www.maledatimes.com “የቴዲ አፍሮ አልበም ምረቃ እገታ የእኔ ስህተት አይደለም” ጆርካ ኢቨንት ኦርጋናይዘር - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

“የቴዲ አፍሮ አልበም ምረቃ እገታ የእኔ ስህተት አይደለም” ጆርካ ኢቨንት ኦርጋናይዘር

By   /   September 6, 2017  /   Comments Off on “የቴዲ አፍሮ አልበም ምረቃ እገታ የእኔ ስህተት አይደለም” ጆርካ ኢቨንት ኦርጋናይዘር

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 6 Second

? “የቴዲ አፍሮ አልበም ምረቃ እገታ የእኔ ስህተት አይደለም” ጆርካ ኢቨንት ኦርጋናይዘር

ቴዲን ጨምሮ በዝግጅቱ ላይ እንዲታደሙ የተጠሩት 900 ናቸው…
እነሆ ዝርዝሩ…

በቴዲ አፍሮ የሲዲ አልበም ምርቃት ክልከላን በተመለከተ አንዳንድ የማህበራዊ እና የመገናኛ ብዙሀን ሚድያዎች ጉዳዩን እኔላይ ማላከካቸው አግባብ አይደለም ሲል ጆርካ ኢቨንት ለሁሉ አዲስ ተናገረ፡፡

የቂርቆስ ክፍለከተማ ፖሊስ መምርያ ሀላፊ ምክትል ኮሚሽነር ሽመልስ ሽፈራው ለቁምነገር መፅሄት እንደተናገሩት ለሙዚቃ ድግሶች እና ከ1000 ሰው በላይ ለሚታደምበት ፍቃድ ከአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ይህን ጉዳይ በተመለከት ከተቋቋመው ክፍል ማምጣት አለበት።

ይሁን እና የምርቃቱ አስተባባሪ የነበረው ጆርካ ኢቨንት ሀሙስ እለት የጥበቃ አካል እንዲመደብላቸው በጠየቁበት ወቅት ፈቃድ ማምጣት አይጠበቅብኝም በማለት እንቢኝ ብሏል ይላሉ።

ሁሉ አዲስም የጆርካን የስራ ሀላፊዎች ስለጉዳዩ አነጋግሯል፡፡ በድግሱ ላይ እንዲታደሙ ጥሪ የተላለፈላቸው ቴዲ አፍሮን ጨምሮ 900 ሰው ብቻ ነው ለዚህም 680ሺ ብር የከፈልንበት ደረሰኝ በእጃችን ይገኛል ይላሉ፡፡

ከዚህ ሌላም ባለፏት አመታት የሲዲ ምርቃትን ጨምሮ 9 ፕሮግራሞች ስናዘጋጅ ምን ማሟላት እንዳለብን በሚገባ እናውቃለን ያሉት አስተባባሪዎቹ የማዲንጎ አፈወርቅ፣ የልጅ ሚካኤል፣ እንዲሁም የቴዲ አፍሮን ጥቁር ሰው አልበም (2ሺህ ሰው የተገኘበት በሂልተን) ስናስመርቅ ፍቃድ አልተጠየቅንም ብለዋል።

ከዚህ በላይ ከ2ሺ በላይ ሰው የታደመባቸው የቫላንታይን ፕሮግራም በሀርመኒ እና ሌሎችም ዝግጅቶች አዘጋጅተናል ይሁን እና ተመሳሳይ ጥያቄ ተነስቶልን አያውቅም ነው የሚሉት፡፡

አስቸኩዋይ ጊዜ አዋጁ ሐምሌ 28 ከመነሳቱ አኳያ ለምረቃው ምንም አይነት ፈቃድ አያስፈልገውም ነው የሚሉት።

ይሁን እና ሌላ ከጉዳዩ ጋር የማይገናኝ ነገር አንዳንድ ሚድያዎች እየፃፏ የሚገኙ ሲሆን እውነታው ግን ከላይ የተገለፀው ነው ብለዋል ሀላፊዎቹ።

ሁሉ አዲስ ማክሰኞ ነሀሴ 30,2009 ዓ.ም

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar