www.maledatimes.com ኢትዮጵያዊው ፊቱን በተሸፈነ ነፍሰ ገዳይ መገደሉ ተሰማ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ኢትዮጵያዊው ፊቱን በተሸፈነ ነፍሰ ገዳይ መገደሉ ተሰማ

By   /   March 20, 2017  /   Comments Off on ኢትዮጵያዊው ፊቱን በተሸፈነ ነፍሰ ገዳይ መገደሉ ተሰማ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 22 Second

የሸቀጣሸቀጥ እና የምግብ ቤት ባለቤት የነበረው ግጠም ሽመልስ ደምሴ ፊቱን በሸፈነ እና ባልታወቀ ሰው መገደሉን የናሽቪል ፖሊስ አስታወቀ ፣የአርባ አንድ አመቱ ጎልማሳ ግጠም ከ፲ አመታት በላይ በናሽቪል ተነሲ የኖረ ሲሆን ሙሉ ህይወቱን በንግድ አለም እንደተሰማራ የናሽቪል ነዋሪዎች ገልጸዋል ።

ፖሊስ እንዳመለከተው ከሆነ ገዳዩ ፊቱን የሸፋፈነ ሰው እንደሆነ ከአይን እማኞች ገልጸዋል ፖሊስ እና የናሽቪል ተነሲ ነዋሪዎች ገዳዩን ለጠቆመ ገንዘብ ሊሰጡ እንደሚችሉ አክለው ገልጸዋል 

ግጠም ሽመልስ ደምሴ የናሽቪል አውራምባ !!
ግጠም ሽመልስ ደምሴን የማውቀው በ፪፲፻፱ አመተ ምህረት ወደ ናሽቪል ለመዛወር ባሰብኩበት ወቅት ነበር በጣም ቀና እና መልካም ሰው ፣ሰውን የማይጠግብ እና ስለ ስራውም ሆነ ስለ ስኬት አውርቶ የማይጠግብ ፣ ሰዎችን መርዳት እና እርሱ የሚሰራውን ስራ እንዲሰሩ መገፋፋት የሚችልበት ፣ገንዘብ ከሌላችሁም ድጋፍ አደርጋለሁ እያለ ጀምሮአት በነበረችው ሱቅ ውስጥ የተለያዩ ሸቀጣሸቀጦችን ፣ ስጋ እና ሌሎች ነገሮችን በመሸጥ ከሚተዳደርባት ሱቅ ውስጥ ማበደር የሚሻ ነው ። እኔም ከሃገርቤት የመጡ ሙዚቃዎችን ፣ሌሎች የሃገር ባህል ልብሶችን እና የእምዬ ኢትዮጵያ መለያ የሆነውን አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ባንዲራ ሸምቼ ከትንሿ ናሽቪል እንደ ባህር ወደተንጣለለው ከተማ ሽካጎ አመራሁ።
በወቅቱ ለንግድ የሚሆኑኝን ነገሮች በሙሉ ያለምንም ማወላወል እና ማንገራገር የምገዛውን ገዝቼ እንደ ሃገሬ ልምድ በእዳ የሚወሰዱትን ወስጄ ፣ ንግዱን ለማጧጧፍ ወሰድኩ ፣ሆኖም እንደ እድል ሆኖ የአለምኩትን ለማድረግ ባይቻለኝም በአቅራቢያ ላለው ማከፋፈያ ሱቅ አከፋፍዬ ፣ለግጠም የሚከፈለውን ገንዘብ በሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ መለስኩ ፣ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ጓደኝነታችን በረታ ጠነከረ ፣ለንግድ ያለውን ራእይ እኔም ውስጥ እንዲበቅል ማበረታታቱን ተያያዘው ግን አልተሳካለትም ነበር ።
እንዲህ ያለው ሰው የእራሱን ስኬት እና እራእይ በሰው ላይ መመልከት የሚሻ ታላቅ ሰው በ፪፻፩፭ በናሽቪል እንደገና የምግብ ቤት ከፍቶ ስራውን በሰፊው ጀመረ ይሄም እሰይ የሚያሰኝ ምግባር እንደነበር ሁሉም ሰው ያውቀዋል ፣በተለይም ናሽቪል ተነሲ እና መንፈስ ያሉ ወገኖች በሙሉ ግጠምን የማያውቁ የሉም ፣አትላንታም በተወሰኑ የንግድ ማእከሎች ስለ ግጠም መልካም እና ተግባቢ ጥሩ የንግድ አእምሮ ያለው እንደሆነ ይናገራሉ ፣ከተወለደባት ጎሃ ጽዮን ከተማም ስለ ግጠም ቢጠየቁ ሳቅ ጨዋታውን እና ሰርቶ ማደርን እንደሚወድ የሚገልጹ ናቸው ፣ታዲያ ይህ ግለሰብ ሰውን መርዳት የሚችል ከሆነ ለምንስ በሰው እጅ ሊጠፋ ቻለ ? ዛሬ እንደ እናቴ የሚንሰፈሰፍልኝ ግጠም ሞቅ ባለ ድምጹ ችካጎ እያለ የሚጸራኝ ጎርናናው ግጠም እስከ ዘለአለሙ አሸልቦአል፣
በአሁን ሰአት አብሮት ይሰራ የነበረውንም አሸናፊን አሰብኩት ምን አይነት የልብ ስብራት ይኖረው እንደሆነ ገመትኩት ፣የእኔን ድንጋጤ እና የልብ ህመም ስብራት ሳስብ ፣እኔ ይህንን አሰቃቂ ዜና ከሰማሁባት ደቂቃ እና ሰአት ጀምሮ ሙሉ ልሊቱን ማመን ባለመቻሌ ቁጭ ብዬ አደርኩ ፣ያ ደግነቱ ፊቴ ላይ ድቅን እያለ ጨዋታ እና ለዛው ፣እንግዳ ተቀባዩነቱ እየታወሰኝ ከልቤ አልጠፋ አለ፣ መቼም አሁንም ከልብ የሚጠፋ ስሜት ያለኝ አይመስለኝም ፣ ታዲያ አብረው ለዘመናት የኖሩት አብረው የሰሩት በንግድ ማእከሉ ውስጥ የተዝናኑት ናሽቪሎችስ እንዴት ይችሉት ይሆን ፣አስደንጋጩ የግጠምን ህይወት ማጣት ምንኛ ስሜትን ይጎዳል ። ብቻ የምለውም ቃል የለኝም ስሜቴ ዝብርቅርቅ እና ስሜት አልባ ጉዞ ላይ ነኝ ፣መጻፍም ያሰኘኝ እና መልሶ ይገታኛል ፣ብቻ ለቅሶ ብቻውን ትርጉም የለውም ቢሆንም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ የዚህን መልካም እና ታታሪ ወገናችንን ህይወትን ያጠፋውን ሰው ለፍትህ ለማቅረብ የእራሳችንን ጥረት እናድርግ ፣ይህ ነገ በኔ (ነግበኔ) የሚለውን የሃገራችንን ብሂል እያሰብን ብዙ ቤተሰቦቹን በመርዳት የሚታወቅውን ግጠምን አጥተነዋል ታዲያ ገዳዮቹን ግን ፈልጎም ቢሆን መጠቆም የሁላችንም ድርሻ ይሆን ዘንድ እላለሁ ዛሬን አስበን ሳንጨርስ ሞት እንደሚቀድመን እናስብ፣ ግን መልካምነት ማድረግ ዘለአለማዊ መታሰቢያነት ነው ። ግጠም ዘለአለም አስብሃለሁ !! ነፍስህን በገነት ያኑርልኝ ፣ለቤተሰቦችህ እና ለናሽቪል ነዋሪዎችም መጽናናትን እመኛለሁ !!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on March 20, 2017
  • By:
  • Last Modified: March 20, 2017 @ 3:21 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar