www.maledatimes.com “ጃ ያስተሰርያል!” አራት አመታት ተከልክሎ በነበረ መድረክ? ክንፉ አስፋ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

“ጃ ያስተሰርያል!” አራት አመታት ተከልክሎ በነበረ መድረክ? ክንፉ አስፋ

By   /   January 27, 2018  /   Comments Off on “ጃ ያስተሰርያል!” አራት አመታት ተከልክሎ በነበረ መድረክ? ክንፉ አስፋ

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 54 Second
            ቴዲ ወደ ባህርዳር ሲያቀና “እንዘምራለን”  ማለቱን ያስተውሏል!።  የጉዞውን አላማ እንዲያ ሲል ነበር ረቂቅ በሆነ መንገድ የገልጸው።  በመዘመር እናበመዝፈን መሃል ያለውን ጥልቅ ልዩነት የማይረዳ ብቻ ነው ለሰሞኑ “አሲዮ ቤሌማ” እጅ የሚሰጠው።  ከኮንሰርቱ ጀርባ ያለው “የፍቅር ጉዞ” የሚለው መሪ ቃልውስጥም ከውቅያኖስ የጠለቀ መልዕክት አለ። ይህንን ቃል የተረዳ ብቻ ነው የተልእኮውን ስኬት ሊያበስር የሚችለው። ዝግጅቱ ኮንሰርት እንጂ ዳንኪራአይደለም። ሁለት ወይንም ሶስት ሰዓት ብቻ የፈጀ ኮንሰርት። ጥላቻ ሳይሆን ፍቅር የነገሰበት ኮንሰርት።  ትንሳዔን አብሳሪ ኮንሰርት። መዝሙር ውስጥ መልዕክት አለ። የሚያንጽ፣ የሚያነቃቃ መልዕክት።
Inline image 1
መላው በጠፋበት በዚህ ወቅት፤  ኢትዮጵያ የምትሻው የተስፋ ቃል ብቻ የሚደሰኩርላትን ሳይሆን ድልድይ የሚዘርጋላትን ሰው ነው።  ጥላቻነግሷል። በሃገራችን ስር ሰድዶ፤ ቤተ እምነትን ሳይቀር አምሶታል፤  ጥላቻ – ጥላቻን ይወልዳል እንጂ ችግርን አይፈታም።  እሱን ለማንገስ ላለፉት 27 ዓመታትብዙ ድንጋይ ተፈንቅሏል። አዎ ጥላቻ በሽታ መሆኑን አይተናል።
ይህን ክፉ በሽታ ለማርከስ  የፍቅርን ዳገት መውጣት ግድ ይላል። ጉዞውን ቴዲ ጀመረው። ጥላቻን የሚያከስሙ ዜማዎቹን የሰሙ …  እነ ለማ መገርሳእነ … ዶክተር አብይ ተከተሉት።  ለማ መገርሳ “ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው” ማለቱ  የቴዲ “ሲንድረም” ስለመሆኑ የሚጠራጠር ይኖር ይሆን?
            ጎበዝ፣  ዘመኑንም እንቃኘው እንጂ!   ሰው ለታቦት ንግስ ወጥቶ በዚያው የሚቀርበት ዘመን እኮ ነው ያለነው። ወገን የእሬቻን በዓል ለማክበር ሄዶእስከዘላለሙ የማይመለስበት ወቅት ላይ ነን።  ልቅሶና ሃዘንን ሰብሰብ ብሎ በጋራ የማይካፈሉባት ምድር፣  ምእመናን ለጸሎት ወጥተው የሚታፈኑበት ሃገር ላይእንደተቀመጥን ለአፍታም አንዘንጋው።  ኮንስርት ማድረግ  ብርቅ የሆነበት ሃገር። ዳር ድንበር እንዲያስከብር የተላከ ወታደር  መሃል  ከተማ ገብቶ የወገን ደምየሚያፈስስበት ምድር!  በዚህች ያልታደለች ሃገር፣ በዚህ አስከፊ ዘመን፣   “ጃ ያስተሰርያል”ን  አጥንት ይዘን ስንጓተት አጃኢብ አይሆንም?
            ይህ እሰጥ እገባ  ልብ ላለው ሁሉ ቅንጦት ይሆናል።  ነገሩን በደንብ የተረዳው ወገን፣  ከ 50 ሺህ ሕዝብ  በላይ በታደመበት ዝግጅት ላይ  “ምንይፈጠር ይሆን?”  እያለ የልቡ ትርታ ከፍ እና ዝቅ ይል ይሆናል እንጂ፣  ቀሪ ሂሳብ አያወራርድም።  ጥሩ ዜና በሚናፈቅበት በዚህ ቀውጢ ሰዓት፣  ሰማይ ላይየወጣን የሕዝብ እምቅ ስሜት ተቆጣጥሮ በሰላም ማጠናቀቅ መቻል እጅግ የሚደነቅ ነገር  ነው። ስለዚህም ጉዳዩ የገባቸው ዝግጅቱ  “እንኳን በሰላም አለቀ!” ይላሉ።  ሻንጣ በጀርባ ሸክፎ ማራቶንን መሮጥ ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ የሚያውቀው ሯጩ ብቻ ነው።
           እርግጥ ነው ሕዝብ ፍላጎቱን ገልጿል። የሕዝብ ጥያቄ ተገቢ ምላሽ ማግኘት ነበረበት።  የሕዝቡ ጫና ቀላል አልነበረም።  ይህንን በተመለከተ ከቴዲአካባቢ የሚሰማው ነገር የህዝብ ስሜትን ያለመረዳት ጉዳይ አይደለም።   ስሜትን መረዳት እና ስሜትን መንዳት ሁለት የተለያዩ ነገሮች ናቸው።   26ኛውየአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩት ቴዎዶር ሩዝቬልት በአንድ ወቅት ሲናገሩ “በመሪዎች እና በአለቃ መካከል ያለውን ልዩነት ሰዎች ይጠይቃሉ።  መሪ ይመራል።አለቃ ደግሞ ይነዳል” ብለዋል።  መንዳት እጅግ ቀላል ነው። ውል ለማስያዝ መምራቱ ነው ከባድ።
        አራት አመታት ሙሉ ተከልክሎ የነበረ መድረክ፣  በሰላም እንዳያልቅ፣   እንከን የሚያሸትቱ ተንኳሾች  አሰፍስፈው የሚጠብቁት ነገር ነበር። የጌታቸውማንጉዳይ ጣልቃ መግባት ነገሮችን አስቀድሞ የመረዳት፣ አርቆ የማሰብ እና የመብሰል ውጤት ነው።  በዚህ ፍቅር ጉዞ እቅድ ላይ  “ጃ ያስተሰርያል”አልነበረም።  ጉዞው ለመዝፈን ሳይሆን መልዕክት ለማስተላለፍ ነው።  የሰላም እና የፍቅር መልዕክት።  በዚያ ውስጥ ሃዘን አለ። በዚያ ውስጥ ብሶት አለ። በዚያውስጥ ቁጭትም አለ።   በነገራችን ላይ በኮንሰርቱ ላይ ባለስልጣኖቹ በይገኙም ልጆቻቸው እና ሚስቶቻቸው በሙሉ ስቴዲየም ገብተው ከሕዝቡ ጋር ሲደሰቱነበር።
ሕዝብ በአንዲት ቃል ብቻ ማነሳሳት እጅግ ቀላል ነው።  በረጅሙ የሚያይ ሳይሆን አጭሩን አላማ የመረጠ ይህንን ማድረግ ይቀልለዋል። ከዚህ ግፊትየሚገኘው ውጤት፣  ኪሳራ እንጂ ትርፉ ሚዛን ሊደፋ አይችልም።  ጥይቱንም፣ ቀለሃውንም የያዙ ሃይሎች ሰፍ ብለው ይህችን ወቅት እንደሚጠብቁአንዘንጋ።
እያወራን ያለነው ስለ ሞብ  ስነ-ልቦና ነው። ሞብ  የማህበረሰብ ስነ-ልቦና አካል ነው። የስነልቦና ምሁራን የሆኑት ጉስታቭ ሌቦን እና ሲግሞንድ ፍሬድ”ሰዎች አንድ አላማ ይዘው በሲሰባሰቡ በሚጋሩት የጋራ የሆነ አመለካከት፣  ግላዊ ሃላፊነትን ከአናታቸው አርደው ስለሚጥሉ፣  ምንም ነገር ከማድረግአይቆጠቡም ” ይሉናል።
            ይህን ያህል ግዙፍ ኮንሰርት ይቅርና ሰዎቹ የራሳቸው የመቀሌው ስብሰባም “በሰላም አለቀ” ይሉን የለ? በረጅሙ እየተነፈሱ “የአዲስ አበባው ጥምቀትበዓል በሰላም ተጠናቀቀ” ብለውናል። በተዘዋዋሪ ሰላም የምትለው ቃል  እንደ ዳይኖሰርስ  ከምድሪቱ ጠፍታለች እያሉን እኮ ነው። ሰዎቹ እኮ አስከሬን አጅቦየሚሄድን ለቀስተኛ እንኳን ማመን የተሳናቸው፣ በራስ ገመድ ተጠልፈው፣  የራሳቸውን ጥላ እንኳን የሚፈሩ፣….  ምጥ ውስጥ ያሉ ናቸው።  የፈሪ ዶላ ረጅምነው እንዲሉ በጋራ ሆኖ ያዜመ ላይ ሳይቀር የሚተኩሱት  ለዚህም ነው።
            ትልቁን ጥበብ እና ማስተዋል የሚጠይቀው ሕዝብ በተሰበሰበበት ስፍራ ሊመጣ የሚችለውን ችግር ማስወገድ መቻል ነው።  ይህ አርቆ ማሰብንይጠይቃል። ቅዝምዝም ሲወረወር ጎንበስ ብሎ የሚያልፍ  አስተዋይ ብቻ ነው። የሕዝብን ስሜት ማረጋጋት መቻል ራሱን የቻለ ጥበብ ይጠይቃል። ብሶትያጋለው ሕዝብ ነው። እልህ የተናነቀው ሕዝብ። በቋፍ ላይ ያለ ሕዝብ።   አንድ ነገር ለማድረግ ጥቂት ቃላት ብቻ ይበቃሉ።
ደግሞ ጨዋ ነው። መሪውን የሚሰማ – ለሚወድደው የሚታዘዝ ሕዝብ።
            ሁሉም ነገር ግዜውን ጠብቆ ይከሰታል። ከዚህ ቀደም ቴዲ “ጃ ያስተሰርያል”ን ለምን አልዘፈነም ብለን ጮኸናል። ለጩኸታችን ምክንያቱ አጥጋቢይሁንም-አይሁን፣  ወቅቱ ይህንን ለማለት ይፈቅድ ነበር። ከአመታት በፊት “ጃ ያስተሰርያል”  ሲዘፈን የነበረው ሁነታ አሁን የለም። አሁን  ስለ ለውጥ እና ስለአዲስ ንጉስ መምጣት አይደለም የምንጨነቀው። የመኖር እና የአለመኖር፣ የለህልውና ጥያቄ ላይ ደርሰናል።  የንጹሃን ደም በየቀኑ ይፈስሳል።  ሃገር እንደጉድይዘረፋል። እየተካሄደ ያለውን ግፍ ቃላት አይገልፀዉም።  ነገሩን ከስሜት መነጽር ወጣ አድርገን እንመልከተው።  ፈጥኖ መፍረድ እና ፈጥኖ መናደድ ከአመክንዮ ሳይሆን ይልቁንም ከፍርሃት እና ከድንቁርና ጋር እጅ ለእጅ የሚሄድ ነገር ነው።
            አሁን ነገሮች ተለዋውጠዋል።  ወደድንም ጠላን፣   አገዛዙ ዳግማዊ “ዘመነ መሳፍንት”  ውስጥ አስምጦን፣  እልቂት አፉን ከፍቶ እየጠበቀን ይገኛል። ሃገሪቱ አጼ «ቴዎድሮስ»ን  ትሻለች። የአይሻልን ጦርነት በድል ተወጥቶ ዳግማዊው ዘመነ መሳፍንትን  ማብቂያ ያሚያውጅ ጀግና የማውጣቱን  ነገር  ግድ ይላል።
በቴዲ እና በአቡጊዳ ኢትዮጵያ የተጀመረው የፍቅር ጉዞ ይቀጥላል።  ቀጣይዋ  ከተማ ውቢቷ ናዝሬት / አዳማ ናት። በከተማዋ ቀደም ሲል የተዘራው የጥላቻ በሽታ በፍቅር ይታከማል። እነ ለማ መገርሳም በአዳማው ኮንሰርት ላይ ይገኙ ይሆናል።
ፍቅር ያሸንፋል!

https://youtu.be/Mq0EGRfjLjI

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

♦ “ ትክክለኛ ፍትሕ አይሰጡም” የተባሉት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ከችሎት እንዲነሱ ተጠየቀ !

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar