www.maledatimes.com ክልሎች ከአዲስ አበባ ጎዳና በተነሱ ዜጎች ማቋቋም ላይ ውዝግብ ውስጥ ገቡ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ክልሎች ከአዲስ አበባ ጎዳና በተነሱ ዜጎች ማቋቋም ላይ ውዝግብ ውስጥ ገቡ

By   /   March 31, 2019  /   Comments Off on ክልሎች ከአዲስ አበባ ጎዳና በተነሱ ዜጎች ማቋቋም ላይ ውዝግብ ውስጥ ገቡ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 14 Second

  • የአማራ ክልል የጎዳና አዳሪ ሕፃናትን በማቋቋም ሥም ለረጅም ዓመታት ከኖሩበት ከተማ ለማስወጣት መጣደፍ ተገቢ አይደለም ብሏል

በቅርቡ የአዲስ አበባ አስተዳደር በጎዳና የሚኖሩ ዜጎችን በማንሳት አብዛኞቹን ወደ ክልል ለመመለስ ተስማምቻለሁ በሚል አዲስ ፕሮጀክት ተግባራዊ ቢያደርግም ክልሎች ለመቀበል ባለመፍቀዳቸው ውዝግብ ውስጥ እየገቡ ነው።

ከወር በፊት ከአዲስ አበባ ጎዳና አዳሪዎችን ማንሳት የተጀመረው በሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር አስተባባሪነትም ጭምር ተነሽዎቹ እስከ 45 ቀናት በማዕከል አገግመው ወደየተወለዱበት ክልል እንዲሔዱ ስምምነት ተደርሷል በሚል ነበር። በወቅቱ አዲስ ማለዳ በጉዳዩ ላይ በሠራችው ʻሐተታ ዘ ማለዳʼ የአዲስ አበባ እና የፌደራሉን የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊዎች አነጋግራ የነበረ ሲሆን በወቅቱም ተነሽዎቹ በአዲስ አበባ ማዕከላት ካገገሙ በኋላ በዘላቂነት ለማቋቋም ክልሎች ኃላፊነት ወስደው ይረከቧቸዋል የሚል ስምምነት መደረሱን ተናግረው ነበር።

በዚህም 50 ሺሕ ጎዳና አዳሪዎችን ለማንሳት ያቀደው ከተማ አስተዳደሩ በመጀመሪያ ዙር እስከ አምስት ሺሕ ለማንሳት እቅድም ይዞ ነበር። በዚህም ሥራው በተጀመረ በቀናት ውስጥ ይነሳሉ ተብሎ የታቀደው 2 ሺሕ የጎዳና አዳሪዎች ቢሆንም ቁጥሩ ወደ 3 ሺሕ አሻቅቧል። ይህም ሆኖ ተነሽቹን በማዕከላት ይዞ የሚገኘው አስተዳደሩ ወደ ክልሎች መመለስ ያለባቸውን ሰዎች ለመላክ ለክልሎች በደብዳቤ ቢጠይቅም አዎንታዊ ምላሽ አለማግኘቱ ታውቋል። ይህም በፕሮጀክቱ ላይ ከወዲሁ ውዝግብ ፈጥሯል።

ጎዳና አዳሪዎቹን አሁን ላይ ተቀብሎ ለማቋቋም ዝግጁ አለመሆኑን በደብዳቤ ለአዲስ አበባ ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ያሳወቀው የአማራ ክልል ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ለተነሺ ዜጎች በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በሥማቸው ተሰብስቦ እያለ ለእያንዳንዳቸው አራት ሺሕ ብር ብቻ እየሰጡ ከአዲስ አበባ ወደ ክልሎች ለመላክ መታሰቡን ኮንኗል። አራት ሺሕ ብሩ ተነሽዎችን ለማቋቋም ሆነ በዘላቂነት ችግራቸውን ለመፍታት በቂ አይደለም ሲልም ውድቅ አድርጎታል።

አዲስ ማለዳ ከምንጮቿ ያገኘችው የአማራ ክልል ደብዳቤ በክልሎች በኩል ቃል የተገባውን ገንዘብ ሳናገኝና በቂ የቅድመ ዝግጅት ሥራ ሳይከወን በጥድፊያ የመመለስ ሥራ መሰራቱ ውጤታማ ስለማያደርግ እንደማቀበለው ያስገነዝባል።

የአማራ ክልል አክሎም፣ የሚነሱ ዜጎች ብዛት፣ የሚሔዱበት አካባቢ፣ መሰማራት የሚፈልጉበት ሥራ እና መሰል ጉዳዮች ሳይጣሩ ሰዎችን አፍሶ ወደ ክልሎች መላክ የመንግሥትን ሀብት ከማባከን ያለፈ ውጤት የለውም በማለት እንደማይቀበለው አሳውቋል።

የተላከልን መረጃ ዕድሜያቸው እስከ 45 ዓመት ድረስ እና ለበርካታ ዓመታት በከተማዋ ነዋሪ ሆኖ እያለ፣ ሕጻናትን ወደ ቤተሰብ ማቀላቀል በሚል ለበርካታ ዓመታት ከኖሩበት ከተማ አንስቶ መላክ ዜጎች በፈለጉበት ቦታ የመኖር ሕገ መንግሥታዊ መብትን የሚጻረር ነው ሲልም የአማራ ክልል ደብዳቤ አትቷል። በግልባጭም ለማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የክልሉ ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረከብ የተባለውን ዜጎች ፍላጎት ለመጥናት ባለሙያ መላኩን ጠቅሶ ፣ ለዜጎቹ ያልሆነ ተስፋ እንደተሰጣቸውና የተሰጣቸውም ተስፋ ከሌለ ተመልሰው ወደ አዲስ አበባ እንደሚገቡ መናገራቸውን እንደተረዳ አመልክቷልል።

ከ90 ሺሕ በላይ ተፈናቃይ ባሉበት እንዲሁም ከአፋር አሚባራ የተፈናቀሉት ከአንድ ሺሕ በላይ የጎዳና ልጆችን ሳናቋቁም ተጨማሪ ዜጎችን ያለምንም የመቋቋሚያ በጀት መረከብ እንደማይችልም ለአዲስ አበባ አስተዳደር አሳውቋል።

ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ጉዳዩ የሚመለከተው የአዲስ አበባውን ቢሮ ነው ብሏል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽ እንዲሰጠን ጠይቀን በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም ዓይነት መረጃ እንደሌለው ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ የጎዳና ተዳዳሪዎችንና ቀጥታ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች ለማደራጀት በቅርቡ ሥራ የጀመረው ፕሮጀክት በአንዳንድ ክልሎች ዘንድ ተቀባይነት እያገኘ አለመሆኑን የአዲስ ማለዳ ምንጮች ለዝግጅት ክፍላችን ተናግረዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 5 years ago on March 31, 2019
  • By:
  • Last Modified: March 31, 2019 @ 1:28 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar