www.maledatimes.com በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

By   /   December 11, 2023  /   Comments Off on በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

    Print       Email
0 0
Read Time:41 Second

በአሁኑ  ሰአት በደረሰን መረጃ መሰረት የኢትዮጵያ የሃገር መከላከያ ሰራዊት በሰሜንሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ እና በገምዛ ወረዳዎች ላይ ከፍተኛ ጥቃት እየፈሸመባቸው እንደሆነ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጠዋል ፡፡

ከማጀቴ ጀምሮ ካራቆሬ ፣ እና አጣዬ አካባቢ ያሉትን ቦታዎች ካለፈው አራት አመታት ጀምሮ በኦሮሞው ሃይል ትቃት ሲደርስባቸው እንደነበር የሚታወስ ቢሆንም ከውስጥ ባገኘነው መረጃ መሰረት ጥቃቱ በመንግስት የታገዘ እንደነበር ምንጮቻችን ጠቅሰዋል፡፡

ዛሬም በአካባቢው ላይ የሚደረገው ጥቃት በመንግስት ትእዛዝ የተደረገ ቢሆንም ፋኖን እናጠቃለን በማለት ወደ ህዝቡ ጥቃት በመሰንዘራቸው ሳቢያ ፣ የአካባቢው ነዋሪው ህዝብም ምላሽ ለመስጠት ጥቃት መፈሸሙን ተናግረዋል ፡፡ ሆኖም ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚህ ጥቃት የተነሳ ለጦርነትም ሆነ ለምንም ዝግጁ አይደለንም እራሳችን ካሳለፍነው መከራ ለማገገም እየሞከርን ነበር ሆኖም መንግስት ሆን ብሎ ህዝባችንን ገደለው ፣ አዳከመንም በማለት የጥቃቱን ሰፊነት ነዋሪዎች ለማለዳ ሚዲያ አብራርተዋል፡፡

ውጊያ ከፋኖ ጋር ነው እያሉ በእየ ህብረተሰቡ ቤት በመግባት ገበሬዎችን እየገደሉ ነው በማለትም የተናገሩ ሲሆን መከላከያ ሰራዊት ህዝብን ይጠብቃል እንጅ ህዝብን ያሸብራል ብለን አንጠብቅም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

♦ “ ትክክለኛ ፍትሕ አይሰጡም” የተባሉት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ከችሎት እንዲነሱ ተጠየቀ !

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar