www.maledatimes.com ግልፅ ደብዳቤ ለአርቲስት ዘለቀ ገሰሰ :- ብዙ ዜጎች በሚሞቱባት ሀገር ፓርቲዎችን በሴራ እያፈረሱ ለአገዛዙ እድሜ ማራዘሚያነት እንዲውሉ መስራት ግን ታሪክ ይቅር የማይለው ሀገራዊ በደል ነው። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

ግልፅ ደብዳቤ ለአርቲስት ዘለቀ ገሰሰ :- ብዙ ዜጎች በሚሞቱባት ሀገር ፓርቲዎችን በሴራ እያፈረሱ ለአገዛዙ እድሜ ማራዘሚያነት እንዲውሉ መስራት ግን ታሪክ ይቅር የማይለው ሀገራዊ በደል ነው። 

By   /   January 2, 2018  /   Comments Off on ግልፅ ደብዳቤ ለአርቲስት ዘለቀ ገሰሰ :- ብዙ ዜጎች በሚሞቱባት ሀገር ፓርቲዎችን በሴራ እያፈረሱ ለአገዛዙ እድሜ ማራዘሚያነት እንዲውሉ መስራት ግን ታሪክ ይቅር የማይለው ሀገራዊ በደል ነው። 

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 14 Second
Image may contain: 3 people, people standing and outdoor

ግልፅ ደብዳቤ ለአርቲስት ዘለቀ ገሰሰ
ጉዳዩ:- ፓርቲያችንን አላማውን ለማሳት የሚያደርጉትን ተግባር እንዲያቆሙ ስለማሳሰብ

ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የድርሻውን ሃላፊነት ለመወጣት በሚያደርገው ጥረት ውስጥ ወጣት ሳሙኤል አወቀን ጨምሮ ብዙ አባላት ውድ የሆነውን የህይወት መስዕዋትነት ከፍለዋል። ቆራጥ አባሎቹም በየማጎሪያ ቤቱ እየተሰቃዩ ይገኛሉ። ብዙዎች አካላቸው ጎድሉዋል፣ ከስራ ተባረዋል፣ ተፈናቅለዋል፣ ቤተሰባቸው ተበትኑዋል። ነገር ግን ይህንን ብዙ መስዕዋትነት የተከፈለበትን ፓርቲ እንዲዳከምና አገዛዙ ለሚፈልገው ዓላማ እንዲውል የሚያደርጉት ተግባር ታሪክ ይቅር የማይለው ነውረኛ ተግባር ነው።
ፓርቲያችን የሕወሐት/ ኢሕአዴግን አመለካከት እንዲቀበል በመስከረም አጋማሽ 2009 ዓ.ም የፓርቲውን ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነትን ደሳለኝ ሆቴል ቀጠሮ እንዲይዙልዎት ጠይቀው የመንግስትን አቁዋም በእርስዎ በኩል እንደገለፁላቸው አይዘነጉትም። ከገለፁላቸውና ህዝብ በወቅቱ የማያውቃቸው ጉዳዮች ውስጥ
1. የአስቸኩዋይ ጊዜ አዋጅ ሊታወጅ እንደሆነ
2. መንግስት ብዙ ጊዜ በሚወቀስባቸውና ተቃውሞ በሚነሳባቸው አዋጆች (የምርጫ አዋጅ፣ የፀረ ሽብር አዋጅ፣ የሲቪክ ማህበራት አዋጅ) ከፓርቲዎች ጋር መደራደር እንደሚፈልግ
3. ኢ/ር ይልቃል አሜሪካን አገር በነበሩበት ጊዜ የሀገራችንን ወቅታዊ ችግር የሚፈታው “የባለአደራ መንግስት” ሲመሰረት ነው ብለው በተለያዩ ስብሰባዎችና ቪኦኤን ጨምሮ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን በመናገራቸው ብዙ የመንግስት ባለስልጣናትን እንዳላስደሰተ ገልፀው ይህንን አቁዋማቸውን እንዲያስተካክሉ መጠይቅወን አይዘነጉትም።
4.በውይይታችሁ መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም መኢአድ ጽ/ቤት ሊደረግ ስለታሰበው የሰማያዊ ጉብኤ እራስዎ በገለፁት መሰረት” ይህንን መፈንቅለ ስልጣት እንዴት ታየዋለህ?” በማለት ጉዳዩን በውል የሚያውቁትና የሚከታተሉት መሆንዎን ኢ/ር ይልቃል እንዲገነዘቡትና ፓርቲው አደጋ ከሚደርስበት አቁዋማቸውን እንዲያስተካክሉ ገልፀውላቸዋል። በተጨማሪም “ስለ ባለአደራ መንግስት አስፈላጊነት የምታራምደው አቁዋም የኢ/ር ይልቃል የግል አቁዋም ወይስ የፓርቲው ነው? “ብለው በእለቱ መጠይቅዎን አይዘነጉትም።
ነገር ግን ኢ/ር ይልቃል እርስዎ ያሉትን ባለመቀበላቸው የተባለው ጉባኤ በእለቱ እንደተደረገና እርስዎም አዲስ “ተመረጠ”ከተባለው አመራር ጋር የሚፈልጉትን ለማስፈፀም ወደ መኢአድ ጽ/ቤት እንደሚሄዱ ፣ አሁንም በዛው ተግባርዎ ገፍተውበት የፓርቲዎች ድርድር በሚባለው ማላገጫ የመንግስት አጋፋሪ ሆነው በድርድሩ ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል።
የሚፈልጉትን አስተሳሰብ ማራመድም ሆነ ኢህአዲግን መደገፍ መብትዎ ቢሆንም ብዙ ዜጎች በሚሞቱባት ሀገር ፓርቲዎችን በሴራ እያፈረሱ ለአገዛዙ እድሜ ማራዘሚያነት እንዲውሉ መስራት ግን ታሪክ ይቅር የማይለው ሀገራዊ በደል ነው።እርስዎም እንደሚያውቁት አሁን አመራር ነኝ የሚለው አካል በምርጫ ቦርድ እውቅና ከማግኘቱ በፊት እነ ኢ/ር ይልቃል አቁዋማቸውን አስተካክለው ከሆነ በሚል ይመስላል የእጅ ስልካቸው ላይ ከኢህአዴግ ጽ/ቤት ተደውሎ በድርድሩ እንዲሳተፉ ግብዣ ተልኮላቸው በእነሱ በኩል የተላኩት ሰዎች ከድርድሩ የሚጠብቁት ነገር ኢህአዴግ ማድረግ ከሚፈልገው አንፃር የማይጣጣም በመሆኑ በእነ ኢ/ር ይልቃል በኩል የተወከሉት ከስብሰባው እንዲወጡ ተደርገው ከሻይ እረፍት በሁዋል እነ የሽዋስ አሰፋ እንዲገቡ ተደርጉዋል። ይህንን ህጋዊ ለማስመሰል ለአሁኖቹ የመኢአድና የሰማያዊ አመራር ነኝ ለሚሉት በአንድ ቀን ውስጥ ከምርጫ ቦርድ እውቅና ተሰጥቱዋቸዋል።
ይህ ሁሉ ግልፅ ሴራና ደባ ሲፈፀም እርስዎ ዋነኛ ተሳታፊ እንደሆኑ እኛም እርስዎም የምናውቀው ጉዳይ ነው። በፓርቲያችንና በህዝብ ትግል ላይ ብዙ በደል እንደፈፀሙ ብናውቅም በተለያዩ ምክንያቶች ይህንን አፍራሽ ተግባርዎን በአደባባይ ከመግለፅ ተቆጥበን ቆይተናል። ይሁን እንጂ እርስዎ የፓርቲያችንን ጉዳይ በራሳችን ጥረት መልክ ለማስያዝ በምናደርገው ሂደት አሁንም ይህንን አፍራሽ ተግባርዎን ቀጥለው ፓርቲው ለህዝብ ተስፋ ሁኖ እንዳይወጣ እየሰሩ መሆኑን ተገንዝበናል። በመሆኑም ከዚህ ሀገርንና ህዝብን እየበደሉ ገዥዎችን ለማጠናከር ከሚፈፅሙት ታሪካዊ በደል እንዲቆጠቡ መስዕዋት በሆኑ ወገኖቻችን ስም እንጠይቅዎታለን።
ኢትዮጵያ የእውነት ሀገር ስትሆን ሁሉም በጊዜው ግልፅ ይሆናል!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

♦ “ ትክክለኛ ፍትሕ አይሰጡም” የተባሉት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ከችሎት እንዲነሱ ተጠየቀ !

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar