www.maledatimes.com የጭለማ ዘመን ከኢትዮጵያ ማህጸን ደጋግሞ የመፍለቁ ሚስጢር ምን ይሆን? - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የጭለማ ዘመን ከኢትዮጵያ ማህጸን ደጋግሞ የመፍለቁ ሚስጢር ምን ይሆን?

By   /   February 28, 2017  /   Comments Off on የጭለማ ዘመን ከኢትዮጵያ ማህጸን ደጋግሞ የመፍለቁ ሚስጢር ምን ይሆን?

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 51 Second
ሸንቁጥ አየለ

—————————————
-ዘመነ መሳፍንት ኢትዮጵያን 179 አመታት በጨለማ ዘመን ዉስጥ አስሮ አኖራት::በርካታ ሀገራት በተለይም ምዕራባዉያን ወደ ቀጣይ እድገት የተሸጋገሩበትን የግንዛቤ ለዉጥ የጨበጡት እና መሰረታዊ የአስተሳሰብ ለዉጥ ያመጡበት ወቅት ይሄዉ ኢትዮጵያ በዘመነ መሳፍንት ጨለማ ዉስጥ ስትዳክርበት የነበረዉ ዘመን ነዉ::

-ኢትዮጵያ በታላቁ አጼ ቴዎድሮስ ራዕይ እና ተጋድሎ በዳግማዊ አጼ ሚኒሊክ የማግባባት ጥበብ እንደ ሀገረ ከተሰባሰበች ብኋላ ከማህጸኗ የሚፈልቀዉ አስተሳሰብ አሁንም ወደ ጨለማ ዘመን የሚጎትታት ሆኗል::ህዝቡን እንደ ዘመነ መሳፍንት በብዙ ንጉሶች እና ገዥዎች ለመቀጥቀጥ እና ሀገሪቱን ለመበተን የሚጮህ ከፉ መንፈስ ጉልበት ያገኘ ይመስላል::

-የኢትዮጵያን ህዝብ እግዚአብሄር ኢትዮጵያ ብሎ የጠራዉ አንድ ህዝብ ነዉ::መልኩ እና መልከዓምድሩን ባህሪዉን እና ማንነቱን ሁሉ መጽሀፍ ቅዱስ ዘርዝሮ የዘገበለት ህዝብ ነዉ:: ሆኖም የኢትዮጵያ ምሁር ተብዬ እና ፖለቲከኛ ተብዬዉ ኢትዮጵያዊነትን እንኳን በተባለዉ ደረጃ ሊያከብረዉ ቀርቶ በኢትዮጵያዊነቱ ላይ ነጋ ጠባ እንደተጨቃጨቀ ይሄዉ አመታታ አለፉ:: አንዱ ጎሳ ከሌላዉ ጎሳ የተለዬ እንደሆነ የሚሰብኩ እና ጥላቻን የሚዘሩት ፖለቲከኞች ምድሪቱን ቀስፈዉ ከያዟት ይሄዉ 50 አመታት አለፋቸዉ:: ወደ ፊት በማዬት የነገን የጋራ በረከት ብሎም በመላዉ አለም እየፈለቀ ያለዉን የቴክኖሎጂ ጸጋ ህዝባቸዉ እንዲጠቀምበት ከማድረግ ይልቅ ኢትዮጵያዊዉ ላታላቅ የመጠፋፋት መንፈስ እንዲነሳሳ ልዩነት እና ጥላቻን ሰባኪ በዝቶበታል::

-ቢልጌት እና ታላላቅ የምድራችን ተጽእኖ ፈጣሪዎች እንደሚተነብዩት የሰዉ ልጅ በ2025 ዓም አጠቃላይ የህይወት እንቅስቃሴዉ በቴክኖሎጂአዊ ቀመር በእጅጉ ይለወጣል:: ይሄ የሚሆነዉ ታዲያ አሁን በቴክኖሎጂዉ ላይ በጥልቀት ሳያሰልሱ እየሰሩ ባሉ ህዝቦች እና ሀገራት ዘንድ ነዉ::

-ኢትዮጵያስ? የኢትዮጵያ ጉዳይ እማ አሁንም ወደኋላ መጎተት ሆኗል::ቴክኖሎጂ ላይ መስራት እና ከቴክኖሎጂ ጋር ህዝቡ መተዋወቁ ቀርቶበት የሚግባባበት የጋራ ሀገር; የጋራ መንፈስ እና ቃላት እንኳን አጥቷል::እሁን ያለዉ ትዉልድ እርስ በርሱ ሊግባባ ቀርቶ ቀድመዉ ከነበሩ የታሪክ ተዋንያን ጋርም ተጣልቷል:: የተሰራለትን ሀገር በምስጋና ተረክቦ የተሻለ ዲሞክራሲያዊ ሀገር አድርጎ ለመስራት በመግባባት ከመስራት ይልቅ ሀገሩን በመከራ ዉስጥ አልፈዉ የገነቡ አባቶችን ምላሱን እያወጣ መሳደቡን ቀጥሏል::የሰፈነዉ ሀገራዊ መንፈስ እጅግ አስጨናቂ እና አስፈሪ ነዉ::

-ይሄን ያስተዋለ እና ጭቅጭቅ የሰለቸዉ አንዳንድ ሰዉ ታዲያ አብረን መኖር ካልሆነልን ለምን አንለያይም ሲል ሀሳብ ያቀርባል:: ግን ጥያቄዉ የኢትዮጵያ ሰዉ ቢለያይስ አሁን በሀገር ደረጃ ያለዉ የመለያዬት እና የጥላቻ መንፈስ ወደ እዬ ነገዱ አይወርድም ወይ? ደግሞስ እዉነት ለመለያዬት ኢትዮጵያኖች ቢነሱ እርስ በርስ የሚያጫርሳቸዉ ብዙ ነገር የለም ወይ? አንዳንዱ እንደሚያስበዉ እያንዳንዱ ቁራጭ መሬት እያንጠለጠለ መሮጥ ይቻላል ወይ? ይሄኛዉ መሬት የዚያኛዉ ጎሳ/ነገድ ብሎ እርኩስ መንፈስ የሰፈረበት ወያኔ እንደከለለዉ ሀገሩ ሲፈርስ ህዝቡ ተስማምቶ ይሄ የኔ ያኛዉ ያንተ ብሎ ምድሪቱን መከፋፈል ይችላል ወይ?መለያዬትስ አብሮ ከመኖር ቀላል ነወይ?

ዋናዉ ጥያቄ ግን እንዲህ የጭለማ ዘመን ከኢትዮጵያ ማህጸን ደጋግሞ የመፍለቁ ሚስጢር ምን ይሆን?

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on February 28, 2017
  • By:
  • Last Modified: February 28, 2017 @ 10:23 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar