www.maledatimes.com የኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ ባለውለታን እንታደገው!! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ ባለውለታን እንታደገው!!

By   /   August 10, 2017  /   Comments Off on የኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ ባለውለታን እንታደገው!!

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 45 Second

(ጋዜጠኛ ሠለሞን ገመቹ ለማ)

በኢትዮጵያ ነፃ ፐሬስ ለረጅም ዓመታት የሠራው ጋዜጠኛ ግርማዬነህ ማሞ፤ በደረሰበት አሳሳቢ የጤና ችግር ምክንያት አንድ እግሩን አጥቷል፡፡ የግራ እግሩን ከጉልበቱ በላይ ባይቆረጥ ኖሮ ሕይወቱ በ48 ሰዓት ውስጥ ሊያልፍ ይችል እንደነበር በሐኪሞች ተነግሮት ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅትም በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ተዘነአ በሚባል የግል ሆስፒታል ሕክምናውን በመከታተል ላይ የሚገኘው ግርማዬነህ፤ አንድ በጎ ፍቃደኛ ግለሰብ ለጊዜው ባስያዙለት 10ሺ ብር አማካይነት የሕክምና እርዳታ ሊያገኝ መቻሉን ተናግሯል፡፡

ጋዜጠኛው ቁስሉ እስኪጠግለት በሆስፒታሉ የሚቆይ መሆኑን ገልጾ፤ እጅግ የሚያሳስበው ከሐምሌ 28 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 8 ቀን 2009 ዓ.ም ድረስ በሆስፒታሉ ለቆየባቸውና ለሚቆይባቸው ጊዜያት፤ የሚከፍለው ከ30 ሺ ብር በላይ የሚሆን የሕክምና አገልግሎት ወጪ እንዴትና በማን ሊሸፈን እንደሚችል ብቻ ሳይሆን፤ ምንም ዓይነት ገቢ የሌለው ከመሆኑ አኳያ ወደፊት ለአርተፊሻል እግርና ለክራንች የሚሆነውን ገንዘብ ከየት ላገኝ እችላለሁ የሚለው ጉዳይ መሆኑን አሳውቋል፡፡

በኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ ታሪክ ስመ ጥሩ በሆኑት በርካታ ጋዜጦችና መጽሔቶች ላይ በአዘጋጅነትና በከፍተኛ ዘጋቢነት የሠራው ግርማዬነህ፤ በአቶ ክፍሌ ሙላት ይመራ የነበረው የኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ ጋዜጠኞች ማኅበር አባል ሲሆን በሕዝብ ዘንድ ተነባቢና ተወዳጅ መሆን በቻሉት የኢትኦጵና የዓባይ ጋዜጣና መጽሔት ዝግጅት ክፍል ከፍተኛ የዘጋቢነትና የአዘጋጅነት ድርሻውን ሲወጣ የቆየ መንፈሰ-ብርቱ ጋዜጠኛ ነበር፡፡
ጋዜጠኛ ግርማዬነህ ማሞ ከኢትኦጵና ከዓባይ በተጨማሪ፤ በጦማር፣ በኢትዮ ታይም፣ በታዛቢ ጋዜጦች፤ እንዲሁም በትውልድ ጋዜጣና መጽሔት ላይ በዘጋቢነትና በቃለ-መጠይቅ አቅራቢነት ሠርቷል፡፡ በጉራማይሌ መጽሔትም ላይ በአዘጋጅነትና በዘጋቢነት የሠራው ግርማዬነህ፤ በመጨረሻም በሐምራዊ እና በዕንቁ መጽሔቶች ላይ ከፍተኛ አዘጋጅ በመሆን መጽሔቶቹ በአንባቢያን ዘንድ ተፈላጊና ተወዳጅ እንዲሆኑ ሙያዊ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡

በአንጋፋው የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ከዶክተር ታዬ ወልደሰማያት ጋር በመሆን የመምህራን ማኅበሩን ልሳን ሲያዘጋጅ የነበረው ግርማዬነህ ከፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም እና ከሟቹ ዶክተር መኮንን ቢሻው ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በመከላከልና በማጋለጥ ረገድ የበኩሉን ዜግነታዊ ድርሻ ተወጥቷል፡፡ የጦማር ጋዜጣ አዘጋጅ በነበረበት ጊዜ ከአንድ ዓመት በላይ ታሥሮ የነበረው ጋዜጠኛ ግርማዬነህ ባለትዳርና የአንዲት ሴት ልጅ አባት ነው፡፡ ጋዜጠኛው ዛሬ በተዘነዓ ሆስፒታል ሕክምናውን በመከታተል ላይ የሚገኝ ሲሆን ምንም ዓይነት ገቢ የሌለው በመሆኑ የኢትዮጵያውያን ወገኖቹን ዕርዳታ ይፈልጋል፡፡ ጋዜጠኛ ግርማዬነህ ማሞ ከ1983 ግንቦት ወር በፊት የኢትዮጵያ ሠራዊት ባልደረባ ነበር፡፡
ጋዜጠኛ ግርማዬነህ እግዚአብሔር ይማርህ! ማለት ለምትፈልጉ፡- በስልክ ቁጥር 0911 12 25 29 ወይም በባለቤቱ በሽብሬ ጥሩነህ በ09 20 00 74 16 ልታገኙት ትችላላችሁ፡፡
ግርማዬነህን ለመርዳት፡-
ወይዘሮ ሽብሬ ጥሩነህ አቢሲኒያ ባንክ አዲሱ ገበያ ቅርንጫፍ የአካውንት ቁጥር 1749501001155 በሚለው ይጠቀሙ፡፡

Image may contain: 1 person, standing and sunglasses

Image may contain: 1 person

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on August 10, 2017
  • By:
  • Last Modified: August 10, 2017 @ 9:36 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar