www.maledatimes.com ከረጲ የኃይል ማመንጫ ጋር በተያያዘ በሕግ ተጠያቂ የሆነ አካል የለም ተባለ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ከረጲ የኃይል ማመንጫ ጋር በተያያዘ በሕግ ተጠያቂ የሆነ አካል የለም ተባለ

By   /   March 31, 2019  /   Comments Off on ከረጲ የኃይል ማመንጫ ጋር በተያያዘ በሕግ ተጠያቂ የሆነ አካል የለም ተባለ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 20 Second

ከዛሬ ሰባት ወር በፊት ከተመረቀ በኋላ በቀናት ወስጥ ስራ ያቆመው የረጲ ኃይል ማመንጫ 50 ሜጋ ዋት እንዲያመነጭ ታስቦ ቢገነባም ግማሹን ብቻ ማምረት እንዲችል በመዳረጉ ኃላፊነት ወስዶ እስካሁን በሕግ ተጠያቂ የሆነ ድርጅትም ወይም ግለሰብ አለመኖሩ በፓርላማ አባላት ጥያቄ ቀረበበት።

በ2ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የኃይል ማመንጫው በተያዘለት ጊዜ ካለመጠናቀቁም በተጨማሪ፤ እንዲያመነጭ ከታሰበው የኃይል መጠን ወደ 25 ሜጋ ዋት መቀነሱ የሚታወስ ነው ። ይህንም ተከትሎ እስካሁን ለተፈጠረው ችግር በሕግ ተጠያቂ የሆነ አካል አለመኖሩ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቅሬታን አስነስቷል።

የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ2011 በጀት አመት የስምንት ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ለምክር ቤቱ ባቀረበበት ወቅት ከምክር ቤት አባላት በኩል ጥያቄ የተነሳ ሲሆን፤ ለረጲ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የኃይል አለመጣጣም እንዴት ተጠያቂ አካል እስካሁን አልተገኘም ሲሉ በርካታ የምክር ቤቱ አባላት ጥያቄያቸውን የሰነዘሩ ሲሆን፤ ተጠያቂ አካላትን ለሕግ ከማቅረብ አንፃርም ሚንስትር መስሪያቤቱ ንዝህላልነት እንደሚታይበት ተናግረዋል።

ከሕዝብ እንደራሴዎች ለተነሳው ጥያቄ ሚንስትሩ ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) ምላሽ ሰጥተውበታል። መጀመሪያም በተቋራጩ ድርጅት እና በኤሌክትሪክ ኃይል መካካል ውል ሲፈፀም ክፍተት እንደነበረበት ያወሱት ስለሺ፤ ‹‹ችግሩ ጠንካራ ነው›› ሲሉ ይጀምራሉ። 50 ሜጋ ዋት ያመነጫል ተብሎ ቢታሰብም በአካል ሲታይ ግን የተባለውን ያህል ኃይል ማመንጨት እንደማይችል ያስታውቃል ብለዋል። ችግሩ ከተፈጠረ በኋላ በርካታ የድርድር ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።

10 ሚሊዮን ብር የሚገመት የማካካሻ ስራ እንዲሰራ ኩባንያው ተጠይቆ ፈቃደኛ ሳይሆን እንደቀረና ይህንንም ተከትሎ የቻይና መንግስት ጣልቃ ገብቶ ስራው እንዲቀጥል እንደተደረገ ከሚንስትሩ የተገኘው ምላሽ ያመላክታል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከተወጣጡ ምሁራን ጋር በቅንጅት በመስራት በኃይል ማመንጫው ላይ ጠቃሚ ምክሮች እየተቀበሉ እንደሆነ ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) ተናግረው፤ ተጠያቂ ናቸው የሚባሉትን ግለሰቦችም ወይም ድርጅቶችን ወደ ሕግ ከማቅረብ አንፃር በሚንስትር መስሪያ ቤቱ የተቀመጠ አቅጣጫ መኖሩን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል፤ የካምብሪጅ ኃይል ማኔጅንግ ዳይሬክሬተር የሆኑት ሳሙኤል ዓለማየሁ በታህሳስ ወር በአዲስ ማለዳ በወጣ ዘገባ ላይ በሰጡት ምላሽ መሰረት፥ ድርጅታቸው የሚጠበቅበትን 1000 ቶን በቀን ማስወገድና 1850 ጊጋ ዋት ሀወር ማመንጨት የሚችል ፕሮጅክት ሠርቶ በውሉ መሰረት አስረክቧል።

ሚኒስትሩ ስለሺ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ ከኹለት አመት በፊት መጠናቀቅ እንደነበረበትና በወቅቱ በነበረ ችግር ተቋርጦ እንደነበር አስታውሰው አሁን ወደ ሙከራና ‹‹ኮሚሽኒንግ›› ስራ እንደተገባ ገልፀዋል።

በተያዘው በጀት አመት በስምንት ወራት የሙከራ አፈፃፀሙም 21 በመቶ እንደሚጠጋ ታውቋል። ከዚህም ጋር ተያይዞ የኃይል ማመንጫው የምረቃ ስነ ስርዓቱ ቢከናወንም ሙሉ በሙሉ አለመጠናቀቁን ሚንስትሩ ለምክር ቤቱ አስረድተዋል።

ማመንጫው እ.አ.አ. ከሰኔ 24፣ 2018 እስከ መስከረም 10፣ 2018 ድረስ በሥራ ላይ የነበረ ወቀት 48 ሺሕ ኪሎ ግራም ቆሻሻ በመጠቀም 9.75 ሚሊየን ኪሎ ዋት ሀወር ኤሌክትሪክ ማመንጨት ችሎ ነበር። ይሁን እንጂ በጥር መጨረሻ ላይ በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ በወጣ ዘገባ ላይ ማመንጫው ቆሻሻ ከማቃጠል የዘለለ ሚና የለውም ሲሉ የሲቪል ኤንድ ኢንቫይሮሜንታል ኢንጂነሪንግ ባለሙያ የሆኑት ሰሃዳት ሑሴን (ዶ/ር) ገልጸው ነበር።

ባለሙያው እንደ ምክንያት ያቀረቡት በኢትዮጵያ የሚመነጨው አብዛኛው ቆሻሻ ተፈጥሯዊና ከፍተኛ እርጥበት ያዘለ መሆኑን ሲሆን፥ ቆሻሻውን ለማድረቅ ከሚያስፈልገው አኳያ ሲታይ “ፕሮጀክቱን ዋጋ ቢስ” ያሰኘዋል ብለውት ነበር። ይሁን እንጂ፣ ከማመንጫው የሚገኘውን ኤሌክትሪክ በ0.07 ዶላር በኪሎ ዋት ሀወር ማቅረብ ይቻላል ሲሉ ሳሙኤል የባለሙያውን አስተያየት አጣጥለዋል።

በኤሌክትሪክ ታሪፍ፣ ኢትዮጵያ ከዓለም ትንሹን የምታስከፍል ሲሆን በኪሎ ዋት ሀወር 0.06 ዶላር ኤሌክትሪክ ታቀርባለች። ይህ አገሪቷ አንድ ኪሎ ዋት ሀወር ኤሌክትሪክ ለማመንጨት ከምታወጣው ወጪ በ0.03 ዶላር ያነሰ ነው።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 5 years ago on March 31, 2019
  • By:
  • Last Modified: March 31, 2019 @ 1:42 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar