014
  • By:
  • Last Modified: September 25, 2014 @ 3:17 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar