www.maledatimes.com አንድ ዓመት 365 ¼ የተባለው ለምንድን ነው? ፣ ጷጉሜ የተባለችው ወርስ ከየት መጣች? - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አንድ ዓመት 365 ¼ የተባለው ለምንድን ነው? ፣ ጷጉሜ የተባለችው ወርስ ከየት መጣች?

By   /   September 10, 2017  /   Comments Off on አንድ ዓመት 365 ¼ የተባለው ለምንድን ነው? ፣ ጷጉሜ የተባለችው ወርስ ከየት መጣች?

    Print       Email
1 0
Read Time:1 Minute, 46 Second

::::::::::::::::::::::::::::
ብዙዎቻችን ስለ ዓመት ስንናገርና ለልጆቻችን ስናስተምር
አንድ ዓመት 365 ¼ ቀንት፣ 52 ሳምንታት እና 12 ወራት
በማለት እንናገራለል፡፡ እውነትም ልክ ነው፤ ነገር ግን 365
¼ ማለት ምን ማለት ነው? ¼ የሚባል ቀን አለን? 12
ወራት በሠላሳ በሠላሳ ቀናት የተከፋፈሉ ሆነው
ድምራቸው 12X30 = 360 ነው፡፡ ታዲያ 5ቀናት እና ¼
የተባለው ከየት መጣ? ጷጉሜስ የተባለችው ወርስ ከየት
መጣች? ለሚባሉትን ጥያቄዎች አስተዋዮች ይጠይቃሉ፡፡
ቀደምት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ግን እንደሚከተለው
ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ አስቀምጠውልናል፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
በአንድ አመት ዉስጥ ስንት ወቅቶች አሉን ከተባለ አራት
ናቸው፡፡ እነሱም ክረምት(ከሰኔ26- መስከረም25)፣
መፀው/መከር(ከመስከረም26- ታኅሣሥ25)፣ በጋ/ሐጋይ
(ከታኅሣሥ26 – መጋቢት25)፣ ጸደይ/በልግ
(ከመጋቢት26 – ሰኔ25) ነው፡፡ እያንዳንዱ ወቅት ደግሞ
ሦስት ወራትን ይዟል፡፡ 3X30=90 ነው፡፡ 90 ሲባዛ በ4
ደግሞ 360 ነው፡፡ እንግዲህ የስሌቱ ነገር የሚጀምረው
እዚህ ላይ ነው፡፡
::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
:::::::::::
ከላይ አንድ ወቅት 90 ቀን ሳይሆን 91 ቀን 7ሰዓት እና
30 ደቂቃ ነው፡፡ ይህ የሚሆነው የየወሩ ቀን ማጠር እና
መርዘምን ተከትሎ በሚመጣ ልዩነት ነው፡፡ ለምሳሌ
መስከረም ላይ 12 ሰዓት አይመሽም ብርሃን ነው፡፡
ታኅሣሥ ላይ ግን 12 ሰዓት ጭልምልም ይላል፡፡ ሌሊቱም
ረዥም ነው፡፡ ለምሳሌ እነዚህ ቀረቡ እንጂ እያንዳንዱ
ወር የተለያየ ልዩነት አለው፡፡ ስለዚህ ጠቅላላውን
አራቱንም ወቅቶች ስንደምራቸው የምናገኘው ውጤት
አንድ ዓመትን ያስገኙልናል፡፡
ክረምት 91 ቀን 7 ሰዓት ከ30 ደቂቃ
መፀው 91 ቀን 7 ሰዓት ከ30 ደቂቃ
በጋ/ሐጋይ 91 ቀን 7 ሰዓት ከ30 ደቂቃ
ጸደይ 91 ቀን 7 ሰዓት ከ30 ደቂቃ
:::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
ጠቅለል አድርገን ስንደምረው ዘጠና ዘጠናው ቀን
ስንደምረው 90 X 4 = 360 ይሆናል፡፡ ይህ የአሥራሁለት
ወሩን ያዘ ማለት ነው፡፡
::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
የየወቅቱን አንዳንድ ቀን ስንደምር 1 X 4 = 4 ይሆናል፡፡
ይህ የጷጉሜ አራቱ ቀናት ናቸው፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የቀሩትን 7 ሰዓት እና 30 ደቂቃዎች ስንደምራቸው 30
ሰዓት ይመጣል፡፡ ወደ ዕለት ሲቀየር 1 ቀን እና 6 ሰዓት
ይሆናል ማለት ነው፡፡ ከላይ ካገኘነው 4 ጋር ሲደመር 5
ቀናት እና 6 ሰዓት ይሆናል ማለት ነው፡፡
::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
በጠቅላላ አንድ ዓመት 365 ከ6ሰዓት ወይም ¼
የሚባለው ለዚህ ነው ይህ ስድስት ሰዓት በአራት ዓመት
አንድቀን ሆኖ ጷጉሜ ስድስት እንድትሆን ያደርገዋል፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ጷጉሜ የግሪክ ቃል ነው በእና ተውሣከ ውርኅ ትባላለች
ማለት የወር ጭማሪ ወይንም ትርፍ ወር የተባለችው
ለዚህ ነው፡፡ ይህቺ ወር በ600 ዓመት 7 ትሆናለች ነገር
ግን ሊቃውንት ይቺን የትርፍ ትርፍ ናትና ከስሌት ውጪ
የማይኖርባት በማለት ይገልጧታል፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡ምንጭ ፡ – (በአለቃ እፁብ ማናዬ)

<<የመጨረሻዋ እሁድ መልካም የ 2009 ዓ.ም መሰናበቻ እና የ 2010 ዓ.ም መቀበያ ቀን ትሁንለልን!!>>

Happy
Happy
100 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar