www.maledatimes.com የኬንያ የምርጫ ኮሚሽን ከፍተኛ ኃላፊ ተገድለው ተገኙ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  AFRICA  >  Current Article

የኬንያ የምርጫ ኮሚሽን ከፍተኛ ኃላፊ ተገድለው ተገኙ

By   /   July 31, 2017  /   Comments Off on የኬንያ የምርጫ ኮሚሽን ከፍተኛ ኃላፊ ተገድለው ተገኙ

    Print       Email
0 0
Read Time:44 Second

 

በቀጣዩ ሳምንት እንደሚደረግ በሚጠበቀው የኬንያ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ቁልፍ ሚና እንደሚጫወቱ ይጠበቁ የነበሩት የምርጫ ኮሚሽኑ ከፍተኛ ኃላፊ ድብደባ ተፈጽሞባቸው ተገድለው መገኘታቸውን የምርጫ ኮሚሽኑ ሊቀመንበር ዛሬ አስታውቀዋል፡:
===============

ከጥቂት ቀናት በፊት መጥፋታቸው ተነግሮላቸው የነበሩት የምርጫ ኃላፊው ክሪስቶፈር ምሳንዶ ሞርጉ በተባለች ከተማ አንገታቸውና ጭንቅላታቸው አካባቢ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ሞተው መገኘታቸውን ሊቀመንበሩ በሐዘን ተውጠው ተናግረዋል፡፡የኃላፊው ተገድለው መገኘትም በምርጫው ላይ መጥፎ የሆነ ምስል እንደሚፈጥር ተገምቷል፡፡
‹‹የምርጫ ኮሚሽኑ ሊቀመንበር ቺቡካቲ ለጋዜጠኞች በሰጡት አስተያየት ‹‹የኮሚሽኑን ሰራተኛ ማንና ለምን እንደገደለው ማወቅ እንፈልጋለን፡፡መንግስት ለሁሉም የኮሚሽኑ አባላት ጥበቃ እንዲሰጥም እንጠይቃለን››ብለዋል፡፡

ተገድለው የተገኙት ሓላፊ በኮሚሽኑ የኢንፎርሚሽን ቴክኖሎጂ ክፍል ተመድበው ይሰሩ ነበር፡፡በምርጫው ወቅትም እርሳቸው የሚመሩት ዲፓርትመንት የመራጮችን ድምጽ ከስርቆት ለመታደግ የባዮሜትሪክ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በኤሎክትሮኒክስ ዘዴ የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱን ለመቆጣጠር ተዘጋጅቶ ነበር፡፡

በኬንያ የሚገኙ የአሜሪካና የእንግሊዝ ዲፕሎማቶች የባለስልጣኑ መገደል እንዳሳዘናቸው በመግለጽ መንግስት በአስቸኳይ የግድያቸውን ምስጢር እንዲፈታ ጠይቀዋል፡፡
በኬንያ ምርጫውን ተከትሎ የሚሰማው ነገር ከቀን ወደቀን የተለየ መልክ እየያዘ በመሆኑ በአገሪቱ የሚገኙ ስደተኛ ኢትዮጵያዊያን የጭንቀት ህይወት መምራት ጀምረዋል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Traveler’s Alleged Crimes and Robbery at Bole Airport Raise Concerns

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar