www.maledatimes.com አንድዬ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  POEMS  >  Current Article

አንድዬ

By   /   August 4, 2014  /   Comments Off on አንድዬ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 14 Second

አንድዬ፡

ከማተቤ መለሰ

ዛሬ ደስ ይበላቸው፡ የዘብቱ ይሳቁ፣
ብቀላውን ከቻሉት፡ በቅርብም ሆነ በሩቁ።

ለጀግና ጽናቱ ነው መመኪያው፡ የሃገር ፍቅር ነው በትሩ፣
የጊዜ ጉዳይ እነጅ፡ ጠላቱም መውደቁ አይቀርም ከሰሩ።

አንድዬ!! ወገን ሊታደግ ህይወቱን መነዘረ፣
በሰቃዩ የመለያየት አጥርን ሰባበረ።

በሃሳብ ሳንገናኝ፡ እንደሰናውር ግምበኛ፣
ተቧድነን ስንቧከስ፡ እንደዚያ እኛው በእኛ።

አንድ አደረገን አንዳርጋቸው፡ አስተሳሰረን በደሩ፣
ተቆርቋሬውን ክፍል፡ ለሃገሩና ለክብሩ።

በተነው ብለው ሲቦረቁ፡ እንደዚያ በድል ነሽነት፣
አንድዬ!! በከፈለው ዋጋ ወገን ተሰባሰበ በአንድነት።

ያለአታለለው በድሎት መኖር ተንደላቅቆ በክብር፣
ለሃገሩ የታገለው አንድዬ!! በቁርጠኝነት ከምር።

ለበረሃ ጉዞ፡  ማቄን ጨርቄን ያላለው፣
ለነጻነት፡ አምርሮ ከልቡ የታገለው።

አየነው ለሃገሩ ሲበራ፡ የመቅረዝ ሻማ ሆኖ፣
በእኛ ላይ እዳ በመጣል፡ እንድንፋለም አስክኖ።

አንድዬ!! የድርሻውን በመወጣት ሰፈፈ፣
በትግሉ ህያው ታሬክን፡ በደማቅ ብዕሩ ጻፈ።
2
አንድዬ!! ለሃገሩ ሲል፡ ለነፍሱ ያልሰሰተ፣
እድሜውን ሙሉ፡ ለነጻነት አጥበቆ የዋተተ።

አንድዬ!! እራሱን ሰጥቶ በአርያነት አስተምሮ፣
አሰልፎናል የኸው፡ እኛን እንደድር አስተሳሰሮ።

አሉላን አስታወሰኝ አንድዬ!! የቀይ ብሃሩን መከታ፣
ግብጽና ቱርክን አጣምሮ፡ በአንድ በትር የመታ።

ለእኔ ትዮድሮስ ነው አንድዬ!! የቋራው መይሳው ካሳ፣
ለሃገሩ አንድነት ሲል፡ ለህይወቱ ያልሳሳ።

ገብርዬንም ይመስለኛል፡ የወደቀውን መቅደላ፣
መሳሬያው እሳት እንደተፋ፡ ትጥቁ ለአንድ ቀን ሳይላላ።

አሞራው ውብነህ ልበለው፡ ወይንስ አብዴሳ አጋ፣
እንዲሁ ስባዝን ውየ አድራላሁ፡ ለአንዲዬ!! አቻ ፍለጋ።

ወይንስ ልበለው ዝም ብዬ፡ ነህአንተ ሃይለማርያም ማሞ፣
የትኛው ይገለጸው ይሆን? ማንንስ ላስታውስ ደግሞ?

አሁን አገኘሁ መሰል ድካሜን  ላቁም አለቀ፣
ሳይመጥነው አይቀርም አባኮስትር በላይ ዘለቀ።

ወደሗላ በመመለስ ቀደምቶቸን ማስታወሱን ልተውና፣
ይልቁን ዛሬ ልበለው አንድዬን!! ከጀግኖች ሁሉ የላቀው ጀግና።

እኔም በድርሻየ ቃል ገባለሁ፡ ከልብ በማምረር ለአንድዬ!!
ትግሉ የጠየቀውን ዋጋ ለመክፈል፡ የእሱን አለማ ተከተዬ፣
ትግሉ የጠየቀውን ዋጋ ለመክፈል፡ የእሱን አላማ ተከትዬ።
ሃምሌ 2006

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on August 4, 2014
  • By:
  • Last Modified: August 4, 2014 @ 6:30 pm
  • Filed Under: POEMS

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

ግፍ መሸከም ይብቃን ( በ ይግዛው እያሱ)

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar