www.maledatimes.com የማለዳ ወግ… እየሳቁ ማልቀስ ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የማለዳ ወግ… እየሳቁ ማልቀስ  !

By   /   July 11, 2015  /   Comments Off on የማለዳ ወግ… እየሳቁ ማልቀስ  !

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 0 Second

* የተሰራው ስራ ስኬት ፣
ባልተሰራው ስራ የሚያመው ህመም  !
===========================
* ወጣቱ አባወራ መሀመድ ሀሰን ሀገር ቤት ገባ  !
* ሁለቱ መሀመዶች ጉዳያችንና ተስፋው …
*  ያሰመረው ተስፋ
* ያልሰራነው የቤት ስራ …
* ባትደግፉ እንኳ  አታደናቅፉ
* እርዱ እረዳችኋለሁ  …

ሁለቱ መሀመዶች ጉዳያችንና ተስፋው …
=======================
ወጣቱ አባወራ መሀመድ ሀገር ቤት በሰላም ገብቷል ። ሰኞ ለማክሰኞ አጥቢያ ሰኔ 29 ቀን 2007 ዓም በሰላም መግባቱን የገለጸልኝ መሀመድ በሳውዲ ቆይታው በተለይም ሮመዳን በገባ ማግስት ተስፋው ጨልሞበት ሰዓት ድረሱልኝ ያላቸው ወገኖቹ በጸሎትና ትብብር ከምንም በላይ መደሰቱን ገልጾልኛል ።

…የሁለት መሀመዶችን የመሰንበቻ ወጋችን ነበር ።  በሀኪሞች ስህተት ዘጠኝ ዓመት የአልጋ ቁራኛ የሆነውን  ታዳጊ ብለቴናው መሀመድና ስደት ያሰናከለው ወጣት አባወራ መሀመድ ሁሴን እያልኩ በዙሪያው ባለው መረጃ ሳቀብላችሁ ከረሜያለሁ ።  የብላቴናው ጉዳይ ውስብስብ ያደረገው በደል አድራሹ ሆስፒታል ጉዳዮችን የማረቅና የማፈን አቅም ቢሆንም ግፍ ተሸፋፍኖ አይቀርምና ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ወደ መጨረሻዋ ሰዓት መዳረሻው የተጣጋን ይመስላል …ፈጣሪ ይርዳን  !

የወጣቱ አባወራ ያልኳችው የመሀመድ ሁሴን ጉዳይ ግን እነሆ ተከውኗል ። Mission Accomplished ብለናል  !  መሀመድን በደረሰበት የከፋ የመኪና  አደጋ በአዲት ጠባብ አልጋ ተወስኖ የመክረሙን አበሳ ፣ የወገን ናፍቆትና ህመሙን ቀድሜ ብረዳም በአካል ሔጀ ሳየው መስማት እንደማየት አለመሆኑን እያወቅኩት ደጋግሜ የተረዳሁነት አጋጣሚ ነበር ። ብርቱው ሰርቶአደር ገበሬ መሀመድ የወለዳቸውን ሁለት ፍሬ ልጆች ብሩህ ተስፋ ብሎ የገባበት ስደት ቢያሰናክለውም ሳገኘው ያየሁበት  በብሩህ ገጽታ ፊቱ በርቶ ነበር ። መሀመድን እንርዳ ካልኩበት ሰዓት ጀምሮ በጸሎትና በገንዘብ ያደረጋችሁለት እርዳታ አተርፍ ብሎ ያጎደለውን መሀመድ በወገን አለኝ ተስፋ አድሶት ተመልክቻለሁ ፣ ህመሙንም አስረስቶታል ።

መሀመድ ዛሬ ራሱን ችሎ መሮጥ  አይችልም። መሀመድ በሀገሩ የሸለለ የፎከረበትን መሬት መርገጥ አይችልም  ።  መሀመድ ትናንት ቤተሰቡን ለመታደግ  ገስግሶ ወደ ስደት የመጣበትን ምድር ይኖር እንደሁ እንጅ አይረግጠውም  ! በኩንፊዳ ሆስፒታል ሳገኘው ለዘጠኝ ወራት በአንዲት ጠባብ አልጋ ላይ የተገጠመለትን ብረትና ብረት ይዞ ጎንበስ ቀና እያለ ፣ ቀኝና ግራ እየተላወሰ ነበር …
ይህ ፈተና የገጠመው መሀመድ ግን ብርቱ ሞራል አለው ። ሲያገኘኝና ፣ አቅፎ ሲስመኝ ደስ አለው … ጽናትና ተስፋውን ተመልክቸ ተደመምኩ …በውስጤ ” ተመስገን ነው! ” ስለ ለፈጣሪ ምስጋና አቀረብኩ !   … መሀመድ በአጭሩ  የቁንፊዳ ቆይታየ ደጋግሞ  ፈጣሪው ስለሆነው ሁሉ ሲያመሰግን ያስታወሰኝ እያለን እና ስለተደረገልን ለፈጣሪ ምስጋና የማናቀርብ እኛም ሀጥኦቹን አስታወስኩ …

የሰመረው ተስፋ ….
=============
ትናንት ሰኞ ሌሊት ሰኔ 30 ቀን 2007 ዓም ሌሊት ሊሸኝ ቅዳሜ ከጅዳ 320 ኪሎ ሜትር ርቀት በአንዱ የቀይ ባህር ዳርቻ ጥግ ባለ ሆስፒታል ስንገናኝ እንዲህ ነበር ያለኝ ” አልሀምዲላህ ፣ ከፈጣሪ በታች በወገኖቸ ስለተፈረገልኝ ጸሎትና ያልጠበቅኩት እርዳታ የጨለመው በርቶልኛል  ፣ አሁን ባለ ተስፋ ነኝ ፣ አላለቅስም ። ነቢዩ ሮመዳን ለሀገሬ መግባት ከቻልኩ ደግሞ እሰየው ነው  ፣ ትሄዳለህ ካልከኝ በኋላ ድኛለሁ ፣ ኢንሻላህ አላህ አለ  !” ነበር ያለኝ

…እነሆ ተስፋው መሀመድ በሮመዳኑ የጸሎት ወር ድረሱልኝ እንዳለ ያሰበው ተሳክቶ ከናፈቃት ሀገሩ ደርሷል ። ታግሎ የጣለ ያደባየው የናፈቀው ወንድሙ አቅፎ ደግፎ ከወገኑ ሊያገናኘው ተቀብሎታል …ከናፈቃቸው ሁሉ ወገኖቹ የመገናኛው ቀን ደርሷል ….መሀመድ ልጆቹና ቤተሰቡ ጋር ሊገናኝ ሳይውል ሳያድር ተንቀባሮ ወዳደገባት ቀየው ሳይውል ሳያድር ወደ ባቲ ይገሰግሳል … ልጆቹ ናፈወቀውታላ !  ሚስቱ ናፍቃዋለቻ  ! እናት አባት ቤተሰብ ፣ ዘመድ አዝማድ ናፍቀውታላ  ! … ሳላስበው ነፍሴ በስሜት ተናጠች …ብዙ መሀመዶችን አሰብኳቸው  ! ብዙ ስም የለሾች በአዕምሮየ ተመለለሱ …

መሰራት ያለበት ፣ የሚያመው ያልሰራው የቤት ስራ …
================================
ወገን እያላቸው ፣ ወገን እንደሌላቸው በየበርሃው ወድቀው የቀሩት ይሁን ቢባል ፣ በየሆስፒታሉ ወድቀው ፣ በየቤቱ ህመማቸውን ህመም አድርገው ደብዛቸው እየጠፋ ያሉ ወገኖቸን ጨካኙ እኔ ላንዳፍታ አሰብኩት … መዲና ከተማ ውስጥ በመኪና አደጋ የተገጨች እህት አለች ፣ አትሰማም አታይም ፣ ማንነቷን እንኳ ከጣቶቿ አሻራ ወስዶ መለየት የቻለ የለም ፣ ያን ሰሞን “ማንነቷን ለዩና አሳውቁን  ” ብለን ነበር ። መጀመሪያ ከቅርብ ወራት ወዲህ ከፖለቲካ ወገንተኛነት ተላቆ ወገናዊ እየሆነ የመጣው ” ወገን ለወገን ” በጅዳ ከባቢ ያለ የፊስ ቡክ ቡድን መረጃውን አቅርቦታል  !  ” ከወገን ለወገን ” ያገኘሁትን መረጃ እኔም አቅርቤያለሁ  !

ያም ሆኖ እኔ በሁለቱ መሀመዶች ጉዳይ ትኩረት ሳደርግ ተሰናክላ ለአመታት የአልጋ ቁረኛ የሆነችቅን እህት ማንነት የሚያረጋግጥ መረጃ ደርሶኛል ። የአመታት የአልጋ ቁራኛ የመሆን አበሳና ስለ ወላጆቿ ያልሰመረ ፍለጋና ሞታለች ብለው ስለደመደሙበትን ሙሉ መረጃ ደርሶኛል …ላለፉት አመታት በተመሳሳይ ሁኔታ በመኪና አደጋ አዕምሮውን የሳተ እጁ ከብረት አልጋ ላይ ታስሮ የሚሰቃየውን ወንድም ደራሽ አጥቶ ለመክረሙ ብዙ መረጃ አለ … ጅዳስ ቢሆን ለአመታት ከሆስፒታል ወድቃ ያላየናት ፣ ከአመታት ያልነቃች እህት የለችምን  ?  ያማል …ያማል …ያማል  !

የምንሰራውን ባትደግፉ እንኳ  አታደናቅፉት …
=============================
የሚሰራውን ስላልሰራችሁ የምወቅሳችሁ ፣ የወገንን ጥቅም አስቀድሙ በማለቴ ጥቅማችሁ ያዛባሁባችሁ ፣ የምሰራውን ስራ የምትነቅፉኝ ሆይ  ! አዙራችሁ ራሳችሁን ጠይቁ  !  … እኔ ስላነሳሁት ብቻ ”  ውሾ ”  ብላችሁ ከማብጠልጠልና ለክብርና ዝና ፣ ብሎም የታመመን አይቶ ከመታመም ፣ የጨነቀውን አይቶ ከመጨነቅ ውጭ የማገኘው ጥቅም ያለ አይምሰላችሁ  ! ቸር  ደግ ሆኘ የማደርገው ልገሳም የለም … ዳሩ ግን እድሜው ሲገፋ ነው መሰል ” በእህቶቸና ወንደሞቸ ላይ የማየው ስቃይና ተለያይቶ መቅረት በልጆቸ ፣ በራሴና በቤተሰቤ ላይ ቢሆንስ ?” እያልኩ እየፈራሁ ወገን ለወገኑ እንዲደርስ  የማደርገውን መረጃ ቅበላን ማስተባበሩን ባትደግፉ እንኳ  አታደናቅፉት   ….  መከራችን አበሳችን ብዙ ነው ፣ በህብረ ት ከሆነ ግን ሊቀረፍ የሚቻለን ብዙ የወገን ችግር አለ  !

ወጣቱ አባወራ መሀመድን ወደ ሀገር ቤት እንዲገባ የሳውዲ መንግስት የትራንስፖርት ወጭን ሸፍኖለታል ፣ እናመሰግናለን  ! …  ከዚህ በተረፈ እኛ ለእኛ ፣ ለራሳችን ወንድም ስላደረግነው ደስተኞች ነን እንጅ ጀብድ አልሰራንም  ! ቆንስሉ ረዳው ኮሚኒቲው  ፣ ማህበራት ደገፉት ፣ ድርጅቶች ፣ አልያም ግለሰቦች ረድተውት እዚህ ደረሰ ፣ ይህ መከራከሪያችን መሆን የለበትም ፣  አይበጀንምና  !  መሀመድን ወደ ሀገር ቤት ለማስገባት ተቋማት ደገፉት ግለሰቦች ማንም ደገፈው ማን ቁምነገሩ  መሀመድ በሰላም ሀገሩ መግባቱ ነው ፣ በቃ አውነቱና የሚበጀን ይህው ነው  ! … ስሜት እዚህ ላይ ልገድበው …
እርዱ እረዳችኋለሁ  …
==============
ለመሀመድ 11.250 የሳውዲ ሪያል ካስረከብኩ በኋላ ተጨማሪ 1100 የሳውዲ ሪያል (700 ሪያል ከ400 ከስልክ ካርድ ጋር ተደምሮ) እርዳታ ሰብስቤያለሁ ። ” ጋን በጠጠር ይደገፋል! ” እንዲሉ በቀጣይ  ለመሀመድ የሚደረገው እርዳታ ቃል የገባችሁ ቃላችሁን እስትፈጽሙ ለቀናት ማሰባሰቡን እገፋበታለሁ ፣ መቋቋሚያ ቢሆነው ያቻልነውን እናድርግ … ፈጣሪም ያለው ” እርዱ እረዳች ኋለሁ!  ” ነውና አሁንም መሀመድን ለመደገፍ የቻልነውን እንሞክር  ! …

በተረፈ አነሰ በዛ ሳትሉ ከጎኔ ለቆማችሁ ስላደረጋችሁት ሁሉ ምስጋናየ እርካታየን ባይገልጸውም  ደጋግሜ አመሰግናችኋለሁ  !

ደስ የሚለውን ሁሉ ይስጣችሁ  !

ነቢዩ ሲራክ
ሰኔ 30 ቀን 2007 ዓም!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on July 11, 2015
  • By:
  • Last Modified: July 11, 2015 @ 9:47 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar