www.maledatimes.com March, 2019 - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  2019  >  March
Latest

ለውጭ ምንዛሪ ክምችት የተለየ መፍትሔ ካልተገኘ ከነዳጅና ከመድኃኒት ግዥ በስተቀር ሌላ ጥያቄ ማስተናገድ እንደማይቻል ታወቀ

By   /  March 31, 2019  /  Ethiopia  /  Comments Off on ለውጭ ምንዛሪ ክምችት የተለየ መፍትሔ ካልተገኘ ከነዳጅና ከመድኃኒት ግዥ በስተቀር ሌላ ጥያቄ ማስተናገድ እንደማይቻል ታወቀ

ቢዝነስ የልማት ባንክ የማይመለስና አጠራጣሪ ብድር 18.1 ቢሊዮን ብር ደርሷል በሦስት ወራት 344 ሚሊዮን ብር መክሰሩ ተገልጿል በቀጣዮቹ ወራት በተለየ ሁኔታ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሪ ካልተገኘ በስተቀር፣ ከነዳጅና ከመድኃኒት ግዥ በዘለለ የኢኮኖሚውን ፍላጎት ማስተናገድ እንደማይቻልየብሔራዊ ባንክ ገዥ አስታወቁ። የብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) የ2011 በጀት ዓመት የስምንት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሐሙስ መጋቢት19 ቀን 2011 ዓ.ም. ባቀረቡበት ወቅት ነው ይህንን የተናገሩት። የባንኩ ገዥ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት ባለፉት ስምንት ወራት አገሪቱ ለውጭ ገበያ ከምታቀርባቸው ሸቀጦችና አገልግሎቶች የተገኘው የውጭ ምንዛሪ1.64 ቢሊዮን ዶላር መሆኑን አመልክተዋል። በተጠቀሱት ወራት ከወጪ ንግድ የተገኘው የውጭ ምንዛሪ በ2010 ዓ.ም. ተመሳሳይ ወቅት ከተገኘው መጠን ጋር ሲነፃፀር በ9.4 በመቶ ያነሰ እንደሆነገልጸዋል። ከግለሰቦችና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች የተላከ የሐዋላ ገቢ በአጠቃላይ 3.8 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ አስረድተዋል። በተቃራኒው ባለፉት ስምንት ወራት አገሪቱ ከውጭ ለምታስገባቸው ምርቶች 10.5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ መደረጉን፣ ይህም ወጪ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይወቅት ጋር ሲነፃፀር በ1.3 በመቶ ብልጫ እንዳለው ገልጸዋል። በተጠቀሱት ወራት ከወጣው የውጭ ምንዛሪ ውስጥ ለነዳጅ ግዥ የተከፈለው 1.7 ቢሊዮን ዶላር ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዝ አስታውቀዋል። በተጠቀሱት ወራት ወደ አገር ለገቡ ሸቀጦች የተከፈለው የውጭ ምንዛሪና ወደ ውጭ ከተላኩ ሸቀጦች የተገኘው የውጭ ምንዛሪ መሀል የ8.9 ቢሊዮን ዶላርየንግድ ሚዛን ጉድለት እንደሚታይ የገለጹት የብሔራዊ ባንክ ገዥ፣ የተገለጸው ጉድለት የተሸፈነው ከአገልግሎት (በዋናነት ከአየር ትራንስፖርት አገልግሎት)፣ከውጭ በሐዋላ ከተላከ ገቢና ከውጭ ከተገኘ ዕርዳታና ብድር መሆኑን አስረድተዋል። በአሁኑ ወቅት ያለው መጠባበቂያ የውጭ ምንዛሪ ክምችት የ2.6 ወራት ፍላጎትን ለመሸፈን ብቻ የሚበቃ እንደሆነ ገልጸዋል።  የንግድ ማኅበረሰቡ የውጭ ምንዛሪ በተመለከተ የሚያቀርበውን እሮሮ በመጥቀስ የምክር ቤቱ አባላት ስለመፍትሔው ማብራሪያ የጠየቁ ሲሆን፣ የባንኩ ገዥበሰጡት ምላሽ በአሁኑ ወቅት ያለው የውጭ ምንዛሪ መጠን የአገሪቱን ኢኮኖሚ ለማንቀሳቀስና የግሉን ዘርፍ የውጭ ምንዛሪ ፍላጎት ለማስተናገድ የሚችልበትሁኔታ ላይ እንዳልሆነ ጠቁመዋል።  እስካሁን ድረስ ጥቅም ላይ እየዋለ የነበረው የውጭ ምንዛሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ ከተለያዩ አገሮች ጋር ተነጋግረው ማምጣት የቻሉት2.7 ቢሊዮን ዶላር መሆኑን ገልጸዋል። በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥረት እንደተገኘው የውጭ ምንዛሪ ተመሳሳይ ጥረት ተደርጎ በቀጣዮቹ ወራት ተመሳሳይ ሀብትካልተገኘ ኢኮኖሚውን ለማንቀሳቀስ እንደማይቻል ገልጸዋል። “ይህ ካልሆነ ልናደርግ የምንችለው ያለውን የውጭ ምንዛሪ ለነዳጅና ለመድኃኒት ግዥ ብቻ በጥንቃቄ ማዋል ነው፤” ብለዋል። ከዚህ በመለስ ኢኮኖሚውንለማንቀሳቀስ የአምስትና የአሥር ዓመታት ስትራቴጂ ነድፎ መንቀሳቀስን እንደሚጠይቅ አስረድተዋል።  በተመሳሳይ ቀን ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ወደ መንበረ ሥልጣን ሲመጡ የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት አረንቋ ውስጥ ወድቆእንደገጠማቸው ገልጸዋል።  ኃላፊነቱን በተቀበሉ በሳምንቱ የቀረበላቸው የ20 ቢሊዮን ብር የደመወዝ ጥያቄ እንደነበርና ይህንን የአገሪቱ አቅም መመለስ እንዳልቻለ፣ በርካታ ሜጋፕሮጀክቶች ግንባታቸው ቆሞ አገሪቱን ለተጨማሪ የሀብት ብክነት ሰለባ አድርገዋት እንደነበር አስታውሰዋል። ችግሩን ለማስተካካል ባከናወኗቸው ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ተግባራት ኢንቨስትመንትንና ትንንሽ ብድሮችን ሳይጨምር ሦስት ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ሀብትማግኘት እንደቻሉ፣ አገሪቱ የተበደረቻቸውን ግዙፍ የውጭ ብድሮች ክፍያ መፈጸም ባለመቻሏ ሊፈጠር የሚችለውን ቀውስ ቀድሞ ለመከላከል ከቻይናመንግሥት ጋር ባደረጉት ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ሥራ፣ መከፈል የተጀመረው ከ400 ቢሊዮን ብር በላይ የሆነ ብድር የመክፈያ ጊዜ በሰፊ ርቀት እንዲራዘምመቻሉን መግለጻቸው ይታወሳል። የብሔራዊ ባንኩ ገዥ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት ያነሱት ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የገባበትን አጣብቂኝ የተመለከተነበር።  በተሰጠው ተልዕኮና ተግባራቱ ምክንያት ባለሙያዎች የፖሊሲ ባንክ በማለት የሚገልጹትና ከመቶ ዓመታት በላይ የአገልግሎት ቆይታው የሚታወቀው ልማትባንክ፣ በኪሳራ ውስጥ መውደቁንና በፍጥነት መታደግ ካልተቻለ ህልውናውን ሊያጣ እንደሚችል ይናገር (ዶ/ር) አስታውቀዋል። ገዥው እንደገለጹት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በ2011 በጀት ዓመት እስከ የካቲት ወር መጨረሻ ድረስ፣ አጠቃላይ የብድር ክምችቱ 46.17 ቢሊዮን ብር ሆኖ ተመዝግቧል። ከዚህ ውስጥም የማይመለስና አጠራጣሪ ብድሩ የአጠቃላይ ብድሩን 39.45 በመቶ እንደደረሰ ይፋ አድርገዋል። ይህም ማለት ልማት ባንክ ካበደረውአጠቃላይ ብድር ወስጥ 18.1 ቢሊዮን ብር የሚሆነውን ሊመለስ የማይችልና መመለሱ አጠራጣሪ ነው።  ይህ ብቻ አይደለም ባንኩ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሦስት ወራት ውስጥ 344 ሚሊዮን ብር እንደከሰረ፣ ለምክር ቤቱ አስታውቀዋል፡፡ የማይመለስና መመለሱ አጠራጣሪ ከሆነው የባንኩ ብድር ውስጥ ዋነኛውን ድርሻ የሚይዘው ለሰፋፊ እርሻዎች የተሰጠው ብድር እንደሆነ የተናገሩት ገዥው፣አብዛኞቹ ተበዳሪዎች የተበደሩትን ገንዘብ ለሌላ ዓላማ እንዳዋሉትና የእርሻ መሬቱ በሚገኝበት አካባቢ የጥበቃ ቤት እንኳን ያልገነቡ መኖራቸውን ገልጸዋል። ተበዳሪዎቹን ተከታትሎ ለሕግ ማቅረብ እንደሚገባ የገለጹት ይናገር (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አሁን ባለው ቁመና ብድሮቹን የማስመለስም ሆነበኢኮኖሚው ውስጥ የተሰጠውን ተልዕኮ የመወጣት አቅም እንደሌለው ተናግረዋል። በመሆኑም ባንኩን አፍርሶ እንደገና መሥራት እንደሚያስፈልግ፣ ይህ ካልሆነ ግን በራሱ ጊዜ በቅርቡ ሊጠፋ እንደሚችል ገልጸዋል። ይህ ከመሆኑ በፊት መፍትሔ ለመስጠት ኮሚቴ ተዋቅሮ በመሥራት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

Read More →
Latest

የዓለም ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት የመንግሥት ሪፎርም ፕሮግራሞች በጥንቃቄ እንዲታቀዱ አሳሰቡ

By   /  March 31, 2019  /  Ethiopia  /  Comments Off on የዓለም ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት የመንግሥት ሪፎርም ፕሮግራሞች በጥንቃቄ እንዲታቀዱ አሳሰቡ

Read More →
Latest

የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አብረዋቸው የታሰሩ ተከሳሾች በዓቃቤ ሕግ ላይ ተቃውሞአቸውን አሰሙ

By   /  March 31, 2019  /  Ethiopia  /  Comments Off on የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አብረዋቸው የታሰሩ ተከሳሾች በዓቃቤ ሕግ ላይ ተቃውሞአቸውን አሰሙ

በሶማሌ ክልል በጅግጅጋ ከተማና በሌሎች የክልሉ ከተሞች በደረሱ የጅምላ ግድያ፣ አካል ማጉደል፣ አስገድዶ መድፈር፣ በዘር ለይቶ ማጥቃት፣ የሃይማኖት ተቋማት ቃጠሎ፣ ንብረት ማውደምና ሌሎች የወንጀል ድርጊቶች ክስ የተመሠረተባቸው የክልሉ የቀድሞ ፕሬዚዳንትን ጨምሮ በእስር ላይ የሚገኙት ተከሳሾች፣ በዓቃቤ ሕግ ላይ ተቃውሞአቸውን አሰሙ፡፡ ተከሳሾቹ ዓርብ መጋቢት 20 ቀን 2011 ዓ.ም. ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል […]

Read More →
Latest

ያለፉት 3 የሕዝብና ቤት ቆጠራዎች አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረጉ አልነበሩም ሲል ማኅበሩ ወቀሰ

By   /  March 31, 2019  /  Ethiopia  /  Comments Off on ያለፉት 3 የሕዝብና ቤት ቆጠራዎች አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረጉ አልነበሩም ሲል ማኅበሩ ወቀሰ

ማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል ያለፉት ሦስት የሕዝብና ቤት ቆጠራዎች አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረጉ አልነበሩም ሲል የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ብሔራዊ ማኅበር ባወጣው ሪፖርት ወቀሰ። አቤቱታውን እንደሚቀበል የገለፀው ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በማኅበሩ በኩል ቁጥሮችን ከፍ አድርጎ የማቅረብ አባዜ መኖሩን ግን አውቃለሁ ብሏል። ከዚህ በፊት በነበሩ ቆጠራዎች የአካል ጉዳተኞች ቁጥር ዝቅ ብሎ መቅረቡን የሚገልጸው የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ብሔራዊ […]

Read More →
Latest

የመገናኛ ብዙኀን የኅዳሴ ግድቡን ረስተውታል በሚል ተወቀሱ

By   /  March 31, 2019  /  Ethiopia  /  Comments Off on የመገናኛ ብዙኀን የኅዳሴ ግድቡን ረስተውታል በሚል ተወቀሱ

Views: 41 የመገናኛ ብዙኀን አውታሮች የታላቁ ኅዳሴ ግድብ ግንባታን በተባራሪ ዘገባ ከመሸፈን ባለፈ የብሔራዊ መግባቢያ አጀንዳ ማድረጉን ረስተውታል የሚል ወቀሳ ቀረበባቸው። የግድቡ ግንባታ ሕዝባዊ አስተባባሪ ምክር ቤት ጽሕፈት የተጣራ መረጃን ይዞ ወደ መገናኛ ብዙኃን ለመቅረብ ወራትን ስለፈጀሁ የፕሮጀክቱ የዘገባ ሽፋን እንዲቀንስ አንድ ምክንያት ሆኗል ያለ ሲሆን፣ የተቀዛቀዘውን የሕዝብ ተሳትፎ ለማነቃቃትና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር እየሠራሁ ነው […]

Read More →
Latest

ከረጲ የኃይል ማመንጫ ጋር በተያያዘ በሕግ ተጠያቂ የሆነ አካል የለም ተባለ

By   /  March 31, 2019  /  Ethiopia  /  Comments Off on ከረጲ የኃይል ማመንጫ ጋር በተያያዘ በሕግ ተጠያቂ የሆነ አካል የለም ተባለ

ከዛሬ ሰባት ወር በፊት ከተመረቀ በኋላ በቀናት ወስጥ ስራ ያቆመው የረጲ ኃይል ማመንጫ 50 ሜጋ ዋት እንዲያመነጭ ታስቦ ቢገነባም ግማሹን ብቻ ማምረት እንዲችል በመዳረጉ ኃላፊነት ወስዶ እስካሁን በሕግ ተጠያቂ የሆነ ድርጅትም ወይም ግለሰብ አለመኖሩ በፓርላማ አባላት ጥያቄ ቀረበበት። በ2ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የኃይል ማመንጫው በተያዘለት ጊዜ ካለመጠናቀቁም በተጨማሪ፤ እንዲያመነጭ ከታሰበው የኃይል መጠን ወደ […]

Read More →
Latest

አዲስ አበባ 74 ጊዜያዊ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቢያስፈልጋትም እየተገነቡ ያሉት 18 ናቸው

By   /  March 31, 2019  /  Ethiopia  /  Comments Off on አዲስ አበባ 74 ጊዜያዊ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቢያስፈልጋትም እየተገነቡ ያሉት 18 ናቸው

በአዲስ አበባ ከተማ 74 ጊዜያዊ የደረቅ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ እና መለያ ቦታዎች ቢያስፈልጉም ግንባታቸው እየተካሔደ ያለው የ18ቱ ብቻ መሆኑ ታወቀ፡፡ በከተማዋ ደረቅ ቆሻሻ ከምንጩ ሳይለይ ወደ ጊዜያዊ ማቆያና መለያ ቦታዎች መከመሩ ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉትን ጥሬ እቃዎች ከማስቀረቱም ባሻገር ከ60 ዓመታት በላይ የከተማዋን ቆሻሻ በመሸከም እያገለገለ ላለው ረጲ መጨናነቅን እየፈጠረ መሆኑ በተደጋጋሚ ይነሳል። በዚህም ባለፈው ዓመት […]

Read More →
Latest

ለተረጂዎች የተገዛ 928 ኮንቴነር ዘይት ለ10 ወራት በሞጆ ደረቅ ወደብ ይገኛል

By   /  March 31, 2019  /  Ethiopia  /  Comments Off on ለተረጂዎች የተገዛ 928 ኮንቴነር ዘይት ለ10 ወራት በሞጆ ደረቅ ወደብ ይገኛል

• ዘይቱ የአደጋ ሥጋት የተደቀነበት በመሆኑ የጤና ፍተሻ ሊደረግበት ነው ተባለ ለ10 ወራት በሞጆ ደረቅ ወደብ የተቀመጠው የብሔራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን 928 ኮንቴነር ዘይት የአደጋ ሥጋት የተደቀነበት በመሆኑ የጤና ፍተሻ ሊደረግበት ነው። ኮሚሽኑ ከውጭ አገራት ያስገባው 928 ኮንቴነር ወይም 24 ሚልዮን 684 ሺሕ 800 ሊትር ዘይት ከሞጆ ደረቅ ወደብ ከወራት በፊት መውጣት የነበረበት […]

Read More →
Latest

ክልሎች ከአዲስ አበባ ጎዳና በተነሱ ዜጎች ማቋቋም ላይ ውዝግብ ውስጥ ገቡ

By   /  March 31, 2019  /  Ethiopia  /  Comments Off on ክልሎች ከአዲስ አበባ ጎዳና በተነሱ ዜጎች ማቋቋም ላይ ውዝግብ ውስጥ ገቡ

የአማራ ክልል የጎዳና አዳሪ ሕፃናትን በማቋቋም ሥም ለረጅም ዓመታት ከኖሩበት ከተማ ለማስወጣት መጣደፍ ተገቢ አይደለም ብሏል በቅርቡ የአዲስ አበባ አስተዳደር በጎዳና የሚኖሩ ዜጎችን በማንሳት አብዛኞቹን ወደ ክልል ለመመለስ ተስማምቻለሁ በሚል አዲስ ፕሮጀክት ተግባራዊ ቢያደርግም ክልሎች ለመቀበል ባለመፍቀዳቸው ውዝግብ ውስጥ እየገቡ ነው። ከወር በፊት ከአዲስ አበባ ጎዳና አዳሪዎችን ማንሳት የተጀመረው በሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር አስተባባሪነትም ጭምር […]

Read More →
Latest

ሕገ ወጥ ኤጀንሲዎች በርካታ ሴቶችን ለዝሙት አዳሪነት እየተጠቀሙባቸው መሆኑ ተገለጸ

By   /  March 31, 2019  /  Ethiopia  /  Comments Off on ሕገ ወጥ ኤጀንሲዎች በርካታ ሴቶችን ለዝሙት አዳሪነት እየተጠቀሙባቸው መሆኑ ተገለጸ

ሕገ ወጥ አሰሪና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች በመርካቶ አካባቢ ምንም ፈቃድ ሳይኖራቸው፣ በርካታ ሴቶችን ወደ ውጭ አገር እንወስዳችኋለን በሚል ሰበብ በአንድ ቤት ውስጥ በማከማቸት ለዝሙት አዳሪነት ጭምር እየተጠቀሙባቸው መሆኑን አዲስ ማለዳ አረጋገጠች። በጉዳዩ ዙሪያ አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው የአዲስ አበባ አስተዳደር የሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አስፋው መብራቴ፣ በመርካቶ አካባቢ እንደዚህ ዓይነት ወንጀሎች እንደሚፈጸሙ መረጃዎች […]

Read More →
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar