www.maledatimes.com ኢትዮጵያ የኤርትራ የእግር ኳስ ቡደን ተጨዋቾች ወደ ግዛቷ እንዳይገቡ አገደች Tamiru Geda - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ኢትዮጵያ የኤርትራ የእግር ኳስ ቡደን ተጨዋቾች ወደ ግዛቷ እንዳይገቡ አገደች Tamiru Geda

By   /   November 11, 2015  /   Comments Off on ኢትዮጵያ የኤርትራ የእግር ኳስ ቡደን ተጨዋቾች ወደ ግዛቷ እንዳይገቡ አገደች Tamiru Geda

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 14 Second

በመጪው የህዳር ወር መባቻ ላይ ኢትዮጵያ ታስተናግደዋለች ተብሎ የሚጠበቀው የ ምስራቅ እና የመካከለኛው አፍሪካ (CECAFA)የእግር ኳስ ወድድር ላይ ለመገኘት እድሉን ካገኙት የአካባቢው አገሮች ብሔራዊ ቡድኖች አንዱ የሆነው የኤርትራ ቡደን ወደ ኢትዮጵያ ተጉዞ አንደይወዳደር በኢትዮጵያ ባለሰልጣናት ክልከላ እንደተደረገበት ተገለጸ።

ጎረቤት ሩዋንዳ ለታዘጋጀው አሰባ በሰተመጨረሻው ከአቋሟ ሸረተት ያለችበት የ 2015 እኤ አ 38ኛው የሲካፋ ሰኔየር እግር ኳስ ተጨዋቾች ወድድር የሚጀመረው የፊታችን ህዳር 21 /2015 ጀምሮ እሰከ ታህሳስ 6 /2015 አኤአ ሲሆን በዚህ ወድድር ላይ የሚሳተፉ አሰራ አንድ ቡድኖች ሲሆኑ ከእነዚህ መካከል አንዱ የሆነው የኤርትራ እግር ኳስ ቡድን ወደ አዲስ አበባ ተጉዞ እንዳይጫወት በ አ/አ መንግስት ባለሰልጣናት ማእቀብ እንደተጣለበት አሶሺተድ ፕሬስ ማክሰኞ እለት ዘግቦታል።

የኤርትራ የእግር ኳስ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መሬት ዘልቀው ስፖርታዊ ወገናዊነት እና ወንድማማችነታቸውን እንዳያሳዩ እንቅፋት የሆነባቸው ምክንያቱ በአ/አ እና በአሰመራ የወቅቱ ገዢዎች መካከል የተፈጠረው የወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ቁርቋርሶ ሳቢያ ነው ተብሏል። በዚህ ውድድር ላይ የ ወቅቱ ሻምፒዪናው የኬኒያ ቡድን፣ የኡጋንዳ፣ የአስተናጋጇ የኢትዮጵያ፣የጅቡቲ፣ የብሩንዲ ፣,የሶማሊያ ፣የሩዋንዳ፣ ፣የሱዳን እና የታንዛኒያ ቡድኖች የሚሳተፉ ሲሆን እገዳ የተጣለበት የኤርትራን ቡድን በመተካት የማላዊ ቡድን( የራሱን የጉዞ ወጪ በመሸፈን)በእንግዳ ቡድን ተሳታፊ እንዲሆን ተጋባዥ ሆኗል።

ምንም እንኳን በተለምዶ አሰተናጋጅ አገር ሁልጊዜ በሩን ለሁሉም ተወዳዳሪዎች መክፈት ሲገባው በኢትዮጵያ በኩል “እነ እከሌ ይምጡ እንእከሌ ግን ድርሽ እንዳይሉ” ማለት ተገቢ ባይሆንም የሲካፋ ዋና ጸሃፊ የሆኑት ኒኮላስ ሞሶናይ”ኢትዮጵያ የኤርትራ ተጨዋቾችን በግዛቴ ላይ አላሰተናግድም የማለት አቋሟን ልናከብርላት ግዴታ አለብን”በማለት የ አ/አ ውሳኔን በአውንታነት ተመልክተውታል። 24 የኤርትራ ተጨዋቾች ለውድድር ወደ ኬኒያ ተጉዘው በዚያው መቅረታቸውን ተከትሎ (ሲካፋ) የኤርትራ እግርኳስን በ2013 ከተሳታፊነት ማገዱ አይዘነጋም።

የኤርትራ የእግር ኳስ ተጨዋቾች ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ በተሰጠው ማእቀብ ዙሪያ ከአሰመራ ባለሰልጣናት ሆነ ከአዲስ አበባ አቻዎቻቸው በኩል እስከ አሁን ድረስ የተሰጠ ምላሽ ባይኖርም በተለይ ደግሞ “ለእርቀ ሰላም ሲባል እሰከ አሰመራ ድረሰ ተጉዘን እንደራደራለን”የሚሉት የወቅቱ የኢትዮጵያ ገዢዎች ከፖለቲካ የጸዳ እና ሰላማዊ የውድድር መንፈስ ይዘው የሚመጡት የኤርትራ እግር ኳስ ተጨዋቾችንን ከዚህ ቀደም እንደማይተዋወቁ በሚያሰመስል “ወዲህ አትምጡብን” ማለታቸ በሁለቱ ፖለቲከኞች መካከል የከራረመውን የጥላቻ ፖለቲካን ያጎላዋል ተብሎ በብዙዎች ዘንድ ይገመታል ።

በተለይ ደግሞ የጉዞው እገዳ አንኳን አብሮ የኖረው እና የተዋለደው ህዝብን ቀርቶ በሰታዲሙ ውስጥ ዳቦ ለወረወረባቸው የናይጄሪያ ቡድን ደጋፊዎች ሳይቀር ቁጣውን በማብረድ ናይጄርያ ከሌላ ቡድን ጋር ስተጋጠም ደጋፉን እሰከ ምሰጠት የደረሰው ኩሩው እና እንግዳ አክባሪው የኢትዮጵያ እግር ኳስ አፍቃሪን መናቅ ይመሰላል። የእግር ኳስ ታላቅነትን በተመለከተ በአለማችን ላይ ለዘመናት ሲናቆሩ የኖሩት እስራኤል እና ፍልስጤም እርቀ ሰላም ሊያወርድላቸው የሚችለው የአለማችን ፖለቲከኞች ጋጋታ ወይም የጦር መሳሪያ ሸመታ ሳይሆን እግር ኳስን ተተኪ በሆኑት በህጻናት እና በወጣቶች መካከል ማሰረጽ በቸኛው መፍትሄ ተደርጎ በሰፖርት ባለሰልጣናት ዘንድ ዘወትር ይመከራል። ይሁን እንጂ የሁለቱ ወገኖችን (ኤርትራ እና ኢትዮጵያ) ደም ካፋሰሰው የ 1998 -2000 አኤአ የድንበር ላይ ግጭት ከ 70 ሺህ በላይ ዜጎች ህይወትን የቀጠፈ ሲሆን ይህ “ሰላም የለም ጦርነትም እንዲሁ “የተሰኘው የወቅቱ የድንበር ላይ ውጥረት ዛሬም ቢሆን ለእረቀ ሰላም ከመጣጣር አንዱ የሌላኛውን ተቃዋሚዎች በማደራጀት እና በማሰታጠቅ “የጠላቴ ጠላት” በሚለው ፈሊጥ ተተብትበው ሲሯሯጡ እና አንዱ የሌላኛውን ውድቀትን ለማየት ሲጥሩ እና ሲመኙ እንደሚገኙ በሰፋት ይነገራል።

Tamiru Geda's photo.
Tamiru Geda's photo.
Tamiru Geda's photo.
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 8 years ago on November 11, 2015
  • By:
  • Last Modified: November 11, 2015 @ 11:48 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar