www.maledatimes.com ኢምባሲውን የመውረር ስክሪፕት ጸሀፊዎች አነማን ይሆኑ? - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ኢምባሲውን የመውረር ስክሪፕት ጸሀፊዎች አነማን ይሆኑ?

By   /   September 30, 2014  /   Comments Off on ኢምባሲውን የመውረር ስክሪፕት ጸሀፊዎች አነማን ይሆኑ?

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 21 Second

ኢምባሲውን የመውረር ስክሪፕት ጸሀፊዎች አነማን ይሆኑ?
=~=~=~=~=~=~=~=~=~=~=~=~=~=~=~=
ይህ ጉዳይ ተቃውሞ ሊባል የሚችልበትን ልክ ያለፈ ይመስለኛል።ከልክ ያለፈ የተራ ወሮበላ ስራ እየሆነ ነው። የዩስ አሜሪካ መንግስት በሀገሩ የሚገኙ የማንኛውም ሀገር ኢምባሲና ዲፕሎማቲክ ሰራተኞች ጸጥታና ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት። ይህ ሀላፊነት የሚነሳው በ፲፱፷፩ የቪየና ዲፕሎማቲክ ግንኙነቶች ኮንቬንሽን አንቀጽ ፳፪ መሰረት የተቀባይ ሀገር ኃላፊነት በመሆኑ ነው።

ኮንቬንሽኑ በተጨማሪም የአንድ ኢምባሲ ግቢ የማይደፈር እንደሆነ ይደነግጋል። የአሜሪካ መንግስት የጸጥታ ሀይሎች በተደጋጋሚ ይህን ሀላፊነታቸውን መውጣት አልቻሉም። የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናትም ለዲፕሎማቲክ ተልዕኮ ሰራተኞቻቸውና ባለስልጣኖቻቸው ደህንነትን የሚመለከት ሀላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል።

ልጅ እያለሁ(ከ፲-፲፪) ያነበብሁት ትርጉም ልብወለድ መጽሀፍ ትዝ ይለኛል። ታሪኩ ስለ አንድ የመገናኛ ብዙሀን (ፕሬስ) ነው። ፕሬሱ ከአሸባሪዎች ጋር ግንኙነት አለው። ፋይናንስ ያደርጋቸዋልም። እናም ወደ ማተሚያ በሚገባበት ሰዓት ሁልጊዜም ሰበር ዜናዎች አሉት። ብዙ ጊዜም የዜናው ዝርዝር አስቀድሞ ነው የሚጻፈው።

የተፈለገው ቦምብ በማድሪድ በፓሪስ ወይም በጣሊያን ከተሞችና በኒዮርክ ሲከናወን ጥዋት ላይ የሚዘግበው ያ ጋዜጣ ብቻ ነው። በመሆኑም ሰበር ዜና ብቻ ሳይሆን ዝርዝሩም በደንብ የሚወርድ ታሪክ አለው። ዲሲም ይህ የዜና ስራ ከዲሲዎቹ የመገናኛ ብዙሀን ጋር በቅንጅት የሚሰራ ይመስላል። የብዙሃን መገናኛ ታማኝነትን ለማግኘት የሚፈበረኩትና የሚተወኑት ሰበር ዜናዎች ቅጥ እያጡ ነው።

በደንብ በተደራጀ ጥቂት ወሮ በሎች የአንድ ኢምባሲ ግቢ ወይም የግለሰብን ንብረትና የክብር አጥርን ያለህግ እየደረመሱ ይገቡና ዜና አንባቢዎቹና ጸሀፊዎቹ ሰበር ዜና ለማብሰር የሚርዋሩዋጡበትን ሁኔታ እየታዘብን ነው።

ስለዚህም ይህች የዜና እሽቅድድም በመገናኛ አውታሮቹ ስምሪት የሚሰጠው ቡድን ለዜና አደን እንደወጣ ጠቋሚ ነው።እነዚህ ግለሰቦች አጥር ጥሰው የሚገቡበትን ተውኔት የሚጽፉትና የአርታዒነት ሚናውን የሚጫወቱት በኢሳት ስቱዲዮዎች ያሉ ወይም እስከዚያ የረዘሙ እጆች ቢሆኑ አያስደንቀኝም።

የሆነ ሆኖ ይህ መንገድ በህግም በሞራልም የሚያዋጣ አይመስለኝም። ተቃውሞም የራስን ኃላፊነት በተገነዘበ መንገድ መከናወን አለበት። መለኪያችን ምንም ይሁን ምን እስካሁን ለተከናወኑት ችግሮች ተጠያቂ አልተደረግንም በሚል በወንጀል ላይ ወንጀል ባይደራረብ ይጠቅማል። በዚያውም የኢሳት የጭንቅላት ጓዳም እየተበረበረ ነው። ወደ ጤናቸው ይመልሳቸው ዘንድ እንጸልያለን።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on September 30, 2014
  • By:
  • Last Modified: September 30, 2014 @ 12:11 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar