www.maledatimes.com በመዲናችን የሚገኙ ጥንታዊ ቤቶችና የነዋሪዎቻቸው ህልውና አደጋ ላይ ነው ፣ ድንገት ሊፈርሱ ይችላሉ ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

በመዲናችን የሚገኙ ጥንታዊ ቤቶችና የነዋሪዎቻቸው ህልውና አደጋ ላይ ነው ፣ ድንገት ሊፈርሱ ይችላሉ !

By   /   October 10, 2017  /   Comments Off on በመዲናችን የሚገኙ ጥንታዊ ቤቶችና የነዋሪዎቻቸው ህልውና አደጋ ላይ ነው ፣ ድንገት ሊፈርሱ ይችላሉ !

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 2 Second
የአፈ-ንጉሥ ነሲቡ መስቀሎ ቤት
ቢቢሲ እንደዘገበው
አጭር የምስል መግለጫበዚህ በአፈ-ንጉሥ ነሲቡ መስቀሎ ቤት ውስጥ በርካቶች ይኖራሉ በማንኛውም ሰዓት ቤቱ ሊደረመስ እንደሚችል ባለሙያዎች ያስጠነቅቃሉ

አዲስ አበባ ከተማ ከተመሰረተችበት ጊዜ አንስቶ ባሳለፈቻቸው ዘመናት የበርካታ ታሪካዊ ቅርሶች ባለቤት ሆናለች። ከእነዚህም መካከል በከተማዋ የሚገኙት ጥንታዊና ታሪካዊ ቤቶች ተጠቃሽ ናቸው።

ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተገኙ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ በከተማዋ ውስጥ ከ230 ያላነሱ በቅርስነት የተመዘገቡ ቤቶች ያገኛሉ። እነኚህ ጥንታዊ ቤቶች ባላቸው ታሪክ፣ የሥነ-ህንፃ ውበት፣ ማህበራዊ ጠቀሜታዎችና ካላችው ረጅም እድሜ አኳያ በቅርስነት የተመዘገቡ ናቸው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የባህልና ቱሪዝም ቢሮም በከተማዋ ውስጥ የሚገኙትን ቅርሶችን የመጠበቅ፣ የመንከባከብና የማሳወቅ ስልጣንና ሃላፊነት ተሰጥቶታል።

ነገር ግን ተዘዋውረን እንደተመለከትነው በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ የበርካታ ጥንታዊና ታሪካዊ ቤቶች ህልውና አደጋ ላይ ይገኛል። ከነዚህም መካከል ፈረንሳይ ለጋሲዮን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው የልዑል ራስ ሥዩም መንጋሻ ቤትና ሳንፎርድ ት/ቤት ጀርባ የሚገኘው የአፈ-ንጉሥ ነሲቡ መስቀሎ ቤት ያሉበት ይዞታ እጅግ አሳሳቢ ነው።

በአሁኑ ወቅት በሁለቱም ቤቶች ውስጥ በርካታ ሰዎች እየኖሩ ይገኛሉ። ከዚህም በላይ አስቸኳይ ጥገና ካልተደረገላቸው የቤቶቹም ሆነ የነዋሪዎቹ ህልውና አደጋ ላይ ይገኛል።

የአምስት ልጆች እናት የሆነችው ወ/ሮ መሰረት ቶላ በአፈ-ንጉሥ ነሲቡ መስቀሎ ቤት ውስጥ ከሰላሳ ዓመትታ በላይ እንደኖረች ትናገራለች።

ደርግ ሥልጣን ላይ በነበረበት ወቅት ለወላጆቿ የቤቱ የኋለኛ ክፍል እንደተሰጣቸውና ከዛን ጊዜ ጀምሮ በቤቱ ውስጥ ስትኖር እንደቆየች የምትናገረው ወ/ሮ መሰረት፤ አሁን አሁን ”ዝናብ ሲዘንብ እንቅልፍ የለኝም! ቤቱ በእኔና በልጆቼ ላይ አንድ ቀን ይደረመሳል በሚል ሥጋት ነው የምኖረው” ትላለች።

በመዲናችን የሚገኙ ጥንታዊ ቤቶችና የነዋሪዎቻቸው ህልውና አደጋ ላይ ነው

በልዑል ራስ ሥዩም መንጋሻ ቤት የሚኖሩ ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሆነ፤ ለወረዳቸውና ለአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ተቀያሪ ቤት እንዲሰጣቸው ማመልከታቸውን፤ ይሁን እንጂ እሰካሁን ምንም ነገር እንዳልተፈጸመ ነግረውናል። ነዋሪዎቹ ቤቱ ብዙ ታሪክ እንዳለው ይረዳሉ፤ ቅርሱም ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ይፈልጋሉ። ይሁን እንጂ እዚህ የሚኖሩት ሌላ አማራጭ ስላጡ እንደሆነና አማራጭ ካገኙ ታሪካዊውን ቤት ለመልቀቅ ፍቃደኛ ናቸው።

የሥነ-ህንፃ ባለሙያና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ፋሲል ጊዮርጊስ እንደሚሉት ”ጥንታዊ ቤቶቹ የተገነቡት ከእንጨትና ከጭቃ ነው። ከእድሜያቸውና ከአስራራቸው አንጻር ቤቶቹ ብዙ መሸከም አይችሉም።

ይሁን እንጂ አሁን በቤቶቹ ውስጥ በርካታ አባዎራዎች እየኖሩ ይገኛሉ። ይህ ማለት ደግሞ በማንኛውም ሰዓት ቤቶቹ ሊደረመሱና ጉዳት ሊያደረሱ ይችላሉ” በማለት ሥጋታቸውን ይገልፃሉ። ስለዚህ ነዋሪዎቹን ወደ ሌላ ቦታ በማዘዋወር የቤቶቹን ታሪካዊነት መጠበቅ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

ፋሲል ጊዮርጊስ ስለ ጥንታዊ ቤቶች ይናገራሉ

በሌላ በኩል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የባህልና ቱሪዝም ቢሮ የቅርስ ቁጥጥርና ኢንቨንተሪ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ደርጄ ሥዩም እንደሚሉት ቢሮው በከተማዋ ለሚገኙ ቅርሶች ጥበቃና ጥገና እንደሚያደርግ፤ ይሁን እንጂ ከብዛታቸው የተነሳ ለሁሉም በአንድ ጊዜ ጥበቃና እንክብካቤ ማድረግ አለመቻሉን ይናገራሉ።

አቶ ደረጄ እንደሚሉት ቢሮው ከፍተኛ ጉዳት ላይ የሚገኙ ቤቶችን ለመጠገን የዲዛይን ሥራው እየተጠናቀቀ መሆኑን ተናግረዋል። ቤቶቹን ለማደስ ሥራ ከመጀመሩ በፊት ግን የማጣራትና ለነዋሪዎቹ ተለዋጭ ቤት በማስፈለጉ ረጅም ጊዜ መጠየቁን ገልፀዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

♦ “ ትክክለኛ ፍትሕ አይሰጡም” የተባሉት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ከችሎት እንዲነሱ ተጠየቀ !

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar