www.maledatimes.com የበላችው ያስገሳታል በላይ በላዩ ያጎርሳታል - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

የበላችው ያስገሳታል በላይ በላዩ ያጎርሳታል

By   /   August 1, 2017  /   Comments Off on የበላችው ያስገሳታል በላይ በላዩ ያጎርሳታል

    Print       Email
0 0
Read Time:9 Minute, 38 Second

ምሕረት ዘገዬ

በዚህ ዘመን ተማሪዎች “አጤሬራ” የሚሉት ፈሊጥ አላቸው፡፡ አጤሬራ ማለት አንድ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ፈተና ክፍል ወይም አዳራሽ ሲገባ ደብቆ ይዞት የሚገባው በአጭር በአጭሩ የተጻፈ ማስታወሻ ማለት ነው፡፡ ዘመኑ የኩረጃና የማጭበርበር ነው፡፡ ኮራጅና ከማስታወሻ ገልባጭ ተማሪ “እየተመረቀ” አገር ምድሩን እየሞላው ነው፡፡ ለማንኛውም ከተማሪዎች ለየት የሚለው የኔ አጤሬራ ከዚህ በታች ይቀጥላል፡፡

A ሰሞኑን በአንዳንድ የአማራው አካባቢዎች ተዘዋውሬ ነበር፡፡ ስለታዘብኳቸው ነገሮች ፎቶግራፎች ነበሩኝ፡፡ ግን በጣም የታወቀን ነገር ለማሳወቅ መድከም እንደማያስፈልግ በመረዳት አሁን አልለጥፋቸውም፡፡

የአማራው ክልል፡-

—  መንገድ የለውም፡፡ ትምህርት ቤት የለውም፡፡ ፋብሪካና ኢንዱስትሪዎች የሉትም፡፡ አብዛኛው ሕዝብ እልም ባለ ድህነትና ኋላ ቋርነት ውስጥ ይኖራል፡፡  የሕዝቡ ኑሮ ከ26 ዓመታት በፊት ከነበረውም እጅግ በወረደ ሁኔታ ስቃይ ውስጥ ነው፡፡ ትምህርት ቤትና የጤና ተቋማት አሉት ከተባለም ኋላ ቀርና የሰውና የቁሣቁስ ድህነት የሚያጠቃቸው ናቸው፡፡ ጥሩ ሞት እንኳን እንዳይሞት ይህም ዕድል ሆነና በቶሎ ምድርን እንዳይሰናበት ተልክሎ ቀስ እያለና እየተሰቃዬ እንዲሞት በወያኔ የተፈረደበት ሕዝብ መሆኑን በዐይኔ በብረቱ ታዝቤያለሁ፡፡ ምሥክርነቴ የክሬን ነውና አልዋሻችሁም፡፡ ደስ የሚለኝ ግን በዚህች ምድር ለዘላለም የሚኖር ምንም ዓይነት ሕይወት ያለው ፍጡር የለም፡፡ ገዳይም ሟችም የመጨረሻ ፍርዳቸውን የሚያገኙበት ሌላ ፍትሃዊ ዓለም መኖሩን ስለማምን በዚያ ብቻ እጽናናለሁ፡፡ “ሁሉም ነገር የከንቱ ከንቱ ነው፤ ንፋሰንም እንደመከተል…” ብሏል ነቢዩ ቀደም ሲል፡፡ ስለዚህም አንድ ሰው ቀን ሰጠኝ ብሎ የክፋቱን ጥግ ሲያሳይህ የዚያን ግልባጭ ከወዲሁ በመመልከት ልታዝንለት እንጂ ብዙም ልትፈርድት አይገባም፡፡ ቀላል ሰው እንደብረት ድስት ነው፡፡ ብረት ድስት ለቅዝቃዜም ለሙቀትም እጅግ ቅርብ ነው፡፡ ቀትረ ቀላል ዜጋም እንዲሁ ነው፡፡ አስተሳሰቡ ከአፍ እስካፍንጫው እንኳ የማይደርስ በመሆኑ ነገን ቀርቶ የዛሬይቱን ምሽትም አያይም፡፡

— አንድ ት/ቤት ጎበኘሁ፡፡ አጥር የለውም፡፡ መማሪያ ክፍሎቹ በርም ሆነ መስኮት የላቸውም፡፡ ማለቴ በሮቹም መስኮቶቹም ወላልቀው ጠፍተው ክፍሎቹ የዓሣማ ጋጣ ይመስል በጭቃና በወረቀት ተሞልተው በነዚያ ውስጥ ነው ተማሪዎች “የሚማሩት”፡፡ የመምህራን ማረፊያና ቢሮዎች እንደነገሩ በአንድ ላይ ተጫፍረው አሉ ለማለት አሉ እንጂ በአግባቡ የሉም፡፡ ከተለጣጠፉ የማስታወቂያ ወረቀቶች እንደተረዳሁት መምህራኑ ራሳቸው እንግሊዝኛውን ይቅርና አማርኛውንም እያወላገዱት ነው – የምላችሁ አማርኛ በአማራው አካባቢም ፈተና ላይ ወድቃለች፡፡ ወያኔ ትግሬ አማራውን ለመበቀልና የአማራን ዘር ለማጥፋት ምን ያህል ርቀት እንደተጓዘ ለመረዳት ምቹ ቦታ ተቀምጦ ወሬና አሉቧልታ ከመኮምኮም ይልቅ የአማራ አካባቢዎችን ተዟዙሮ በመጎብኘት እውነቱን ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ አማራ እያለቀለት ነው! ቅስቀሳ አልያዝኩም፡፡ እውነቱን እየተናገርኩ እንጂ፡፡ እውነትን መናገር ደግሞ ከዘረኝነትም በሉት ከጎጠኝነት ይለያል፡፡ እውነትን መደበቅ ወይም ለመናገር አለመፈለግ ነው ይልቁንስ ዘረኝነት፡፡

— በብዙ የአማራ አካባቢ መብራት የለም – የሌለው ደግሞ ለሰዓታት ወይም ለቀናት ብቻ ሣይሆን ከናካቴው ነው – ለ15 ቀናት አንድ ከተማ ውስጥ ተቀምጬ ከ30 ይሁን 40 ደቂቃ በስተቀር ሁልጊዜ ጨለማ ነበር፡፡ ለምን እንደሆነ አልገባኝም – ሲፈልጉ ለደቂቃዎች ብልጭ ያደርጉትና በዕንቁልልጭ የአማሮችን አንጀት ያበግኑታል – አማራ በጨለማ ውስጥ ቆሞ ጌቶቹን ትግሬዎች መብራት ይዞ እያበላ ነው፡፡ ሕዝቡ ለመሠረታዊ ፍላጎቶቹ የሚጠቀመው የቻለ ትናንሽ ጄኔሬተሮችን በመግዛት ያልቻለ እንደጥንቱ ክትክታን በመቀጥቀጥ ነው፡፡ ቡና ቤቶችና የግል ሐኪም ቤቶች የሚበላሹ ነገሮቻቸውን በፍሪጅ ለማስቀመጥ ጄኔሬተር መግዛት ይኖርባቸዋል – ለተወሰነ ሰዓት እንኳን ለማቀዝቀዝ፡፡ ሞባይሌን ቻርጅ ለማድረግ ለአንድ ጊዜ ቻርጅ አምስት ብር ከፍዬ ነው ቴክኖሎጂያዊ ግንኙነቴን የቀጠልኩት፡፡ አማራ አካባቢ መኖር አሣር ነው፡፡ በሺዎች ዓመታት ወደኋሊት መጓዝ፡፡ ትግሬዎች በአማራ ነፍሰ ሥጋ እየተጫወቱ ነው፡፡ ድመት በቁጥጥሯ ሥር ያስገባቻትን ዐይጥ ከመመገቧ በፊት ወደላይ እየወረወረች በማፍረጥ ብዙ ከተጫወተችባት በኋላ ትለላታለች፡፡ አማራም እንደታወረች ዐይጥ ሆኖ በወያኔዎች መጫወቻ ሆኗል፡፡ ይህን ጽሑፍ የምታነብ አማራ ለበቀል እንዳትነሳሳ – ለእውናዊም ለምናባዊም በቀል፡፡ በቀልን ለተበቃዩ ህጋዊ አካል ብቻ ካንጀትህ ሆነህ ስጠውና አንተ ግን ወደ ኅሊናህ ተመለስ ይልቁንስ፤ ተመልሰህም ከሰማያዊ አባትህ ጋር አሁኑ ታረቅ – መጣላትህ ነው ለዚህ ዓይነቱ ጉግማንጉግ መንግሥት የዳረገህ፡፡ ሁሉም ሊሆን የግድ ነው፡፡ የሚሆነው ሁሉ ሆኖ ሲያልቅ ለሚሆነው ተዘጋጅ እንጂ ሊሆን ባለው ነገር ጊዜህን አታባክን፡፡ ለመጨረሻው አርማጌዴዎን ግን ስንዱ ሁን፡፡ ያም ቀን ቀርቧል፡፡ ዛሬ ማታ ወይ ነገ ጧት፡፡ ካልሆነም ሰሞኑን ጠብቅ፡፡

— በአማራው አካባቢ እንኳንስ ለትልቅ ፋብሪካ የሚሆን ለጥቃቅን የጎጆ ኢንዱስትሪ የሚሆን የኤሌክትሪክ ኃይል የለም፡፡ በዐዋጅ የታገደ ነው የሚመስለው፡፡ ብኣዴን የሚባለው ወፍ ዘራሽ መናጆ ምን እየሠራ እንደሆነና ምን ዓይነት አፍዝ አደንግዝ እንደተዞረበት ማወቅ አልቻልኩም፡፡ አጠገቡ የምትገኝ ትግራይ በልማትና በቴክሎጂ ስትንበሸበሽ አማራው ግን በዳፍንት ውስጥ ሲንጠራወዝ ብኣዴን ተብዬው ይህን የአሜሪካንና የቱምቡክቱን መሰል ልዩነት ሳያይ ቀርቶ አይደለም፡፡ ከአማራው ወደ ትግራይ ክልል ስትገቡ ከኢትዮጵያ ወደ አውሮፓ የገባችሁ ያህል ይሰማችኋል፡፡ ትግራይ እያንዳንዱ ገጠር ውኃና መብራት ገብቶለታል፡፡ በሣምሬን በኩል ነው ያለፍኩትና ሁሉን ታዝቤያለሁ – ትግራይ ውስጥ ሰው ታጣለህ እንጂ ሥልጣኔና ስይጣኔ በሽ በሽ ናቸው፡፡ በልዩነታችን ሳቢያ አንድ ሀገር ውስጥ መኖራችንን ትረሱታላችሁ፡፡ ተለያይተናል!

— አማራው አካባቢ በሚዲያም እንደሰማሁት አንድም የኤሌክትሪክ ማስፋፊያ ፕሮጀክት በኤልፓ በኩል አልተካሄደም፡፡ ምክንያቱም የፌዴሬል ተብዬውን መሥሪያ ቤቶች የተቆጣጠሩት ትግሬዎች በመሆናቸው ከትግራይና በተወሰነ ደረጃ ከኦሮሞው አካባቢዎች በስተቀር በሌሎች በተለይም በአማራው አካባቢዎች ምንም ዓይነት የልማት ሥራ እንዳይከናወን ሆን ተብሎ ተከልክሏል – ባሕር ዳር አካባቢ እዚህና እዚያ የሚታዩ የዘይት መጭመቂያ ማሽኖች ቢኖሩ ለታይታ ነውና ከቁም ነገር የሚቆጠሩ አይሆኑም፡፡ ማንም ሰው ወደ አማራው አካባቢ ሄጄ ላልማ ቢል በነፍጠኝነትና በዱሮ ሥርዓት ናፋቂነት ተከስሶ ወህኒ ይወርዳል ወይም ከሀገር ይባረራል፡፡ የደሴ ቴርሼሪ ሆስፒታል ፕሮጀክት የተዳፈነበት ምክንያትም ከዚሁ ወያኔ-ትግሬዎች አማራ ላይ ካላቸው ጥላቻና አካባቢው ምንም ዓይነት የልማት አውታር እንዳይኖረው ለማድረግ ቆርጠው ከመነሳታቸው ቁርጠኛና የማይለወጥ ውሳኔያቸው ጋር የሚያያዝ ነው፡፡ ስለዚህ አማራም ሆነ ሌላው የኢትዮጵያ አካባቢ በፍትሃዊነትና በእኩልነት እንዲለማ ከተፈለገ ወያኔዎች ከኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ከጠቅላላዋ ምድራችን ተጠራርገው መጥፋት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህም ይሆናል፡፡

— ሙስናና ወንጀል የወያኔ እስትንፋስ መሆኑ የታወቀ ሆኖ ሳለ በሙስና ስም ሰዎች እየታሰሩ የሚገኙት በሰበቡ አማሮችን ለማጥቃት መሆኑ ከሚያዙት ሰዎች ስም ራሱ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ስኳር ኮርፖሬሽን ይሠራ የነበረና ከሦስት ዓመታት በፊት ለቅቆ ወደሌላ መሥሪያ ቤት በውድድር አልፎ የገባ ሰው አሁን መታሰሩ የሚጠቁመው ሌላ ሳይሆን በዘሩ ሳቢያ ለማጥቃት ብቻ ነው – እንጂ የሙስና ቋንጣ የለውምና ለምን እስካሁን ሳያስሩት ቀሩ ብሎ መጠየቅም ይቻላል፡፡ እነሐጎስና እነግደይ፣ እነአብረኸትና እነፍሬወይኒ በሙስናና በዘረፋ ያከማቹት በቢሊዮን የሚቆጠር ሀብትና ንብረት ሀገር ምድሩን እያስጨነቀ ሳለ ጡጥም እንደፈስ ተቆጥራ ስንሻውና ገመቹ በሏት በተባለች የክትፎ ሙስና የሚሳደዱበትን ምክንያት ከሙስና ቁንጮዎቹ ከአቦይ ስብሃትና ከአባይ ፀሐዬ በስተቀር ማንም አያውቅም፡፡ ዕንቆቅልሽ ምናውቅልህ፡፡  እውነት ለመናገር በአሁኑ ሰዓት በወያኔ ሥርዓት ውስጥ የሚገኝ ምንም ዓይነት ግለሰብም ይሁን ተቋም ሰውን በሙስና ለመክሰስ የሚያበቃ የሞራል ብቃት የለውም፡፡ በዚህ አንገቴን እሰጣለሁ፡፡ አንድ ሰው ከሙስና ውጪ አይኖርም – ልኑር ቢልም አይችልም፤ ልሞክር ብሎ ቢነሳ ዕብደት ነው – በችግር ይቆጋል፤ ማንም ሰው በተለይ የመንግሥት ተቀጣሪው ቴክኖክራትና የቀድሞው ንዑስ ከበርቴ ተብዬ በወር ገቢው መኖር የማይችልበት አሰቃቂ ድህነት ውስጥ ገብቷልና የትም ስትሄድ እየተቁለጨለጨ እጅህን  የሚያየው ሠራተኛ ብዙ ነው፤ ፋይልህ በሥሩ የሚያልፍ ከሆነማ ወደህ ሳይሆን ተገደህ ነው የደንቧን ጠብ አድርገህ ጉዳይህን የምታስጨርስ፡፡ ኢትዮጵያ ቦታ የሌላት ለምሁርና በንጽሕና ልኑር ለሚል ነው –  ቦታ ያላት ለደናቁርትና ለማይማን ብቻ ነው፡፡ ወያኔዎች እውነቱን አጥተውት ሳይሆን ይህን የሙሰኝነት ካርድ የሚጠቀሙበት ሰውን ለማጥቃት ብቻ ነው፡፡ አሻንጉሊቱን ኃ/ማርያምን ጨምሮ ሁሉም የማፊያው ቡድን አባላት ካለሙስ ለአንዲትም ሴከንድ በሕይወት መቆየት አይችሉም፡፡ ይህን ሕዝቡም ሆነ ሌላው የዓለም ማኅበረሰብ ያውቃል፡፡ ነገሩ የሌባ ዐይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ እንዲሉ ነው፡፡ እንትን ላይ ተቀምጦ ፈስ ገማኝ አይባልም፡፡ በግልጽ ለመናገር አንድ ቆማጣም ቆማጣን ቆማጣ ብሎ ሊሰድብ አይቻለውም፡፡ እንደዚህ ዓይነት ነገር ቢገጥም የለዬለት ድንቁርና ወይም ራስን ከመርሣት የሚመነጭ ደደብነት ነው፡፡

— ወያኔ እንደልቡ የሚፈነጭበትን የቀድሞ ኢቲቪ አምኖ በወያኔዎች የፀረ-ሙስና እስርና የዜጎች እንግልት የሚደሰት ወይም “ወያኔ አሁን ገና ወንድ ሆነ!” ብሎ ጮቤ የሚረግጥ ዜጋ ካለ እርሱ የመጨረሻ ገልቱና ከነሱም የባሰ ደንቆሮ ነው፡፡ ወያኔን የሚያውቅ በወያኔዎች አይታለልም፡፡ መታሰርና መሰቀል ያለባቸው ወንጀለኛ ወያኔዎች አንድም ሰው የማሰር ብቻም ሳይሆን በወንጀል የመጠርጠር መብት የላቸውም፡፡ ሁሉም ቃሊቲ ሊታጎሩ ሲገባቸው ወንበሩን ስለያዙት ብቻ አንዳንዴ እንደነሱ ወንጀለኞችን ብዙውን ጊዜ ደግሞ ንጹሓንን በካንጋሩ ፍ/ቤቶቻቸው በስልክ የመሰላቸውን ፍርድ እያስተላለፉ ሲያሰቃዩ ይታያሉ፡፡ ቀን የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል፡፡

— ግብር ጣልን አሉ፡፡ ግብር የጣሉት ከትግሬ ውጪ ላለው ነጋዴ ነው፡፡ የሚገርመው ደግሞ “የግንዛቤ ማስጨበጫ” በሚሉት ጉንጭ አልፋ የቀበሌ ዲስኩራቸው አሳመንናቸው የሚሏቸው ተላላኪ አሽቃባጮቻቸው የሚናገሩት ሁሉ ከእውነቱ የሚጣረስ መሆኑ ነው፡፡ አንድ ሺ አንድ ግንዛቤ ቢጨብጡ በቀን ሁለት መቶ ብር የማታገኝ የመንገድ ዳር ቡና አፍይ ሴት በምን ሂሳብ በቀን 1200 ብር እንደምታገኝ ተሰልቶ ከፍተኛ የቀን ግብር እንድትከፍል የተደረገበትን አመክንዮ ለሰው ማስረዳት ቀርቶ ለራሳቸውም ሊረዱት አይቻላቸውም፤ መቁሽሽ ስለተከፈላቸው ብቻ ቲቪ ላይ ቀርበው በሉ የተባሉትን ይዘባርቃሉ – ሲነጋ ያፍሩበታል፡፡ ዐይናቸውን በጨው ያጠቡ ወያኔዎች ድንጋይን ዳቦ ነው ብለው የማሳመን ችሎታ እንኳን ቢኖራቸው ይህን አዲሱን የግብር አጣጣል ለማሳመን መቼም ቢሆን አይቻላቸውም፤ በኃይል ከሆነ ልክ ነው፡፡ አንድ ወቅት የመለስ ፍየል ጠፋችና ፌዴራል በያቅጣጫው ፍለጋ ገባ አሉ፡፡ በመጨረሻም አንዱ ቡድን አገኛትና ወደ መለስ ቤተ መንግሥት ይዟት ቀረበ፡፡ መለስም ወጣና አያት፡፡ ሲያያት ግን በዱላ የተቀጠቀጠችና ደም በደም የሆነች ትንሽዬ የመንደር ውሻ ናት፡፡ “እንዴ! የጠፋኝ እኮ ፍየል ነው፤ እንዴት ይቺን ውሻ ፍየል ናት ብላችሁ ታመጣላችሁ” ብሎ ያፈጥባቸዋል አሉ፡፡ እነሱም ቀበል አደረጉና “ብፃይ መለስ፣ ስንደበድባት ፍየል መሆኗን አምናለች፡፡” አሉት አሉ፡፡ በዚህ መልክ ነው  እንግዲህ ላለፉት 26 ዓመታት አናት አናታችንን እየተቀጠቀጥን እርቦን ሳለ እንደጠገብን፣ ታርዘን ሳለ እንደለበስን፣ ተጎሳቁለን ሳለ እንዳማረብን፣ ከስተን ሳለ እንደወፈርን… አምነን እንድንቀበልና ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም እንድንመሰክር በወያኔ ትግሬዎች እየተገደድን አሳራችንን ስንበላ የከረምነው፡፡ ሰይጣን እጁን ታጥቦ ከጠፈጠፋቸው አጋንንታዊ ሥሪቶቹ መካከል እንደወያኔ መቶ በመቶ ስኬታማ የሆነ አለ ብዬ አላስብም፡፡

— የማፊያው የወያኔ ቡድን አባላት ከንጉሥም በላይ ናቸው፡፡ መግደልን ጨምሮ የፈለጉትን ወንጀል ቢሠሩ፣ ዘረፋና ንጥቂያ ቢያካሂዱ ማንም አይነካቸውም፡፡ ሕግ የለም፡፡ ፖሊስ የለም፡፡ ዳኛ የለም፡፡ ፍርድ ቤት የለም፡፡ ለነሱ ምንም ነገር አይሠራም፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ አንድ ሰው መኪናውን ከበስተኋላው አንድ ሰው ይገጭበታል፡፡ ተገጪው ወርዶ መኪናውን ሲያይ በጣም ተጎድታበታለች፡፡ ገጪውም ይወርድና “አሥር ሺህ ብር ልስጥህና እዚሁ እንገላገል” ይለዋል፡፡ ተገጪው ግን የመኪናው ጉዳት ከባድ በመሆኑ ትራፊክ ፖሊስ ያስመጣል፡፡ … ጉዳዩ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሲሄድ ነገሩ ይዞርና ወንጀሉ ወደ ተገጪው እንዲዞር ይደረጋል፡፡ ትራፊክ ፖሊሱም “ወንድሜ! ባለሥልጣን አይከሰስም፡፡ እሳቸው ባለሥልጣን ስለሆኑ በሰላም መገላገል ከፈለግህ ዝም ብለህ ወደቤትህ ሂድና የራስህን በራስህ አሠራ፡፤ ኋላ ነግሬሃለሁ!”  ብሎ ያባርረዋል፡፡ ወደፊት ልግፋ ቢል ዘብጥያ ሊወርድ ሆነ፡፡ መኪናውን 50 ሺህ ብር አውጥቶ አሠራት፡፡ ይህ ሰው “ሀገሬ የት ነው? እኔስ ማን ነኝ?” እያለ እንደመወፈፍ አድርጎታል፡፡ እርግጥ ነው – ሀገር የለንም፡፡ ባለሥልጣን ከሆንክና በዚያ ላይ ትግሬነትን ከደረብክበት ሁሉ በጅህ ሁሉ በደጅህ ነው፡፡ ትግሬ ሆነህ ማንንም ከቀየው አፈናቅለህ ያሻህን ቦታና የመኖሪያ ቤት ብትይዝ ዳኛህ ኅሊናህ እንጂ በኢትዮጵያ አንድም የሚገዳደርህ ህግ የለም፡፡ ማሳሰርና ማስፈታት፣ ማስገረፍና ደብዛን ማስጠፋት መብትህ ነው – ከአንተ የሚጠበቀው ወያኔ ትግሬ መሆን ብቻ ነው፡፡  ይህችን የዘመን ህግ መርሳት የለብም፡፡ አደራህን ግን መከራህ ተዝቆ አያልቅምና አማራ ሆነህ መፈጠርን እንዳትመርጥ! ኦሮሞ መሆን ትችል ይሆናል፤ ነገር ግን ከወንድሞችህ ጋር እንዳያጣሉህ ጠንቀቅ በል! ነገም ሌላ ቀን ነውና፡፡

የምትጠላውን ገድለህ ወይ አስገድለህ ተንቀባረህ የምትኖርባት ሀገር – ኢትዮጵያ! የፈለግኸውን ወንጀል ሠርተህ በገንዘብህና በነገድህ ተማምነህ በነፃነት የምትኖርባት ሀገር – ኢትዮጵያ! በድለህ ዘንጠህ የምትኖርባት ሀገር – ኢትዮጵያ! ደንቁረህ እንደምሁር የምትቆጠርባት ሀገር – ኢትዮጵያ! ሳትማር የፈለግኸውን ዲግሪ የምትጭንባት ሀገር – ኢትዮጵያ! ወንጀለኞችን አቅፎና ደግፎ አሞላቅቆ የሚይዝ የወሮበሎች መንግሥት ያለባት ብቸኛዋ ሀገር – ኢትዮጵያ! ጊነስ ቡክ ኦፍ ሪከርድስ ባላወቀውና ባልመዘገበው ሁኔታ ቤተ መንግሣቷን ወላድ አትይሾች የሚፈነጩባት ጉደኛ ሀገር – ኢትዮጵያ! አዲዮስ ኢትዮጵያ፡፡

—   አሁን ደግሞ በወያኔ የተጠለፈችው ቤተ ክርስቲያን ሕዝቡ እንዳይቀበር ዋጋ ቆልላች፡፡ ለአንድ አስከሬን 4 ሺህ ብር! አራት ሺህ ብር ካልተከፈለ ወስዳችሁ የፈለጋችሁት ቦታ ጣሉ እየተባልን ነው፡፡ ጉድ ፈላብን፤ ጉዳችን ተንተከተከ፡፡ አፄውና ደርጉ በጉያቸው ይዘውት የነበረው ገመናችን ወጥቶ ፀሐይ እያንቃቃው ነው፡፡ ካህናቱም ከፓትርያርክ እስከ ዲያቆን የአጋንንት ውላጅ ሆኑብንና ከወያኔው ባልተናነሰ ከዱርየው የወያኔዎች መንግሥትና ከዲያብሎስ ጋር እየተሸራሞጡ ቁም ስቅላችንን እያሳዩን ነው፡፡ የቀብር ቦታ ይሸጣሉ፤ በጉቦና በሙስና ሥራ ያሲየዛሉ፤ ከዝቅተኛ ደብር ወደ ትልቅ ደብር በሊቀ ገበዝነት ለመዛወር በመቶ ሺዎች ጉቦ ይከፈላ፡፡ የማይሠራ ወንጀልና ኃጢኣት የለም፡፡ ብለው ብለው እኛንም ያለችንን ብቸኛ መጽናኛ ሞትንም ሊከለክሉን ነው፡፡ ቆመን ዕዳ፤ ሞተንም ዕዳ – እንኑር እምቢ – እንሙትም እምቢ፡፡ ለሞተውስ ግዴለም – ተገላገለ፡፡ ወስፋቱን የሚሸነግልበት ቤሳቤስቲን የሌለው ድሃ ቤተሰብ አንድ ወገኑ ሲሞትበት ቆጥሮት የማያውቀውን የገንዘብ መጠን ለሬሣ ማስቀበሪያ ይጠየቃል፡፡ እግዚአብሔርም ከሰው ተደርቦ ጨከነ፡፡ ዝም አላቸው፡፡ ዝምታውም የመቃብር አዘቅት ያህል እጅጉን ገነነ፡፡ ወዮ በሉ! ወዮ ለኢትዮጵያ! ለአንዲት ከርስ መሙያ ለብጣሽ እንጀራ ብሎ ሀበሻ ሊጨራረስ ነው!

— አሥራት አብርሃም ሰሞኑን ግሩም መጣጥፍ ጻፈ፡፡ ግን ምን ዋጋ አለው – “ወጣ ወጣና እንደሸንበቆ ተንከባለለ እንደሙቀጫ” ሆነና ዐረፈው፡፡ አሥራት ወያኔን አያውቅም ወይም ሞኝነት ያጠቃዋል፡፡ ከዚህ አልፌ እርሱን በድጋፍ ሰጪነት መፈረጅ ግን ኅሊናየ አልፈቀደልኝም – ምንም እንኳን የሕወሓት ቫይረስ የሚሞተው በሺዎች ዲግሪ ሴልሼስ መሆኑን ብረዳም፡፡ አሥራት ወያኔን ቢያውቅ ኖሮ ከመጣጥፉ የጠቀስኩትን ከዚህ በታች ያለውን ሃሳብ በጽሑፉ ውስጥ አይጨምርም ነበር፡፡ ወያኔ ከመቼ ጀምሮ ነው ተከሶ ፍርድ ቤት ቀርቦ የሚያውቅና የተፈረደበት? “የዕብድ ገላጋይ ድንጋይ ያቀብላል” ይባላል፡፡ አሥራት ትልቅ ስህተት ፈጽሟልና በዚህችስ አደራችሁን ጠይቁልኝ፡፡ ክፉኛ ታዝቤዋለሁ፡፡ “ወያኔ ነፃ ፍርድ ቤትን፣ ዴሞክራሲን፣ ሰላምን፣ ፍትህን፣ እኩልነትን አጥፍቶ በምትካቸው ስደትን፣ ሞትን፣ ግድያና እስራትን፣ ችግርንና ስቃይን በማስፈኑ አይደለም ወይ ይሄ ሁሉ ሀገራዊ ትርምስና ዕልቂት የተፈጠረው” ብላችሁ ለአሥራት ንገሩልኝ፡፡ አሥራት በዚህች ሃሳቡ ብቻ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ መጠየቅ ይኖርበታል፡፡ ወያኔ ከሳሽ፣ ወያ ዳኛ፣ ወያ ጠበቃ፣ ወያ ዐቃቤ ህግ፣ ወያ ፖሊስ፣ ወያ እስረኛ ጠባቂ፣ ወያ ሁሉም ነገር በሆነባት ሀገር ውስጥ ማን ነው ማንን የሚከሰው? በማወቅም ይሁን ባለማወቅ እንዲህ የሚል ሰው ለማያውቁት ይታጠን፡፡ I don’t know whether he wants to legitimize TPLF or not, nevertheless; he shouldn’t dare say  ‘TPLF must bring TPLF to the court of TPLF whose prosecutor and judges are TPLFites’. So funny! What, perhaps, an absolute innocence!

“… ባለአንድ መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎች ደግሞ የጋራ ኮሚቴ ማቋቋምና መንግስት መጠየቅ አለባቸው። ጉዳዩም ወደ ፍርድ ቤት ነው መሄድ ያለበት። ምክንያቱም ፕሮግራሙ አሁን በታደለው የክራውንና የሰንጋ ተራ ኮንዶምኒየም በግልፅ የታጠፈ በመሆኑ ከዚህ በኋላም በሌሎች ኮንዶምኒየም ባለአንድ መኝታ እንዳለማወቅ አይቻልም። ስለዚህ ተመዝጋዎቹ ጉዳዩን ወደፍርድ ቤት መውሰድ ነው ያለባቸው የሚል እምነት ነው ያለኝ። (አፅንዖት የተጨመረ)

mz23602@gmail.com

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

♦ “ ትክክለኛ ፍትሕ አይሰጡም” የተባሉት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ከችሎት እንዲነሱ ተጠየቀ !

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar