www.maledatimes.com በባሕር ዳር ዩንቨርሲቲ ፖሊ ቴክኒክ ግቢ የትግራይ ተወላጅ ተማሪዎችን የሚያስጠነቅቅ ወረቀት ተበትኖ አደረ | የዘር ግጭት እንዳይነሳ ሥጋት አለ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በባሕር ዳር ዩንቨርሲቲ ፖሊ ቴክኒክ ግቢ የትግራይ ተወላጅ ተማሪዎችን የሚያስጠነቅቅ ወረቀት ተበትኖ አደረ | የዘር ግጭት እንዳይነሳ ሥጋት አለ

By   /   March 1, 2017  /   Comments Off on በባሕር ዳር ዩንቨርሲቲ ፖሊ ቴክኒክ ግቢ የትግራይ ተወላጅ ተማሪዎችን የሚያስጠነቅቅ ወረቀት ተበትኖ አደረ | የዘር ግጭት እንዳይነሳ ሥጋት አለ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 32 Second

መንግስት በዘር የከፋፈለው ለእንደዚህ አይነት የእርስ በእርስ ግጭት ሊዳርግ እንደሚችል አለመጠናቱ ጉዳቱ መንግስትን ፍርሃት ውስጥ አስጥሞታል !!

የዘር ግጭት ከተነሳ መላው የብሄር ብሄረሰቦች አይኑን ወደ ትግራይ ተወላጅ ላይ እንደሚዳርግ የተለያዩ ጥናቶች ያመለክታል

የትግራይ ተወላጆች እና አመራሮች ይህንን ጠንቅቀው ስለሚያውቁት በህዝቦች ላይ ከፍተኛውን ግፍ እያደረጉ እንደሆነ ካለፉት አስር አመታት ወዲህ የሚያሳየው መረጃ ይጠቁማል !

(ዘ-ሐበሻ) የሕወሓት መንግስት በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ እንዲሁም በጎጃምና በጎንደር ሕዝብ ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ በመቃወምና በማውገዝ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፖሊ ግቢ ተማሪዎች የትግራይ ተወላጅ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን የሚያስጠነቅቅ ወረቀት ትናንት ለዛሬ አጥቢያ ተበትኖ ማደሩ ተሰማ::

 

ከዩኒቨርሲቲው አካባቢ የሚገኙ የዘ-ሐበሻ የዜና ምንጮች የተበተነውን ወረቀት ይዘት ልከውታል:: “ማስጠንቀቂያ ለትግራይ ተማሪዎች” ሲል የሚጀምረው ይኸው ደብዳቤ “በትግራይ የአገዛዝ ስር የወደቀችው አማራ በህዝቡ ላይ ሕወሀት ከፍተኛ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀመበት መሆኑን ደጋግመን መናገራችን ይታወቃል፡፡ነገር ግን መናገራችን እንደ በደል ተቆጥሮብን በደሉ እየገፋ መምጣቱን ሆን ብሎ አስቀጥሎታል፡፡ እኛም እናንተ የትግራይ ተማሪዎች አትዮጵያዊ ስሜት ይኖራችኋል ብለን በዝምታ ስንከታተላችሁ ብንቆይም እናንተ ግን የእኛ ሞት ለእናንተ ደስታ ሆኖላችሁ በ 19/06/09 ዓ.ም በባህር-ዳር ከተማ የሙዚቃ ድግስ አዘጋጅታችሁ ስትዘፍኑ መዋላችሁ የአማራ መሞት ለእናንተ ደስታ መሆኑን አረጋግጠናል፡፡” የሚለው ደብዳቤው በማስጠንቀቂያውም ካሁን በኋላ አማራው እየተገደለ በአማራው ክልል ላይ በሚደረጉ ማናቸውም የፈንጠዝያ ዝግጅቶች ላይ እርምጃ እንደሚወስዱ ይናገራል:: ተማሪዎቹም አማራውን ከሚያስቆጡና ከሚያሳዝኑ ነገሮች እንዲቆጠቡ ይመክራል”::

 

ይህን ተከትሎ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ፖሊ ግቢ የዘር ግጭት ይነሳል በሚል  ከፍተኛ ሥጋት መኖሩም የደረሰን መረጃ ያመለክታል::

 

በአማራው ክልል በአሁኑ ወቅት ወጣቶች ቤት ለቤት እየተለቀሙ ወደ ብር ሸለቆ እየተወሰዱ እንደሚሰቃዩ አንዳንዶችም በመድሃኒት እንደሚገደሉ በተደጋጋሚ ሲዘገብ የቆየ ጉዳይ ነው:: ሌሎች ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ የአማራ ተወላጆችም የት እንደደረሱ እንደማይታወቅ በተደጋጋሚ ተዘግቧል::

 

በተመሳሳይም በኦሮሚያ ክልል የሶማሌ ልዩ ፖሊስ በርካታ ኦሮሞዎችን በመግደል ላይ ይገኛል:: እንደዚህ ያሉት ዘር ማጥፋቶች ሲፈጸሙ የስርዓቱ ደጋፊዎች የገዳዩን የሕወሓት ስርዓት በዓል በጭፈራ ማክበራቸው ብዙዎችን እንዳሳዘነ በሶሻል ሚዲያዎች ከሚሰጡ አስተያየቶች መረዳት ይቻላል:: የትኛውም ሕዝብ ሕዝብ ሲገደል አብሮ መቆም እንዳለበት የሚመክሩት አስተያየት ሰጪዎች ሰዎች ከዘር ውጭ ማሰባቸውን አቁመው አንዱ በአንዱ ላይ ጥቃት ሲሰነዝር መቃወም አለበት የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ::

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on March 1, 2017
  • By:
  • Last Modified: March 1, 2017 @ 12:07 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar