www.maledatimes.com አንድም እናት መሞት የለባትም በሚለው የመንግስት አዋጅ ወጣቶች በሃኪሞች ግዴለሽነት እየሞቱ ነው ። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

አንድም እናት መሞት የለባትም በሚለው የመንግስት አዋጅ ወጣቶች በሃኪሞች ግዴለሽነት እየሞቱ ነው ።

By   /   January 18, 2018  /   Comments Off on አንድም እናት መሞት የለባትም በሚለው የመንግስት አዋጅ ወጣቶች በሃኪሞች ግዴለሽነት እየሞቱ ነው ።

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 0 Second

በሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ አጣዬ ከተማ ባለው ሆስፒታል እየተከናወነ ያለው አስደንጋጭ ትእይንት ህዝብን አስደንግጧል ፣ ባለፉት ወራት ብዙ ወጣቶች ወደ ሆስፒታሉ ገብተው ህይወታቸውን እያጡ መመለሳቸው መንግስትም ምላሽ እንዲሰጣቸው ፣ህዝቡም የአመለካከት አድማሱን አስፍቶ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ሲሉ ገልጠዋል ።

በትላንትናው እለት ከዞኑ መስተዳድር ከሚኖሩ ዜጎች ለማለዳ እና ዘሃበሻ መረጃ ማእከል አቤቱታቸውን ያደረሱን ግለሰቦች እባካችሁን ችግራችንን ለህዝብ አሳውቁልን ፣በህዝብ ገንዘብ በተገነባው ሆስፒታል የህዝቡ ልጅ እየሞተ ነው የሚወጣው ሲሉ ገልጠዋል ፣ለዚህም እንደምሳሌ ያቀረቡት ወጣት መሃመድ ሰይድ የተሰኘውን ወጣት ህክምና ለማግኘት ገብቶ የቀዶ ጥገና ሊደረግልህ ይገባል ብለውት ከገባ በሁዋላ በሃኪሞች ስህተት ቀዶ ጥገናውን ካደረጉ በሁዋላ ጥገናው የተደረገበትን የውስጠኛውን አካል በትክክል ካለመስፋታቸው የተነሳ የወጣቱ ደም ያለመጥን ከመፍሰሱ የተነሳ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሪፈራል ሆስፒታል ቢላክም ህይወቱ ሊተርፍ አልቻለም ሲሉ ገልጸዋል ።

በተያያዘም ዜና አንድ የሰንበቴ ወጣት በእንደዚሁ አይነት ሁኔታ ባለፉት ስድስት ወራት ማለፉን የጠቆሙ ሲሆን ፣ ወላጅ እናቶች ግን በየ እለቱ ህይወታቸው በኦፕራሲዮን አድራጊ ዶክተሮች አማካይነት እንደሚቀጠፍ ተናግረዋል ፨

የአብዛኞቹ እናቶች ሞት በወሊድ ወቅት ከፍተኛ የማደንዘዣ መድሃኒት ከወጓቸው በሁዋላ በዚያው እንደሚያሸልቡ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል ። አንድም እናት በወሊድ ምክንያት መሞት የለባትም የሚለው ዲስኩር በአጣዬ ሆስፒታል አይሰራም ፣ገና ብዙ ራእይ ያላቸው ሴት እህቶቻችን በአጭሩ በሆስፒታሉ እየተቀጩ ነው ሲሉ መናገራቸውን የማለዳ ምንጮች ገልጠዋል።

ሟቹ በመሃከል ያለው ወጣት ሞሃመድ ሰይድ ይመር ነው ። የማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል ለቤተሰቦቹ ለጉዋደኞቹ እና ለባልደረቦቹ መጽናናትን ይመኛል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

♦ “ ትክክለኛ ፍትሕ አይሰጡም” የተባሉት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ከችሎት እንዲነሱ ተጠየቀ !

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar