www.maledatimes.com የጌትሽ ማሞ የፈጠራ ስራ ዘረፋ እና የታደሰ ገለታ እሮሮ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የጌትሽ ማሞ የፈጠራ ስራ ዘረፋ እና የታደሰ ገለታ እሮሮ

By   /   September 9, 2017  /   Comments Off on የጌትሽ ማሞ የፈጠራ ስራ ዘረፋ እና የታደሰ ገለታ እሮሮ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 4 Second

ጥያቄ አለኝ ለ#ጌትሽ ማሞና ለ#ሔለን በርሄ

# # # ***# # # 

#ጌትሽ ” ፎቷችን ይመስክር” የሚለውን የመጀመሪያ ህን ሲንግል ዘፈን ግጥም ከፃፍኩልህ ቀን አንስቶ  በኔና ባንተ መሀል የነበረው ጥልቅ ጓደኝነት ገመዱ ተበጥሶ እንድንቆራረጥ ያደረገንን የሄለን በርሄን  “አታስፈራራኝ” የሚለውን ዘፈን የሰራን ቀን አንተ ቤት ሆነን  ዜማ ለመስራት ኦርጋንህን ይዘህ ያመጣሁትን ግጥም ሳነብልህ የነበረህን  አድናቆት ትረሳዋለህ? በተለይ ፦ ” አንተን ካጣሁ መኖር የማልችል ፣

ነፍሴ በእጅህ  ያለች ይመስል። የሚለውን አገላለፅ ወደኸው ስንት ጊዜ ደጋግመህ በቃልህ  ስትለው  እንደነበረስ ይረሳሀል? እኔ ግን እነማን እንደነበሩ እንኳን ላስታውስህ እችላለው ።  እሺ ዘፈኑን ሰርተን ከጨረስን በኻላ አንተ የሰራህላትን ሌላ ዘፈን ጨምሬ ሁለቱንም በእኔ እጅ ፅሁፍ ቁልጭ አርጌ ” አታስፈራራኝ” ዜማ “ጌትሽ ማሞ” ፣ግጥም ታደሰ ገለታ ” ብለን ፅፈን ” ነገ እሰጣታለው” ብለኸኝ እንደነበረስ እሱም ይረሳሀል ?  በእርግጥ ያስጠናሀት ቀን ” አታስፈራራኝ” እያለ ያልቅ  የነበረው ግጥም ላይ ” ከበቃህ ይብቃኝ ” የሚል ቃል እንደጨመርክበት ባልክድም  እሱንም ለዜማው ውበት ብለህ እንጂ ግጥሙ ጉድለት ኖሮበት እንዳልሆነ የነገርከኝንስ አታስታውሰውም ? እውነት ትረሳዋለህ?

ታዲያ ከዚች ቃል ውጪ ሙሉ ግጥሙ የኔ በሆነው ስራ .ሲዲው ላይ ስምህን ከኔ ስምጋ ( ያውም ያንተን ስም ከፊት አድርገህ ) መለጠፍህ ሳያንስ ስንት ጊዜ  በሚዲያ እንግዳ ሆነህ ስለዚህ ዘፈን በተጠየክ  ቁጥር  አንድም ቀን እንኳን የኔን ስም አለማንሳትህ ሕሊናህን አይሞግተውም ? ” ግጥሙ የታደሰ ገለታ ነው ” ማለቱ ቢቀር እንኳን ” የታደሰም ተሳትፎ አለበት ማለቱ ማንን ገደለ? አንድ ሰው የእራሱ  ያልሆነውንና ያልወለደውን  ልጅ.. ያውም አባቱ እያለ አንድ ከረሜላ ስለሰጠው ብቻ  የኔ ልጅ ነው ብሎ በኔ ስም ብቻ  ካልተጠራ ለማለት የህሊና ሞራልስ ይኖረዋልን? ይሄ ጥያቄዬ ለዚህ ዘፈን ብቻ ሳይሆን የሜላት ኮድ እና የሳሚ  በየነን ዘፈን ግጥምም ይጨምራል።

**** ### *** ##

#ሔለን በርሄ በእርግጥ እኔና አንቺ ባካል ተገናኝተን ባናውቅም ፤ ስራው እጅሽ የገባው በጌትሽ  በኩል ቢሆንም ፤ አልበምሽ ሊወጣ በተቃረበ ጊዜ እኔጋ ደውለሽ ” ጌትሽ ግጥሙን ጌትሽና ታደሰ ብለሽ አፅፊ አለኝ! እጄ ላይ ያለው ወረቀት ላይ ግን ግጥም ታደሰ ገለታ ስለሚል ግራ ገብቶኝ ነው” ብለሽ ስትነግሪኝ በጣም ገርሞኝ “እውነት ጌትሽ እንደዛ ካለሽ የኔን ስም ተይውና በእሱ ስም ብቻ አድርጊው የኔ ስም  እንዲፃፍ  አልፈልግም ይቅርብኝ ስልሽ  ” ግጥሙ ያንተ እንደሆነ እርግጠኛ ብሆንም ለኔ የሰጠኝ እሱ ስለሆነና ካሴቴ ሊወጣ ስለሆነ ለኔ ስትል ተስማሙልኝ በ.እ.ና.ት.ህ .” እያልሽ እንደለመንሽኝ ተረስቶሽ ነው ዛሬ ከጌትሽ ጎን ስትቀመጪ የእሱ ስራ እንደሆነ እርግጠኛ ሆነሽ በሙሉ አፍሽ የምትናገሪው? አንቺ እኮ የመጣልሽን ተቀበልሽ እንጂ ዘፈኑ ሲሰራ ከእኛጋ  አልነበርሽም !!! ምን የምታውቂው እውነት አለ?

ታዲያ ዛሬ” አታስፈራራኝ” ግጥሙ የጌትሽ ነው ብለሽ አፍሽን ሞልተሽ የምትናገሪ ከሆነ ሲዲሽ ላይ የኔ ስም ምን ሊያድርግ ገባ? ማን ፃፈው ? እጅሽ ላይ  የነበረው ወረቀት ” ታደሰ ገለታ እንደሚልና ግጥሙም የጌትሽ እንዳልሆነ የሚያውቁ ጓደኞችሽ እንደነገሩሽ ፤ አንቺም እራስሽ ባንደበትሽ የእሱ ግጥም እንዳልሆነ ያስታውቃል” ብለሽ ያመንሽልኝን እውነት ዛሬ ከእሱ ጎን ስትቀመጪ እረስተሽው ነው የኔን ስም ማንሳት  ያልፈለግሽው ? ሄለን 2 ተቃራኒ ነገሮች  አብረው  አይሄዱምና  ወይ ሕሊናሽን አምነሽ  ዝም  በይ ..ወይ ስሜን  ከሲዲሽ  ላይ ፍቀሽ  አጥፊው፡ አንደበት  የካደው ስም ሲዲሽ ላይ  ተፅፎ  ምን  ይሰራልሻል ?

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar