www.maledatimes.com “ነን ሶቤ (ዋሸሁ እንዴ?) ” ይላል የአምቦው ፈርጥ ሃጫሉ ክንፉ አሰፋ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

“ነን ሶቤ (ዋሸሁ እንዴ?) ” ይላል የአምቦው ፈርጥ ሃጫሉ ክንፉ አሰፋ

By   /   December 10, 2017  /   Comments Off on “ነን ሶቤ (ዋሸሁ እንዴ?) ” ይላል የአምቦው ፈርጥ ሃጫሉ ክንፉ አሰፋ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 14 Second

ን ሶቤ (ዋሸሁ እንዴ?” ይላል የአምቦው ፈርጥ ሃጫሉ

ክንፉ አሰፋ

        “ዋሸሁ እንዴ?” (ነን ሶቤ)  ሲል ይጠይቃል፣ ድምጻዊ  ሃጫሉ ሁንዴሳ። ይህንን ጥያቄ የሚያቀርበው ለታዳሚው ሕዝብ አይደለም። በአስር ሺዎች የታደሙበት የኮንሰርት አዳራሽ  ውስጥ ከታዳሚው ፊት-ለፊት ለተቀመጡት ለእነ አባዱላ ገመዳ፣ ወይንም ደግሞ ለእነ ለማ መገርሳ ይመስላል።ከፍ ሲል ደግሞ ኮንሰርቱን በቀጥታ ስርጭት እየተከታተሉ ላሉት የአድዋ ባለ ግዜዎች የቀረበ ጥያቄ ነው።   

        ይህ ድምጸ-መረዋ ወጣት በምርጥ ቅላፄውያንጎራጎረው ፉከራ እና ዜማ እጅግ ያስደምማል። ማስደመሙ እውነትን በመድረክ ላይ መዘርገፉ አይደለም። ከራሱ ደህንነት ይልቅ የወገኑን ስቃይ እና ሰቆቃ በማስቀደሙ ነው። እንዲህ አይነቱ እውነትን አደባባይ ወጥቶ በድፍረት የመናገር  ገት የነበረው ቴዲ አፍሮ ነበር። ይህንን በማድረጉም  በአንባገነኖቹ ጥርስ ውስጥ ገብቶ ብዙ ቢያስከፍለውም፣ ከህዝብ ልብ ውስጥ ሊወጣ አልቻለም።   

                በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ፣ትላንት ምሽት የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመርዳትየኦሮሞ ሙዚቀኞች ማህበር ባተዘጋጀው “ወገንለወገን” ኮንሰርት ላይ ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳመድረኩን ጠቆጣጥሮት ነበር። የሕዝቡን ስሜት እየኮረኮረ፣ ብሶቱን በአደባባይ ዘርግፎታል።  ጠንከር ባሉ ቃላት የተቃኘው ስንኝ ከውብ ድምጽና ቀስቃሽ ዜማ ጋር ታጅቦ ሲቀርብ ልዩ ስሜትን ፈጥሮ ነበር። ይህ ዜማ በቀጥታ ስርጭት ሲተላለፍ በአዳራሹ የነበረው ድባብ እጅግ ይደንቃል። ሃጫሉ ይጠይቃል፣ ታዳሚው ስሜቱን በጩኸት ይገልጻል።  የኦሮሞኛ ቋንቋ ባልችልና የሚለውን ነገር ባልረዳ ኖሮ ይጸጽተኝ ነበር። ይህ ወጣት ድምጻዊ መድረኩን ተቆጣጥሮ ይዞ እንዲህ ይል ነበር፤

Geerar geerar naan jettuu

Dhiirri geeraree hin quufne

Hidhaa qaallitti jiraa

Dhiirri geeraree hin quufne

Hidhaa qilinxoo jiraa

Dhiirri geeraree hin quufne

Hidhaa karchallee jiraa

Karchallee Amboo jiraa…

 

ይህ ስንኝ በካፊል ወደ አማርኛ ሲመለስ፤

 

ሸልል ሸልል ይሉኛል

ምኑን ልሸልል እኔ

ቂልንጦ አይደለም ወይ

ቃሊቲ አይደለም ወይ

ከርቸሌ  አይደለም ወይ

አምቦ ከርቻሌ  አይደለም ወይ…

መኖርያው የወገኔ

 

የፈረሶቻችንን ዝና፣

የጀግኖቻችንን ዝና

አድዋ ላይ ይንገረና!

መቀሌ ላይ ይነገር!

አብሮ መኖር ይሻላል ብለን…

መከባበር ይሻላል ብለን…

እስከዛሬ ታግሰናል…

ከእንግዲህ ግን ይበቃናል!” ይለል ሃጫሉ።

        እስር ቤቱ ሁሉ አፋን አኦሮሞ ይናገራል ሲሉ እነ ስዬ አብርሃ እንኳን የመሰከሩለት ጉዳይ በመሆኑ ይመስላል ሃጫሉ በመሃል እንደ አዝማች፣  “አይደለም እንዴ? ዋሸሁ እንዴ? (ነን ሶቤ?)” የሚለው የአለምዬ ጌታቸውን ስንኝ  የሚያክልበት። በቃሊቲ፣  በቂሊንጦ፣ በከርቸሌ፣… እየማቀቁ ያሉ የሕሊና  እስረኞች ጉዳይ ከራሱ ደህንነት በላይ ስላስጨነቀው ይህችን አጋጣሚ መጠቀም ነበረበት። 

        ይህ የጥበብ ሰው ከርቸሌን በወሬ ሳይሆን በተግባር ያውቃታል። የአድዋ፣ የመቀሌ የሚላቸው ጥጋበኞች አምቦ ላይ አስረውት ለሁለት አመት አሳቃይተውታል። ለእስር እና ለዱላ ያበቃው ወንጀሉ መብቱን ማቀቁ ነበር።        በወሩ መጨረሻ ላይ በጊዮን ሆቴል ያዘጋጀው ኮንሰርትም በወያኔ ካድሬዎች ተሰርዞበታል።

        ተከባብረን አብረን እንኑር ያሉ የኦሮሞ መሪዎች፤ እነ ፕ/ር መረራ ጉዲና፣ እነ በቀለ ገርባ በአድዋ ልጆች የግፍ ብትር እየተመቱ ነው።  አድዋዎቹ ይህንን መከባበር እንደፍርሃት ከወሰዱት፣ መከባበሩ ካሁን በኋላ ያበቃል የሚል መልዕክት ነው ሃጫሉ ያስተላለፈው።

        ይህ የሃጫሉ ስራ፣ አትሌት ለሊሳ ፈይሳ በአሎምፒክ በድረክ ከፈጸመው ጀብዱ አይተናንስም። እርግጥ ነው። አትሌት ለሊሳ አለም አቀፍ ትኩረትን ስቦ ነበር።       ሃጫሉ ግን መልዕክቱን ሲያስተላልፍ በአንባገነኖቹ ጉያ ሆኖ፣ ሊመጣበት የሚችለውን ነገር ሁሉ ተጋፍጦ ራሱን ለመስዋ እትነት ያዘጋጀ ጀግና ነው።

        ይህንን አድርጎ ቢታሰርም ፣ ታሪክ ሰርቷልና ምን ግዜም አይቆጨውም። የግዜ ጉዳይ እንጂ አንባገነኑ ስርዓት ይሄዳል የሃጫሉ ስራ ግን ምንግዜም ይዘከራል።  

        ሙዚቃውን  ለመመልከት ይህን አስፈንጣሪ ይጫኑ፣

 https://youtu.be/bH61mCEclSw

         

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

♦ “ ትክክለኛ ፍትሕ አይሰጡም” የተባሉት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ከችሎት እንዲነሱ ተጠየቀ !

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar