በኔዘርላንድስ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር በተጻፈ ደብዳቤ አምባሳደሩ ለምን ከሀገር እንዲወጡ እንደተወሰነ በዝርዝር ተቀምጧል።

ደች አርጎስ የተባለው ሬዲዮ ዘገባን ተከትሎ የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ በጻፉት ደብዳቤ ከዚህ ውሳኔ የደረሱት፤ የኤርትራ ስደተኞች የቆንሱላ አገልግሎቶችን ለማግኘት በኤርትራ ኤምባሲ የዲያስፖራ ግብር እንዲከፍሉ ይጠየቃሉ ብለዋል።

የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ፤ በኤርትራ የዲያስፖራ ማህብረሰብ ላይ ተደጋጋሚ የሆነ የማስገደድ እና የማስፈራራት ምልክቶች ታይተዋል ብለዋል።

ምንም እንኳ የኤርትራ ኤምባሲ ምንም አይነት ህገወጥ የሆነ ስራን ባይሰራም እንዲህ አይነት ተግባርን መታገስ ስለማንችል ጠንከር ያለ መልዕክት ማስተላለፍ ስለምንፈልግ ነው ከዚህ ውሳኔ የደረስነው ሲል የደች ካቢኔት አስታውቋል።